ከሰሜን ዕዝ ታግተው የነበሩ የመከላከያ አባላት ተከዜ መገኘታቸው ታወቀ           አሻራ ሚዲያ        ህዳር 19/2013 ዓም ባህር ዳር በህወሃት ከሰሜ…

ከሰሜን ዕዝ ታግተው የነበሩ የመከላከያ አባላት ተከዜ መገኘታቸው ታወቀ አሻራ ሚዲያ ህዳር 19/2013 ዓም ባህር ዳር በህወሃት ከሰሜ…

ከሰሜን ዕዝ ታግተው የነበሩ የመከላከያ አባላት ተከዜ መገኘታቸው ታወቀ አሻራ ሚዲያ ህዳር 19/2013 ዓም ባህር ዳር በህወሃት ከሰሜን ዕዝ ታግተው የነበሩ አራት ሺህ ያህል የሰራዊቱ አባላት ትላንት ምሽት ተከዜ ላይ አምጥተው ጥለዋቸው መመለሳቸው የታወቀ ሲሆን እነዚህ በተከዜ በኩል የተገኙት ወታደሮች ሁሉም ማዕረግ የሌላቸውና ከአማራ ብሔር ውጭ ያሉ መሆናቸው ታውቋል። ህወሃቶች በተንቤን በኩል ነው አምጥተው የጣሏቸው እነዚህ የመከላከያ ሰራዊት አባላት በእግራቸው ተጉዘው ሰሜን ጎንደር ዞን በየዳ ደርሰዋል። የአማራ ተወላጆችንና ሌሎች ማዕረግ ያላቸው ወታደሮች የት እንዳሉ እስካሁንም አይታወቅም። ዘጋቢ፡- ማርሸት ጽሀው

Source: Link to the Post

Leave a Reply