You are currently viewing ከሰሞኑ በባህርዳር እና አንዳንድ የአማራ ክልል አካባቢዎች የተጀመረውን መንግስታዊ አፈና እና አፈሳ አስመልክቶ የአማራ ወጣቶች በባህርዳር የሚከተለውን መግለጫ አውጥቷል። የአማራ ተማሪዎች ማህ…

ከሰሞኑ በባህርዳር እና አንዳንድ የአማራ ክልል አካባቢዎች የተጀመረውን መንግስታዊ አፈና እና አፈሳ አስመልክቶ የአማራ ወጣቶች በባህርዳር የሚከተለውን መግለጫ አውጥቷል። የአማራ ተማሪዎች ማህ…

ከሰሞኑ በባህርዳር እና አንዳንድ የአማራ ክልል አካባቢዎች የተጀመረውን መንግስታዊ አፈና እና አፈሳ አስመልክቶ የአማራ ወጣቶች በባህርዳር የሚከተለውን መግለጫ አውጥቷል። የአማራ ተማሪዎች ማህበር ፕሬዘዳንት እሸቱ ጌትነት ላይ በተደረገው መንግስታዊ አፈና በፅኑ እናወግዛለን ‼️ ታሕሳስ 12 ቀን 2015 ዓ.ም… አሻራ ሚዲያ ፣ የአማራ ተማሪዎች ማህበር ከተመሰረተ ጊዜ ጀምሮ በርካታ አበረታችና ጉልህ ስራዎችን ሰርቷል ።ከእነዚህም መካከል ፦ 1).አስራ ሰባት (17) የአማራ ተማሪዎች በደምቢዶሎ ዩኒቨርስቲ መንግስታዊ ድጋፍ ባለው ሀይል ታግተው ደብዛቸው ሲጠፋ[[ እስካሁንም ለተማሪ ቤተሰቦች ፥ለመላው የአማራ ህዝብ ያልተረዳ መርዶ ነው]] ከአማራ ወጣቶች ማህበር ጋር በመተባበር መላው አማራ ህዝብ ቁጣው ፤ሰላማዊ ተቃውሞውን በአደባባይ እንዲገልፅ አድርጓል ።በተመሳሳይ ከሰሞኑ የአማራ ተማሪዎች መታገታቸው የሚታወስ ነው ። 2).የአማራ ተማሪዎች የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና ላይ መንግስታዊ እና ስርዐታዊ የውጤት ማሳጣት ፣ማጭበርበር ሲደርስባቸው በተመሳሳይ ከአማራ ወጣቶች ማህበር ጋር በመተባበር ውጤታቸው ዳግም እንዲታይ እንዲሁም በጦርነት ውስጥ የነበሩ የአማራ ተማሪዎች ከሌሎች የአገሪቱ አካባቢዎች በተመሳሳይ ሊፈተኑ አይገባም በማለት በአደባባይ ድምፃችን ያሰማን [[በዚህም ጥያቄው በተወሰነ መልኩ መልስ አግኝቶ በጦርነት አካባቢ ሆነው የተፈተኑ የአማራ ተማሪዎች ድጋሚ የመፈተን ዕድል እንዲያገኙ ተደርጓል ]] ፤በተጨማሪም እነዚህ ተማሪዎች በውጭ አገር ከሚገኙ የአማራ ማህበራት ጋር በመተባበር የማጠናከሪያ ፣የማካካሻ ትምርህት እንዲያገኙ ያደረገ የአማራ ተቋም ነው ። 3).የህውሓት ወራሪ ሀይል የአማራን ህዝብ አንገት ለማስደፋት ፣ለማዋረድ ባደረገው ወረራ በርካታ የአማራ ልዩ ሀይል ፣የአማራ ሚኒሻ እና ነበልባሉ የአማራ ፋኖ አኩሪ ጀብድ ፈፅመዋል ።በዚህ ታሪካዊ የጀግነትና አማራዊ ገድል ለተሰው የአማራ ፋኖ ፣የአማራ ሚኒሻ ቤተሰቦች ፤ያለ አሳዳጊ ለቀሩ እንቦቀቅላ ልጆች በውጭ አገር ከሚገኙ የአማራ ተቆርቋሪ ማህበራት ጋር በመተባበር የከበረ መስዕዋትነት ለከፈሉ የአርበኛ ሚስቶች ድጋፍ እንዲያገኙ ፣የጀግና ልጆች ደግሞ በዘላቂነት ድጋፍ አግኘተው እንዲያድጉ የሚያስችል ፕሮጀክቶችን ቀርፆ [መንግስት ተብዬው መስራት ሲገባው ፤ሀላፊነቱ የመንግሰት ቢሆንም መንግሰት ያልሰራውን የሰራ ]] የአዲሱ አማራ ትውልድ ተቋም ነው ። ከላይ በጥቂቱ የተጠቀሱ የአማራ ተማሪዎች ማህበር በንፁህ አእምሯቸው ፣በአፍላና የልጅነት ጉልበታቸው መማር ማጥናት ሲገባቸው የአማራ ህዝብ የገጠመውን የህልውና አደጋ ፤በአማራ ተማሪዎች ላይ አየደረሰ ባለው መዋቅራዊ ፣ ስርዓታዊ እና ምሁራዊ የዘር ፍጅት( intellectual genocide) ለመከላከል የሚችለው እያደረገ ያለ ፣ ያደረገ በወጣት አእምሯቸው መማር ሲገባቸው የአማራን ህዝብ እወክላለሁ የሚለው ብአዴን (አማራ ብልፅግና) መስራት ያልቻለውን ሃላፊነት እየተወጣ የሚገኝ አዲሱ አማራ ትውልዱ አንዱ ተቋም ነው ።ነገር ግን ይሉኝታ የሌላቸው ፣አድርባዮች ፣ዘላለም አሽከርነት የማይሰለቻቸው ጉዶች እና የአማራ ህዝብ መዥገሮች ከላይ በጥቂቱ የተጠቀሱ ህዝባዊ ስራዎች ከሚሰሩ ተቋማት አንዱ የሆነው የአማራ ተማሪዎች ማህበር ፕሬዝዳንት እሸቱ ጌትነትን ከጓደኛው መታገስ ፀጋ ጋር አፍኖ ከሰወራቸው ቀናቶች ተቆጥረዋል ። የአማራ ወጣቶች ማህበርም በአማራ ተማሪዎች ማህበር ፕሬዝዳንት እሸቱ ጌትነት በደረሰው መንግስታዊ አፋና በፅኑ እያወገዝን ከሰሞኑ ለአማራ ህዝብ ህልውና በመታገል ላይ ያሉ የነቁ አማራዎችን ማፈን ፣ማሳደድ እና ጅምላ እሰር በአስቸኳይ እንዲቆም ጥሪያችን እናስተላልፋለን ። በማሰር የሚቆም ፣የተጀመረ የአማራ ትግል ፈፅሞ የለም ።የትግላችን መዳረሻ የአማራ ህዝብ ነፃነት ነው ። የአማራ ወጣቶች ማህበር ታህሳስ 12/2015 ዓ.ም አማራ በቆራጥ ልጆቹ ተጋድሎ ታሪኩን ያድሳል‼️ “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply