ከምስራቅ ወለጋ ዞን ኪረሞ ወረዳ ለደህንነታችን ዋስትና የሚሰጥ የመንግስት አካል የለም በሚል ከአካባቢው ለቀው ለመውጣት የሚሞክሩ አማራዎች በኦሮሚያ ልዩ ኃይል ክልከላ እና ወከባ እየደረሰባቸ…

ከምስራቅ ወለጋ ዞን ኪረሞ ወረዳ ለደህንነታችን ዋስትና የሚሰጥ የመንግስት አካል የለም በሚል ከአካባቢው ለቀው ለመውጣት የሚሞክሩ አማራዎች በኦሮሚያ ልዩ ኃይል ክልከላ እና ወከባ እየደረሰባቸ…

ከምስራቅ ወለጋ ዞን ኪረሞ ወረዳ ለደህንነታችን ዋስትና የሚሰጥ የመንግስት አካል የለም በሚል ከአካባቢው ለቀው ለመውጣት የሚሞክሩ አማራዎች በኦሮሚያ ልዩ ኃይል ክልከላ እና ወከባ እየደረሰባቸው መሆኑ ተነገረ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 21 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን ኪረሞ ወረዳ የካቲት 18 ቀን 2013 ዓ.ም ኦነግ ሸኔ በሚባለው የሽብር ቡድንና በተባባሪዎችቹ 12 አማራዎች በስለት የመታረዳቸውን ልብ የሚሰብር ዜና መዘገባችን ይታወሳል። ሾፌሮች አስከሬን ጭነን እንዳንወጣ ተከልክለናል በማለታቸውም የሁሉም ሟቾች ስርዓተ ቀብር በኪረሞ ወረዳ በቦቃ እና ጨቤ ቀበሌ መፈፀሙ አይዘነጋም። ከግድያ የተረፉ እና ዋስትና የሚሰጣቸው የመንግስት አካል ያጡ በርካታ አማራዎች አሁን ላይ በኪረሞ ወረዳ በየበረዳው እያደሩ በብርድ፣በውሃ ጥምና በርሀብ እየሰቃዩ መሆናቸውን የደረሰን መረጃ አመልክቷል። ወደ መናኸሪያ አቅንተው ወደሌላ አካባቢ ለመሳፈር ሲሞክሩም በኦሮሚያ ልዩ ኃይልና በአካባቢው ፖሊሶች ድብደባና ወከባ እንደሚፈፀምባቸው ከስፍራው ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች ገልፀዋል። በሁኔታው የተከፉና ዋስትና ያጡ የኪረሞ ነጋዴዎችንም ለምን ሱቅ ዘጋችሁ በሚል ሲደበድቡና በኃይል እንዲከፍቱ ሲያደርጉ የተመለከተ የዐይን እማኝም ነገሮች ሁሉ አሳሳቢ መሆናቸውን ጠቁሟል። መንግስት ከጅምላ ግድያ ከመታደግ ይልቅ እያስገደለን መሆኑን እወቁልን፤ ለመላው አማራና ኢትዮጵያዊ፣ለሚዲያ ተቋማትና ለአለም አቀፍ ማህበረሰብ በሙሉ እውነታውን አሳውቁልን ሲሉ ተፈናቃይ አማራዎች ጠይቀዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply