
ከሰሜን ወሎ በህወሃት ኃይሎች የተወሰዱ ከ460 በላይ ነዋሪዎች የት እንዳሉ አይታወቅም ተባለ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 27 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በፌደራል መንግስትና በህውሃት ሃይሎች ተቀስቅሶ በነበረው የሰሜኑ ጦርነት የአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ሙሉ ለሙሉ በትግራይ ክልል ሃይሎች በቁጥጥር ስር ውሎ በነበረት ወቅት በተለይም የህውሃት ሃይሎች ወልዲያንና አካባቢዋን ሲቆጣጠሩ የጦር መሳሪያ ይዘው የተገኙ የቀድሞው ሰራዊት አባል ወይም ሚሊሻ ናችሁ በሚል ጥቅምት 23 ቀን 2014 ዓ.ም በርካታ ሰዎችን ወደ መቀሌ እየጫኑ እንደወሰዷቸው የጥቃቱ ሰለባ ቤተሰቦች አስረድተዋል። በሰሜን ወሎ ዞን ጉባ ላፍቶ ወረዳ ደቦት እና በቅሎ ማነቂያ ተብሎ በሚጠራ ስፍራ አዲስ ዘይቤ በተገኘበት ወቅት በህወሃት ሃይሎች አባቶቻቸው የተወሰዱባቸውን ልጆች እንዳሉ አተጋግጧል። አቶ ስለሺ ተስፋ በሰሜን ወሎ ዞን ጉባ ላፍቶ ወረዳ ደቦት ቀበሌ ነዋሪ ሲሆን ጥቅምት 23 ቀን 2014 ዓ.ም አባቱ፣ አጎቱና ሌሎች ሶስት ጎረቤቶቹ በህወሃት ሃይሎች ተወስደውበታል። አባቱ አቶ ተስፋ ቢክስ እና አጎቱ አቶ አረጋ ቢክስ በደቦት ቀበሌ አርሶ አደሮች ሲሆኑ ቤታቸው ሲፈተሽ የግል መሳሪያ ስለተገኘባቸው የቀድሞው ሰራዊት አባላት (ሚሊሻ) በመሆናችሁ ለፌደራል መንግስት መረጃ ታቀብላላችሁ ተብለው እንደተወሰዱ አቶ ስለሺ ተስፋ ይናገራል ሲል ያጋራው አዲስ ዘይቤ ነው።
Source: Link to the Post