ከሰሞኑ በአዲስ አበባ በተለያዩ ቦታዎች በመሳርያ የተቀነባበሩ ጥቃቶች እየደረሱ ነው፡፡ከሰሞኑ በመዲናዋ በሁለት ቦታዎች በመሳርያ የተቀነባበረ ጥቃት መድረሱን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮምሽን አስ…

ከሰሞኑ በአዲስ አበባ በተለያዩ ቦታዎች በመሳርያ የተቀነባበሩ ጥቃቶች እየደረሱ ነው፡፡

ከሰሞኑ በመዲናዋ በሁለት ቦታዎች በመሳርያ የተቀነባበረ ጥቃት መድረሱን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮምሽን አስታውቋል፡፡

ቅዳሜ እለት በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 15 በተለምዶ አያት አደባባይ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሶስት ጓደኛሞች መካከል በተፈጠረው ግጭት በአንደኛው ግለሰብ ላይ ከፍተኛ የአካል ጉዳት እንደደረሰበት ኮሚሽኑ ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታውቋል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የኮሚኒኬሽን ዳሬክተር ኮማንደር ፋሲካው ፋንታ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት በእለቱ ሶስቱ ጓደኛሞች በጊዜያዊ ግጭት ባለመግባባታቸው ምክንያት በተፈጠረው ግጭት በአንደኛ ጓደኛቸው ላይ የአካል ጉዳት አድረሰዋል ብለውናል፡፡

ተጎጂው ግለሰብ ሁለት ቦታ ላይ በሽጉጥ እንደተመታ የተናገሩት ኮማንደር ፋሲካው አሁን ህክምና እየተደረገለት ይገኛል ብለዋል፡፡

ፖሊስ ጥቃቱን ያደረሱት ግለሰቦች ተከታትሎ ለመያዝ ባደረገው ጥረት አንደኛው ግለሰብ የተያዘ ሲሆን አንደኛው ለጊዜው አለመያዙን ነው ኮማንደር የተናገሩት፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከሰሞኑ የፌደራል ፖሊስ ባልደረባ በአንድ የመዝናኛ ቦታ ላይ በከፈተው ተኩስ የአንድ ግለሰብ ህይወቷ ሲያልፍ ዘጠኝ ሰዎች ላይ ደግሞ ጉዳት ማድረሱን ነው የተነገረው፡፡

ጥቃቱ የደረሰው በየካ ክፍለ ከተማ ኮተቤ ብረታ ብረት ሲቭል ሰርቪስ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው፡፡

በጥቃቱ አንድ ወጣት ሴት ስትሞት ሌሎች ዘጠኝ ያህል ዜጎች ደግሞ ከፍተኛ የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው ተገልጿል፡፡

ሔኖክ ወ/ገብርኤል
ጥቅምት 15 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply