ከማይካድራ በቅርብ ርቀት ላይ በተደረገ ፍተሻ የትህነግ የጦር መሳሪያ እና ማሰልጠኛ ተገኘ         አሻራ ሚዲያ     ህዳር 27/2013 ዓ.ም ባህር ዳር በወልቃይት…

ከማይካድራ በቅርብ ርቀት ላይ በተደረገ ፍተሻ የትህነግ የጦር መሳሪያ እና ማሰልጠኛ ተገኘ አሻራ ሚዲያ ህዳር 27/2013 ዓ.ም ባህር ዳር በወልቃይት…

ከማይካድራ በቅርብ ርቀት ላይ በተደረገ ፍተሻ የትህነግ የጦር መሳሪያ እና ማሰልጠኛ ተገኘ አሻራ ሚዲያ ህዳር 27/2013 ዓ.ም ባህር ዳር በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ከማይካድራ ከተማ በቅርብ ርቀት በሚገኝ የእርሻ ካምፕ ውስጥ የአማራ ልዩ ኃይል ፖሊስ ባደረገው ፍተሻ የወራሪው፣ ተስፋፊውና አሸባሪው ትህነግ የጦር መሳሪያዎችና ማሰልጠኛ ተገኝቷል። በካምፑ ውስጥ ከአንድ ሽህ በላይ የተለያዩ ፈንጆችም ተገኝተዋል። የእርሻ ካምፑን የወራሪው፣ ተስፋፊውና አሸባሪው ትህነግ ቡድን አመራሮች ሲጠቀሙበት የቆየ ነው፡፡ የአማራ ልዩ ኃይል ፖሊስ የቴዎድሮስ ብርጌድ ምክትል አዛዥ ሎጀስቲክ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ዘመድ ግርማው እንደገለፁት አሸባሪዎችን ሲያሠለጥኑበት በነበረው ካምፕ የራዲዮ መገናኛዎች፣ ለሽብር ተግባር ሊውሉ የነበሩ የተለያዩ ሃገራት ወታደራዊ ልብሶች፣ የአልሸባብ እና የኦነግ ሸኔ ወታደራዊ ልብሶች፣ የሠው ማሠቃያ ሠንሰለቶች፣ መፅሐፎች፣ ካሴቶች፣ ሲዲዎች እና የተለያዩ ፈንጆች ተገኝተዋል። በአንድ መካዘን ውስጥ ከተገኙት ፈንጆች መካከል 700 ፀረ ሰው ፣ 200 ፀረ ታንክ ፣ 200 ሳሙና መሠል ፈንጂ እና ከ100 በላይ ፀረ ፎቅ ወይም ፀረ ድልድይ ፈንጅዎች ተገኝተዋል። ዘጋቢ፡- ማርሸት ጽሀው ዘወትር አዳዲስ መረጃ እንዲደርስዎ https://t.me/asharamedia24 በመጫን ይቀላቀሉን። ዩትዩብ፥ https://bit.ly/33XmKro ላይክ እና ሰብስክራይብ ያድርጉን

Source: Link to the Post

Leave a Reply