ከምስራቅ ወለጋ ተፈናቅለው በአዲስ አበባ አስኮ ለሚገኙ አማራዎች የጾም መያዣ ዝግጅት ተደርጓል!! ባህርዳር :- የካቲት 19/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ከምስራቅ…

ከምስራቅ ወለጋ ተፈናቅለው በአዲስ አበባ አስኮ ለሚገኙ አማራዎች የጾም መያዣ ዝግጅት ተደርጓል!! ባህርዳር :- የካቲት 19/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ከምስራቅ ወለጋ ተፈናቅለው በአዲስ አበባ አስኮ የሚገኙ አማራዎች ቁጥራቸው 50 ይሆናሉ። እነዚህ በችግር እየተፈተኑ ያሉ ተፈናቃይ ወገኖች የጾም መያዣ ዝግጅት ተደርጎላቸዋል። በዝግጅቱም ጋዜጠኛ መዓዛ መሀመድ፣ ባንችአየሁ ክንዴ፣ ሉሊት እና እኔም ዓባይ ዘውዱ ተገኝተን፤ በመንግስት ዘንድ አስታዋሽ ያጡ ወገኖቻችን የኑሮ ሁኔታ ተመልክተናል። በዝግጅቱ የተገኙ ወንድም እና እህቶችም ችግሩ ይፈታ ዘንድ ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ አድርገዋል፤ ከጎናቸው እንደማይለዩም በመግለጽ ተባብረውና ተከባብረው እንደ አማራ የገጠመንን ሁለንተናዊ ችግር እንዲያልፉ መክረዋል። ከወለጋ ተፈናቅለው በአዲስ አበባ ቆይተው መንግስትን የሰብአዊ ድጋፍ እንዳይጠይቁ ወደ አርሲ አቦምሳ ከዛም ወደ ምስራቅ ሸዋ ዞን አዋሽ መልካሳ በኃይል ተጭነው የተወሰዱት፣ ከቤተሰብና ከሚዲያ ጋር እንዳይገናኙ ስልካቸውን የተነጠቁት የአማሮች ጉዳይም አሳሳቢ መሆኑ ተገልጧል። በጾም መያዣ የማዕድ ማጋራት ዝግጅቱም ብዙዎች ተገኝተው ተሳትፈዋል፤ ከበጎ ፈቃደኞች ለተደረገላቸው እና ለሚደረግላቸው ድጋፍም ከፍ ያለ ልባዊ ምስጋና አቅርበዋል። የካቲት 19 ቀን 2014 በተደረገው አጭር የጾም መያዣ መርኃ ግብር ላይ የተገኙ በሀገራቸው ላይ ሀገር አልባ የተደረጉ አማራዎች መንግስት እስካሁን አንዳችም የሰብአዊ ድጋፍ እና እውቅና እንዳልሰጣቸው ተናግረዋል። በጎ ፈቃደኞች የሚያደርጉት እገዛ እንዳለ ሆኖ የሰብአዊ ጉዳይ ያገባናል የምትሉ ተቋማትና መንግስት ሁሉ በዘላቂነት ማቋቋምን በተመለከተ ትኩረት ሰጥታችሁ እንድትሰሩ ተጠይቃችኋል። ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- ቴሌግራም :- https://t.me/asharamedia24 Facebook :- https://www.facebook.com/asharamedia24 youtube :- https://www.youtube.com/channel/UChir2nIy58hlLQRYyHIQeHA

Source: Link to the Post

Leave a Reply