ከምስራቅ ጎጃም ዞን ጉዞ የተወጣጡ 39 የፖሊስ አባላትና አመራሮች ከትሕነግ ነጻ ወደወጡት ወልቃይት ጠገዴ ዳንሻ እና ሁመራ ለሁለተኛ ዙር ስምሪት አደረጉ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ…

ከምስራቅ ጎጃም ዞን ጉዞ የተወጣጡ 39 የፖሊስ አባላትና አመራሮች ከትሕነግ ነጻ ወደወጡት ወልቃይት ጠገዴ ዳንሻ እና ሁመራ ለሁለተኛ ዙር ስምሪት አደረጉ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 25 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በምስራቅ ጎጃም ዞን ፖሊስ መምሪያ ስር ከሚገኙ ሁሉም ወረዳወዎች የተውጣጡ ሶስት አመራሮችን ጨምሮ 39 የፖሊስ አባላት በሁለተኛው ዙር ከትሕነግ የጭቆና አገዛዝ ነጻ የወጡ አካባቢወችን ለማረጋጋት ወደ ወልቃይት ጠገዴ ዳንሻ እና ሁመራ ጉዞ አድርገዋል። በሽኝት ኘሮግራሙ ላይ ተገኝተው ኦረንቴሽን የሰጡት የዞኑ እቅድ ዝግጅት ዋና ክፍል ሀላፊ ኮማንደር ልንገረው በዛ አባላቱ በራሳቸው ፈቃደኝነት የሚሰጣቸውን ማንኛውንም ግዳጅ ለመወጣት ዝግጁ ሆነው መምጣታቸውን ገልፀዋል። ለዚህም በዞኑ ፖሊስ መምሪያ ስም አመስግው በተሰማራችሁበት ቦታ ሁሉ የሚሰጣችሁን ተግባር በጥንቃቄና በጥሩ ስነ ምግባር ተወጣችሁ ዞናችንን እንድታስመሰግኑና ግዴታችሁን በድል አጠናቃችሁ በሰላም እንድትመለሱ እንመኛለን ብለዋል። በስራ ምክንያት በአሸኛኘቱ ላይ ያልተገኙት የዞኑ ፖሊስ መምሪያ ሀላፊ ም/ኮማንደር አያልነህ ተስፋየም በተወካያቸው አማካኝነት ባስተላለፉት መልክት ለግዳጅ የተሰማሩ አባላት ጉዞአቸው የተሳካ እንዲሆንና በድል እንዲመለሱ ተመኝተው የዞኑ አመራርም በማንኛውም ችግር ከጎናቸው እንደሆነና በተቻለ መጠን ከቦታው ድረስ ሄዶ በተሰማሩበት ቦታ ለመጎብኘትም ሁኔታወችን እንደሚያመቻች መልክት አስተላልፈዋል። ዘገባው የምስራቅ ጎጃም ፖሊስ ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply