ከምዕራብ ወለጋ ጉሊሶ ወረዳ ጋዋ ቋንቋ ሰቀጀርቢ ቀበሌ የተፈናቀሉ ወገኖች አስፈላጊውን በቂ ድጋፍ እንዲደረግልን እንፈልጋለን ሲሉ በምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ ዳስ-ጉንዶ የሰፈሩ ወገኖ…

ከምዕራብ ወለጋ ጉሊሶ ወረዳ ጋዋ ቋንቋ ሰቀጀርቢ ቀበሌ የተፈናቀሉ ወገኖች አስፈላጊውን በቂ ድጋፍ እንዲደረግልን እንፈልጋለን ሲሉ በምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ ዳስ-ጉንዶ የሰፈሩ ወገኖች ገለጹ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 30 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የአማራ ክልል ሴቶች ህፃናት ቢሮ ከዩኒሴፉ ጋር በመተባበር ከምዕራብ ወለጋ ወሊሶ ወረዳ ጋዋ ቋንቋ ሰቀጀርቢ ቀበሌ በማንነታቸው ተፈናቅለው ለመጡ ወገኖች በምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ ዳስጉ-ንዶ ቀበሌ በመገኘት ድጋፍ አድርጓል። የአማራ ክልል ሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ቢሮ የዩኒሴፍ አስተባባሪ አቶ በረከት ዩሃንስ በቂ ባይሆንም ለጊዜው ማረፊያ የሚሆን ድንኳንና ለሴቶች የንፅህና መጠበቂያ የሚሆን ቁሳቁስ ድጋፉ አድርገናል በቀጣይ ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር በመቀናጀት እገዛ እንድደረግላቸው ጥረት እናደርጋለን ብለዋል። የመተማ ወረዳ ሴቶች ህፃናት ወጣቶች ከምዕራብ ጎንደር ዞን ሴቶች ህፃናት እና ወጣቶች መምሪያ ጋር መረጃወችን በማደራጀት በጋራ በመተባበር ድጋፍ እንዲደረግ ጥረት ማድረጋቸውን የመተማ ወረዳ ሴቶች ህፃናት ወጣቶች ጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ኤደን ምንውየለት ገልጸዋል። የምዕራብ ጎንደር ሴቶች ህፃናት ወጣቶች ተወካይ ሃላፊ አቶ አበበ ሲሳይ ከዚህ በፊት ከተለያዩ አጋር አካላት የምግብ አቅርቦትና ሌሎች ቁሳቁሶች ድጋፍ ቢደረግም ችግሩን የከፋ ያደረገው ሴቶችና ህፃናት መኖራቸው ነው ብለዋል። አቶ አበበ አክለውም የሚመለከታቸው አካላት ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩ እና ዘላቂ የሆነ መፍትሄ እንዲሰጥ ቢደረግ የተሻለ ነው ሲሉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል። የተፈናቀሉ ወገኖች እንዳሉት የተደረገው ጭፍጨፋ ዘግናኝ በመሆኑ ወደቦታችን ለመመለስ ሞራልና ፍላጎት የለንም። ስለሆነም መንግስት በቋሚነት በክልላችን ሆነን ህይወታችን እንድመራ እንዲያደርግልን እንጠይቃለን ብለዋል። ተፈናቃዮችም 131 አባውራ አጠቃላይ በቤተሰብ ደግሞ 227 ሲሆኑ 96ቱ ህጻናት ናቸው። እየተደረገላቸዉ ላለዉ ድጋፍ አመስግነዉ በቀጣይ መንግስት በዘላቂነት መፍትሄ እንዲሰጠን ሲሉ የተፈናቀሉ ወገኖች ጠይቀዋል ሲል የመተማ ወረዳ ኮሚኒኬሽን ዘግቧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply