
በቅርቡ የሸገር ከተማ ተብሎ በተዋቀሩት በአዲስ አበባ ዙሪያ በሚገኙት የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች ሕገወጥ ናቸው በሚል በርካታ መኖሪያ ቤቶች እየፈረሱ ነው። በአካባቢው አስተዳደሮች እና በፀጥታ ኃይሎች ድጋፍ በሚካሄደው ቤቶችን የማፍረስ ዘመቻ በርካታ ቁጥር ያቸው ነዋሪዎች በድንገት ያለቤት መቅረታቸውን ይናገራሉ። ነዋሪዎች ያለምንም ማስጠንቀቂያና አማራጭ ለዓመታት የኖርንበት ቤት ፈርሶ ሜዳ ላይ እንድንወድቅ ተደርገናል ይላሉ።
Source: Link to the Post