You are currently viewing ከምስራቅ ወለጋ ዞን ጎቡሰዮ እና ስቡስሬ ወረዳ ተፈናቅለው ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ከነበሩበት የወረዳ 15 ጊዜያዊ መጠለያ እንዲወጡ የተደረጉ አማራዎች የወገንን እርዳታ ጠየቁ። አማራ ሚዲያ…

ከምስራቅ ወለጋ ዞን ጎቡሰዮ እና ስቡስሬ ወረዳ ተፈናቅለው ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ከነበሩበት የወረዳ 15 ጊዜያዊ መጠለያ እንዲወጡ የተደረጉ አማራዎች የወገንን እርዳታ ጠየቁ። አማራ ሚዲያ…

ከምስራቅ ወለጋ ዞን ጎቡሰዮ እና ስቡስሬ ወረዳ ተፈናቅለው ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ከነበሩበት የወረዳ 15 ጊዜያዊ መጠለያ እንዲወጡ የተደረጉ አማራዎች የወገንን እርዳታ ጠየቁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል ህዳር 10 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ከምስራቅ ወለጋ ዞን ጎቡሰዮ እና ስቡስሬ ወረዳ በማንነታቸው ምክንያት ከደረሰባቸው ዘርፈ ብዙ ጥቃት በታዓምር ተርፈው ወደ አዲስ አበባ ከመጡት ተፈናቃይ ወገኖች ጋር ቆይታ አድርገናል። ከጥቅምት 29 ቀን 2014 ጀምሮ በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ወረዳ 15 በአሁኑ አደረጃጀት በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 15 በወጣቶች ማዕከል ለአንድ ሳምንት ተጠልለው ከቆዩ በኋላ ነበር ህዳር 7 ቀን 2014 ተገደው ከመጠለያ እንዲወጡ የተደረጉት። እነዚህ ተፈናቃይ አማራዎች ጥቅምት 24 ቀን 2014 ለዘመናት ከሚኖሩበት፣ሀብት ንብረት አፍርተው፣ ትዳር መስርተው ልጅ ወልደው፣ ድረው ኩለው ከሚኖሩበት ቀዬ ነው በአሸባሪው ኦነግ ሸኔ እና የዘር ማጥፋት ተባባሪዎቹ እንዲፈናቀሉ የተደረጉት። መጀመሪያ ላይ ጥቅምት 23 ቀን 2014 በአካባቢው የነበሩ ሁሉንም ሚሊሾች ተከባችኋል፤ ምንም ስለማናደርጋችሁ ትጥቅ አስረክቡ በማለት ትጥቅ ባስፈቱ በማግስቱ ነው ወደ ጭፍጨፋው የገቡት ይላሉ ነዋሪዎቹ። ጥቃቱ የተፈጸመውም በስቡስሬ እና ጎቡሰዮ ወረዳዎች በተለይም አጎላፍቴ እና ቡጅራ ቀበሌዎች ሲሆን በርካቶች በግፍ ተገድለዋል፤ በየጫካው የተበተኑትም ብዙዎች ናቸው፤ ሽህዎችም ተፈናቅለዋል። 72 ሆነው ከመጡት በወረዳ 15 የመስተዳድር አካላት ግፊት ከወጣቶች ማዕከል ደጋፊ ወጣቶችና የአካባቢው ማህበረሰብ ደከመን ሳይሉ በኃይል እንዲወጡ መደረጉ ተገልጧል። ይህ አካሄድም በርካታ የአስኮ አካባቢ ነዋሪዎችንና ወጣቶችን ያስቆጣ መሆኑን ለአሚማ ከቀረበው ቅሬታ ለነረዳት ተችሏል። “ስለምን ከማዕከል አስወጣችኋቸው? ችግር ቢደርስባቸው ማን ሊጠየቅ ነው?” በሚል ለተነሳባቸው ቅሬታ የወረዳ 15 ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ዘውድነሽ ከክፍለ ከተማው አስወጭ ተብዬ ነው፤ ከዚህ በላይ ለመርዳት ባለመቻሌ ነው ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። አሁን ላይ አስኮ ዙሪያ በሜዳ ከሚገኙት መካከል ከፊሎቹ የሚያስጠጋ ዘመድ እና ስራ ፍለጋ የሄዱ ሲሆን 47 የሚሆኑት ግን አብዛኞቹ ወላድ እናቶች እና ህጻናት በመሆናቸው መሄጃ አጥተው የወገንን እርዳታ በመጠባበቅ ላይ እንደሚገኙ ነግረውናል። አማራ ሚዲያ ማዕከል አሚማ ከተጎጅዎች መካከል: _ 1) የ2ኛ ዓመት የዩኒቨርስቲ ተማሪ እና ባለ 6 ቤተሰብ ከሆነው ከተማሪ ተመስገን ክብሩ፣ 2) 7 ቤተሰብ ካላቸው ከወ/ሮ በለጠች ገደፋውና 3) 8 ቤተሰብ ካላቸው ከወ/ሮ ጸጋነሽ ሺመልስ ጋር ያደረገውን ቆይታ ወደ አድማጭ ተመልካቾች የሚያደርስ ይሆናል። ሜዳ ላይ ለወደቁት 47 ከሞት የተረፉ ተፈናቃይ አማራዎች አስቸኳይ ወገናዊ እርዳታ ለመስጠት ለምትፈልጉ ይህን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት መጠቀም ትችላላችሁ:_ 1000297015908 ተመስገን ክብረቱ፣ ስልክ_090167472 0924870801 ታደሰ ተፈራ፣

Source: Link to the Post

Leave a Reply