You are currently viewing “ከምንም በፊት ሕዝብ ይቀድማል!”  አቶ ክርስቲያን ታደለ የአብን የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ታህሳስ 30 ቀን 2013 ዓ.ም         አዲስ አበባ ሸዋ የአማራ…

“ከምንም በፊት ሕዝብ ይቀድማል!” አቶ ክርስቲያን ታደለ የአብን የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ታህሳስ 30 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የአማራ…

“ከምንም በፊት ሕዝብ ይቀድማል!” አቶ ክርስቲያን ታደለ የአብን የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ታህሳስ 30 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ የአብን የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ክርስቲያን ታደለ መተከልን በተመለከተ የሚከተለውን በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጻቸው የሚከተለውን አጋርተዋል;_ በ1999 ዓ/ም የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ ውጤት መሰረት የ«ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል» ካለው 1,127,000 ሕዝብ ውስጥ የአማራ (እጣፈንታቸው ከአማራ ሕዝብ ጋር የሆኑትን ጨምሮ) ሕዝብ ድርሻ 60.59% ይደርሳል። በዚህ ስሌት መሰረት አማራው 47.88% የሚሆነውን የክልሉን ሕዝብ ሲሸፍን አገው 8.23% እንዲሁም ሽናሻ 4.58% ይሸፍናሉ። አብላጫ ቁጥር ያለው የአማራ ሕዝብ ቢሆንም በክልሉ በየደረጃው ባሉ የአስተዳደር እርከኖች ውክልና እንዳይኖረው መዋቅራዊና ሕጋዊ መገለሎች እየደረሱበት ይገኛል። ይህ አልበቃ ብሎ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተስፋፊ ፋሽስቶች ከአማራ የነፃ ምድር የመፍጠር የዘር ፍጅት ፕሮጀክት ገፋፊነት የጎጃም ክፍለሀገር አካል በነበረው መተከል ዞን ከ173,000 በላይ ወገኖች ማንነትን መሰረት ያደረገ ማፈናቀል ሲፈፀምባቸው በርካቶችም እጅግ ሰቅጣጭ የሆነ የዘር ፍጅት ተፈፅሞባቸዋል። በዚህ የዘር ፍጅት በጎጃም ክፍለሀገር ሥር የቀደመ ግዛታዊ አንድነት የነበራቸው፣ እጣፈንታቸውና ማኅበራዊ ስነልቦናቸውም የማይነጣጠሉ አማራ፣ አገውና ሽናሻ ዋነኛ የጥቃት ሰለባዎች የነበሩ ሲሆን ከአማራው ጋር መልካም ግንኙነትና ትብብር አላችሁ የተባሉ ንፁኃን የኦሮሞ ወገኖችም ተጎድተዋል። የፌዴራል መንግስት ተቋም የሆነው የማዕከላዊ ስታስቲክስ ባለሥልጣን ያወጣውን መረጃ ይዘን ብንከራከር እንኳን (የሕዝብ ቆጠራው በአማራው ላይ የሰራውን አሃዛዊ ዘርፍጅት ልብ ይሏል! )፣ አማራውን በሚጎዳ መልኩ በተዘጋጀው የሟች ትሕነግ ሰነድ በሆነው «ሕገመንግስት» መሰረት እንኳን፤ ሕዝብን ማዕከል ባደረገና የሕዝብን ፍላጎት መሰረት አድርገን ዘላቂ እልባት ይሰጠው ቢባል እንኳን፤…መተከል የግዮን መውጫ በር የጎጃም ግዛት አካል ነው። ከዘፍጥረት ጀምሮ አንድ የነበርን ሕዝብ በፖለቲካ መነጣጠል መቼውንም ልክ ሊሆን አይችልም። ከኢትዮጵያ መስራች አባት ንጉስ ኢትኤል ጀምሮ አንድ የነበረ ሕዝብ፥ ይኸው ተፈጥሯዊ አንድነቱ ሊቀጥል ይገባል ማለትም እንደግዛት መስፋፋት እና መሬት ፍለጋ ተደርጎ መሳል አይኖርበትም። ከምንም በፊት ሕዝብ ይቀድማል! መተከል፥ ጎጃም ፥ ግዮን ምድር!

Source: Link to the Post

Leave a Reply