ከምዕራብ ወለጋ ጥቃት የተረፉ አሁንም ሥጋት ውስጥ መሆናቸውን ገለፁ

https://gdb.voanews.com/E2EAA9B5-5E77-4C85-9049-05638122D03D_w800_h450.jpg

በኦሮምያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ ወረዳ የተፈጸመውን ጥቃት ተከትሎ የተፈናቀሉ ተጎጂዎች አሁንም ለደህንነታቸው እንደሚሰጉ እና በመንግሥት የሚወሰደው እርምጃ አጥጋቢ እንዳልሆነ ገለፁ።

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትሩ ዶ/ር ለገሰ ቱሉ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት አስተያየት የቅዳሜውን የጊምቢ ወረዳ ጥቃት ጨምሮ ሰሞኑን የተፈጸሙ ጥቃቶች መንግሥት “ሸኔ” በሚለው እና እራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ብሎ በሚጠራው ቡድን መፈጸማቸውን ገልጸው፣ ጥቃቱ በተፈጸመበት ሥፍራ በቡድኑ ላይ ጠንካራ እርምጃ እየተወሰደ ነው ብለዋል፡፡

የሰራዊቱ ቃል አቀባይ ግን ጥቃቱ የተፈጸመው በራሱ በመንግሥት ሚሊሺያዎች መሆኑንና ገለልተኛ ምርመራ እንዲካሄድ ጠይቀዋል።

ኦነግ እና ኦፌኮ ዛሬ ባወጧቸው መግለጫዎች ጥቃቱን በተመለከተ በገለልተኛ አካል ምርመራ እንዲካሔድ ጠይቀዋል፡፡ ዩናይትድ ስቴትስ በንጹኃን ላይ የተፈጸመው የጅምላ ግድያ በጽኑ እንዳሳሰባት አስታውቃለች፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡት።

 

Source: Link to the Post

Leave a Reply