ከምስራቅ ወለጋ ዞን ኢበንቱ ወረዳ ተፈናቅለው በቡሬ ከተማ አስተዳድር የሚገኙ አማራዎች አስቸኳይ የሰብዓዊ እርዳታ እንዲደረግላቸው ተጠየቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 14 ቀን 201…

ከምስራቅ ወለጋ ዞን ኢበንቱ ወረዳ ተፈናቅለው በቡሬ ከተማ አስተዳድር የሚገኙ አማራዎች አስቸኳይ የሰብዓዊ እርዳታ እንዲደረግላቸው ተጠየቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 14 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ከኦሮሚያ ክልል “ከምስራቅ ወለጋ ዞን ኢበንቱ ወረዳ የተፈናቀሉ አማራዎች በቡሬ ከተማ አስተዳድር ውስጥ ተጠልለው ይገኛሉ ተብሏል፡፡ ተፈናቃዮች በወረዳው ከ7-18 ዓመታት የኖሩበትን አካባቢ የሚቀይሩት ልብስ እንኳ ሳይዙ ነው ለሁለት ሳምንታት በጫካ ውስጥ ሲጓዙ ቆይተው ነው ወደ ቡሬ የደረሱት፡፡ ከተፈናቃዮች መካከል በወለደች ሁለት ቀን የሆናት እናት የምትገኝ ሲሆን ደም እየፈሰሳት ሁለት ሳምንት ጫካ ላይ ቆይታ ነው ቡሬ ላይ የደረሰችው ተብሏል፡፡ ከዚህም ሌላ አንዲት የአምስት ልጆች እናት በልጆቿ እና እሷ ፊት ባለቤታቸውን ገድለውባታል፡፡ ከምንም በላይ ግን እነዚህ ሰዎች ለ2 ሳምንት ያህል በብርድ፣ በረሃብ፣ እና በፍርሃትና ሃዘን ተቆራምተው ቡሬ ከተማ ላይ የደረሱ ሲሆን፣ በወቅቱም የቡሬ ዙሪያ የሙዚቃ ቡድን ለዳቦ የሚሆን እርዳታ ለመሰብሰብ ሲሞክሩ ታይተዋል፡፡ በርካታ ህፃናት አሁንም የምግብ ያለህ እያሉ እየጮሁ ናቸው፡፡ የደረሰባቸውን በደልና ሰቆቃ እረፍት የሚነሳ ስለመሆኑ ተገልጧል። አስቸኳይ የሰብአዊ እርዳታ የሚፈልጉ ስለመሆናቸውም የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲ መምህርን ደሳለው ጌትነትን በመጥቀስ በይፋዊ የማህበራዊ የትስስር ገጹ ያጋራው ጋዜጠኛ በላይ ማናዬ ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply