ከምስራቅ አማራ ፋኖ የተሰጠ የአቋም መግለጫ አምስተርዳም :- ሰኔ 29/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ የአባቶቻችንን የደም አርበኝነት እና የግብር ፋኖነት መቼ…

ከምስራቅ አማራ ፋኖ የተሰጠ የአቋም መግለጫ አምስተርዳም :- ሰኔ 29/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ የአባቶቻችንን የደም አርበኝነት እና የግብር ፋኖነት መቼም በምንም ሁኔታ አንተዉም! የሰሜን ወሎ ዞን ከፍተኛ የፖለቲካ እና የጸጥታ አመራሮች ሰኔ 28/2014 ዓ.ም ራያ ግንባር ምሽግ ላይ የሚገኘዉን ታላቁን የምስራቅ አማራ ፋኖ ስራ አስፈጻሚ ወልድያ ከተማ ስብሰባ ጠርተው በአንዳንድ ጉዳዮች ዙሪያ አነጋግረዉናል። ስለሆነም የዞኑ ከፍተኛ አመራሮች ለስብሰባ ሲጠሩን በራያ ግንባር ባለው ወቅታዊ የጠላት አሰላለፍ ሁኔታ ጉዳይ ዉይይት ለማድረግ ብለው ነበር። ነገር ግን የዉይይቱ ጉዳይ ሌላ አቅጣጫ ይዞ አግኝተነዋል። ነገሩ እንዲህ ነው የዞኑ ከፍተኛ የፖለቲካ እና የጸጥታ አመራሮች ፋኖ ላይ አቅጣጫዎች አስቀምጠዋል። 1.ፋኖ ሙሉ ለሙሉ ወደ ሚሊሻ መግባት አለበት! 2. በማንኛዉም ሁኔታ ፋኖ ከህዝብ የገንዘብ ድጋፍ ማሰባሰብ አይችልም የሚሉ አቅጣጫዎችን አስቀምጠዋል። ስለሆነም የሰሜን ወሎ ዞን ያስቀመጣቸዉን አቅጣጫዎች በተመለከተ የምስራቅ አማራ ፋኖ አቋም የሚከተሉት ናቸው:- 1. ፋኖነት ስማችን ብቻ ሳይሆን ደምና አጥንት የተገበረለት የአባቶቻችን ዉርስ ዛሬም ያለ ወደፊትም ከአማራ ህዝብ ጋር ህያው ሆኖ የሚኖር ስሪታችን ነው። አባቶቻችን በአድዋ በማጨው በጋራ ሙለታ በመቅደላ መድፍና ታንክ ይዞ የመጣ የዉጭን ወራሪና ቅኝ ገዥ ሃይል በባህላዊ መሳሪያ በጦርና ጋሻ አንበርክከው የቀጡበትና ዋጋ የከፈሉበት እምቢ ለአገሬ ለነጻነቴ ብለው በፋኖነት እንጂ ሌላ ተቀጽላ ወይም የተዉሶ ስም አልነበራቸዉም። ስለሆነም ከአባቶቻችን የወረስነዉን ፋኖነት እኛ አልፈንበት ለልጆቻችን የምናወርሰው ቅርሳችን መሆኑን እናሳዉቃለን። 2.ፋኖ ያለ ደመወዝ ለአማራ ህዝብ ብሎም ለሃገሩ ኢትዮጵያ አንድ ህይወቱን ለመስጠት የተዘጋጀ እየሰጠም ያለ ስለሆነ ህዝብ በትጥቅ እና ስንቅ እንዲደግፈን አጥብቀን እንሰራለን። 3. በቆቦ ከተማ እና በራያ ቆቦ ወረዳ በሁሉም ቀበሌዎች መንግስት በፋኖ ስም የሚሰበሰበው ገንዘብ የፋኖ አለመሆኑን ሁሉም ህዝባችን እንዲያውቀዉ እና ግንዛቤ እንዲኖረው ለማሳወቅ እንወዳለን። 4. የትግራይ ወራሪ ሃይል ለዳግም ወረራ በተዘጋጀበት እና ተደጋጋሚ በመግለጫዎቻቸው የአማራን ህዝብ በጠላትነው ፈርጀው ከሚንቀሳቀሱበት አላማቸው የአማራን ህዝብ እንደ ህዝብ ለማጥፋት እና በሃገሩ ሃገር አልባ ለማድረግ በአማራ ጉዳይ ጠላቴ ከሚሉት ጋር አንድ ሆነው አጀንዳ እየሰጡ በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች አማራ መሆኑን እንኳን የማያውቅ የአርባ ቀን ህጻን ሳይቀር እና አማራ እንዳይሆን ከእናቱ ሽል ጭምር እየተተለተለ በግፍ የሚጨፈጨፍበት ወቅት ላይ ሆነን እንደዚህ አይነት አጀንዳ ማንሳቱ ወቅቱን ያላገናዘበ ድርጊት መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን። በመጨረሻም ፋኖ የተጀመረው የአማራ ህዝብ ሁለንተናዊ ትግል ዳር ደርሶ የትግራይ ወራሪ ሃይል እና በግብር የሚመስሉት የአማራ ብሎም የኢትዮጵያ ሃገራችን ጠላቶች ለሃገር እና ለህዝብ ስጋት በማይሆኑበት ደረጃ ከደረሱ እና ፍትህ እኩልነትና ነጻነት ከተረጋገጠ ፋኖ ወደ መደበኛ ሰላማዊ ህይወቱ የሚመለስ መሆኑን በምስራቅ አማራ ፋኖ ስም ለመግለጽ እንወዳለን። “ፋኖነት ለኢትዮጵያዊነት ህያው ምስክር ነው።” ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply