ከምስራቅ አማራ ፋኖ የተሰጠ የአቋም መግለጫ አማራነት እንደ ወንጀል ተቆጥሮ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አለ የተባለ ግድያ ጭፍጨፋ እና በአጠቃላይ ዘር ማጥፋት በአማራ ህዝብ ላይ ተፈፅሟል። እየተ…

ከምስራቅ አማራ ፋኖ የተሰጠ የአቋም መግለጫ አማራነት እንደ ወንጀል ተቆጥሮ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አለ የተባለ ግድያ ጭፍጨፋ እና በአጠቃላይ ዘር ማጥፋት በአማራ ህዝብ ላይ ተፈፅሟል። እየተፈጸመም ይገኛል። ይህ ድርጊት የተቀነባበረ ታሪካዊ የሀገራችን ጥላቶች ጋር ትስስር ያለው አማራ አንደ አማራ መኖር ቀርቶ አማርኛ ተናጋሪ እንዳይኖር በማይፈልጉ እንደ ኦነግ እና የትግራይ ወራሪ ሀይል ጥምር ሃይሎች የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ እየተፈጸመበት ይገኛል። አስተዋይነቱ የበዛው ህዝባችን በሁሉም አካባቢ የአብርሃም በግ ሁኖ ሲታረድ ተው ይህ መጠፋፋት ሀገርን እንደ ሃገር አያቆምም በሚል እሳቤ ትዕግስቱ እንደ ባህር ጥልቅ መሆኑ በጥላት በኩል አንድም በፍረሃት አሊያም አቅመቢስነት ሲያልፍም ጅላጅል ቂልነት እና ግዑዝ አካል አድርገው ቆጥረዉታል። በሁሉም ያልፋል እሳቤ ከዚህ በላይ መታገስ እንደ ኩርድ ሀገር አልባ እንደ አሜሪካ ኢንዲያን ዘራችን እንዲጠፋ መተባበር መሆኑን ሁሉም ህዝባችን ሊያውቀው የሚገባ የፀሃይ እውነት ነው። እጅግ አሳሳቢው ነገር አማራን የማጥፋት ህልማቸውን ለማሳካት የታቀደ የተቀነባበረ በመሪዎች የሚመራ ድርጊቱ እጅግ የከፋ መዋቅራዊ ሰንሰለት ያለው በቅብብሎሽ የሚፈፀም መሆኑ ነው። የወለጋው መዋቅር መራሽ ጭፍጨፋ ሀዘናችን ሳይወጣ በየቀኑ የአማራ ደም ካልፈሰሰ የደም ስካራቸው የማይበርድ የዘመኑ ፊት አውራሪዎች እሳቱን ስበው ቀያችን ድረስ በማምጣት በአጣየ እና አካባቢው ለኩሰውታል። በዚህ ድርጊታቸውም ደራሽ አልባው ህዝባችን እየተቃጠለ ይገኛል። በተለይ ከሰሞኑ በአጣየ እና አካባቢው ህዝብ ብሎም በአማራ ልዩ ሀይል ላይ የተፈፀመው ድርጊት አማራው ላይ የታወጀው የዘር ማጥፋት እንደሆነ ትልቅ ማሳያ ነው። ይባስ ብሎ የውስጥ የፖለቲካ ብሶቱን አማራን የማጥፋት ፓሊሲውን ለመፈፀም ከዚህ ቀደም እሰከ ሰሜን ሸዋ ድረስ ወረራ የፈጸመው የትግራይ ወራሪ ሃይል መግስት ያቀረበለትን የሰላም የመደራደሪያ ሀሳብ ውድቅ በማድረግ ለዳግም ወረራ ተዘጋጅቶ የትግራይን መሬት አስመልሳለሁ በሚል አባዜ ወረራ ለመፈፀም ተዘጋጅቻለሁ የሚል መግለጫ ጋጋታ በቡችላው ጌታቸው ረዳ በኩል መተንፈስ ጀምረዋል። ከዚህ አንፃር ፦ 1.መላው ህዝባችን ለአይቀሬው የህልዉና ትግል እራሱን አንዲያዘጋጅ እና ራያ ግንባር እንዲከት! 2. በሁሉም አካባቢ ያለ የታጠቀ ያልታጠቀ ህዝባችን እንደ ህዝብ ተደራጅቶ ትግሉን በመቀላቀል እኛ ተሰዉተን ቀሪው ህዝባችን ፍትህ እኩልነትና ነጻነት ሰፍኖለት በሰላም የሚኖርበትን አውድ መፍጠር ይኖርብናል! 3.የፊት ተዋጊ ግንባር ሲገባ የኋላ ደጀን ሀይላችን ትጥቅና ስንቅ በማቀበል እንዲያግዝ ባለው አደረጃጀት እንዲጠባበቅ ስንል መልክታችንን እናስተላልፋለን። በመጨረሻም በህግ ማስከበር ስም አማራዉን እርስ በርሱ ለማጋጨት እና ያለዉን አንድነቱን ጭምር ለማሳጣት ብሎም የከፋ ማህበራዊ ቀዉስ ዉስጥ እንዲገባ ታስቦ እየተሰራ መሆኑን ሁሉም የአማራ ህዝብ የጸጥታ አደረጃጀቶች የጋራ መግባባት ላይ በመድረስ ህዝባችንን ደጀን አድርገን የጋራ ጠላቶቻችንን በጋራ እንድንታገል ስንል በአማራ ህዝብ ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን! ” ፋኖነት ለኢትዮጵያዊነት ህያው ምስክር ነው።”

Source: Link to the Post

Leave a Reply