ከምስራቅ ቤዝ በሚነሱ አውሮፕላኖች ኬሚካል ርጭት በሶማሌ ክልል የተከተሰው የአንበጣ መንጋ በቁጥጥር ስር እየዋለ ነው-ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

ከምስራቅ ቤዝ በሚነሱ አውሮፕላኖች ኬሚካል ርጭት በሶማሌ ክልል የተከተሰው የአንበጣ መንጋ በቁጥጥር ስር እየዋለ ነው-ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሶማሌ ክልል የአንበጣ መንጋ ያደረሰውን ጉዳት ጎበኙ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጉብኝቱን አስመልክተው በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው እንዳሉት ÷ ከምስራቅ ቤዝ በሚነሱ አውሮፕላኖች ኬሚካል ርጭትም መንጋው አሁን በቁጥጥር ስር እየዋለ ነው::
በሌላ በኩል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአውባረ ወረዳ በ100ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የሚመረተው ሰብል ውስጥ የስንዴና ሌሎች ዘሮች ማሳ ጎብኝተዋል።
በዚህም እንደ መጀመሪያ በሄክታር 30 ኩንታል ምርት መመረቱ ጥሩ ቢሆንም በቀጣይ ምርታማነቱን ማሳደግ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።

The post ከምስራቅ ቤዝ በሚነሱ አውሮፕላኖች ኬሚካል ርጭት በሶማሌ ክልል የተከተሰው የአንበጣ መንጋ በቁጥጥር ስር እየዋለ ነው-ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply