ከሰሞኑ ወለጋ ውስጥ በሚኖሩ የአማራ ተወላጆች ላይ በኦሮሚያ ነፃነት ሰራዊት መጠነ ሰፊ ጭፍጨፋ መፈፀሙ ተገለፀ! ጳጉሜ 01/2014 ዓ.ም (አሻራ ሚዲያ) ከነሐሴ 28/2014 ዓ.ም ጀምሮ…

ከሰሞኑ ወለጋ ውስጥ በሚኖሩ የአማራ ተወላጆች ላይ በኦሮሚያ ነፃነት ሰራዊት መጠነ ሰፊ ጭፍጨፋ መፈፀሙ ተገለፀ! ጳጉሜ 01/2014 ዓ.ም (አሻራ ሚዲያ) ከነሐሴ 28/2014 ዓ.ም ጀምሮ ወለጋ ውስጥ በሚኖሩ የአማራ ተወላጆች ላይ በሚዲያ ጭምር የታገዘ መጠነ ሰፊ ዘር ተኮር ጭፍጨፋ መፈፀሙን የአይን እማኞች ተናግረዋል። በአማራ ተወላጆች ሞት፣ መፈናቀል እና መገላታት የእለት ጉርሳቸውን የሚሞሉት የ”OMN” እና ኩሽ ሚዲያዎች በሰሞኑ ጭፍጨፋ የጥላቻ መልዕክት በማስተላለፍ ተከታዮቻቸውን በማነሳሳት ጥቃቱ እንዲፈፀም አስተዋጽኦ አድርገዋል። በዚህም በርካታ የወለጋ አከባቢዎች በሰሜኑ የሐገራችን ጦርነት ምክንያት የመከላከያ ሰራዊት አከባቢዎቹን በመልቀቃቸው ምክንያት የኦሮሚያ ነፃነት ሰራዊት ያለማንም ከልካይ ንፁሐንን በመግደል፣ በማፈናቀልና ከግለሰብ… ንብረት ጀምሮ እስከ ትልልቅ የመንግስት ተቋማትን እስከ አሁኗ ሰዓት ድረስ ሟቾቹ የአማራ ተወላጆች ሆነው ሳለ ኦሮሞ ተጨፈጨፈ እያሉ በሐሰት እየከሰሱ ይገኛሉ ። አዲስ የጀመሩት የውሸት ፕሮፖጋንዳ ደግሞ ምንም የሌለበትን ፋኖ ንፁኃንን ጨፈጨፈ የሚል አዲስ ትርክት ይዘው መጠዋል። እውነታው ግን ፋኖ በሰሜኑ ጦርነት ከመከላከያ ጋር በመሆን ለሀገር ህልውና እየተዋደቀ ይገኛል። ስለሆነም የኦሮሚያ ነፃነት ሰራዊት የተለያዩ የወለጋ ዞኖችን፣ ወረዳዎችን፣ ቀበሌዎችን እና የከተማ መስተዳደሮችን በመቆጣጠሩ በአካባቢው ለሚኖሩ የአማራ ተወላጆች ከፍተኛ ስጋት ስለሆነባቸው ብዙወች ሀብት ንብረታቸውን በመተው ተፈናቅለዋል። አሁንም በሆሮጉድሩ ወለጋ ዞን በአሙሩ ወረዳ፣ በጃርቴ ጃርዴጋ ወረዳዎች ከ82 ንፁሃን ኗሪዎች በላይ ጥቃት መፈፀሙን ተረጋግጧል። በምስራቅ ወለጋ ዞን በጊዳ አያና ወረዳ፣ በሊሙ ወረዳ፣ በኪረሙ ወረዳ፣ በሐሮ ገሊላ፣ በጉቶ ጊዳ፣ በሲቡስሬ ወረዳ፣ በሳሲጋ ወረዳ፣ በአኖ ወረዳ፣ በድጋ ወረዳ በአርጆ ጉደቱና በዙሪያው ስር በሚገኙ በርካታ የአማራ ማህበረሰብ በሚኖሩበት አከባቢዎች ደግሞ ከ85 በላይ ንፁሐን አማራዎችን መጨፍጨፋውን ነዋሪዎች ተናግረዋል። በሰሞኑ በሆ/ጉ/ወ/ዞን በአሙሩ ወረዳ በአጋምሳ ቀበሌ በተፈጠረው የኦሮሚያ ነፃነት ሰራዊት ጥቃት በርካታ የአማራ ተወላጆች ላይና ከኦነግ የትግል አቅጣጫ አካሔድ ከጎኑ ሳይሰለፉ በቀሩ የኦሮሞ ተወላጆች ላይ ጭፍጨፋ ከፈጸመ በኋላ ልክ እንደ ነፃ ቡድን እራሱን በመቁጠር እራሱ ጨፍጭፎ እራሱ በወንድሞቻችን ሞት ላይ ሲሳለቅ ተስተውሏል ብለዋል። በአጋምሳ ቀበሌ ከወለጋ አከባቢዎች እንዲሁ በአማራ ተወላጆች ጥቃት የተመለከቱ የኦሮሞ ተወላጆች አማራን ከእሳት ቃጠሎና ከዘር ጨፍጨፋው በቤታቸው በመደበቅ ሲያተርፉ ተስተውሏል። በዚህም ከ50 በላይ ንፁሐን ተጨፍጭፈዋል። በዚህ ቀና አመለካከት የአማራ ወንድሞቻቸውን በማትረፍ በመሸሽ ላይ እያሉ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት በነዚህ ንፁሃን የኦሮሞ ተወላጆች ላይ የጥይት ናዳ አውዶባቸው ከአማራ ወንድሞቻቸው ጋር በአንድ ቦታ ገሏቸዋል።ስለሆነም በሐገራችን ዳግም በተቀሰቀሰው ጦርነት ከታሪካዊ ጠላቶቻችን ጋር በመሆን የሠላም በሩን ዘግቶ ለዳግም ጭፍጨፋ እየተዘጋጀ መሆኑን በወለጋ የሚኖሩ የአማራ ተወላጅ ኗሪዎች የሚመለከተው አካል እንዲደርስላቸው መንግሥትን ተማጽነዋል። በመጨረሻም በወለጋ በዚህ ሰዓት ከፍተኛ ስጋት ከገጠማቸው አከባቢዎች መካከል 👉 አንገር ጉትን ከተማና የዙሪያዋ አከባቢዎች 👉 የሐሮ አዲሳለም ከተማና የዙሪያዋ ህዝቦች 👉 የኡኬ ከተማና የዙሪያዋ ህዝቦች 👉 የአርጆ ጉደቱና የዙሪያዋ ህዝቦች 👉 የቱሉጋና ከተማና የዙሪያዋ ህዝቦች 👉 የአንዶዴ ከተማና የዙሪያዋ ህዝቦች 👉 በፊጢበቆ ቀበሌ ስር የሚገኙ መ.6,7,8,9 👉 በአርቁምቢ ቀበሌና በዙሪያው ያሉ አከባቢዎች 👉 በሐሮ ገሊላና በዙሪያው ያሉ ህዝቦች 👉 በጃቦዶበን ቀበሌና በእድገቴ ቀበሌ 👉 በጃርቴ ጃርዴጋና በቱሉ ዋዩ 👉 በሻምቦ ከተማና በዙሪያው 👉 በመንደር 10 ከተማና በአባሙሳ ቀበሌ 👉 በአሊና በዙሪያው 👉 በሲቡስሬ ወረዳና በአኖ ወረዳ 👉 በባኮ ትቤ ወረዳና በዙሪያው 👉 በቤኒሻንጉል ክልል በከማሽ ዞን በሶጌ ወረዳ እና በወለጋና በቤንሻንጉል ክልል በየአጎራባች በሚገኙ አማራ በብዛት በሚኖርባቸው አከባቢዎች ከሸኔ በተጨማሪ የህወሓት አባልና አመራር በነበሩ ፅንፈኛ ቡድኖችና በቤኒን ታጣቂዎች የጋራ የጥፋት ጥምረት ህዝባችን አደጋ ላይ ወድቋል። ስለሆነም በሐገራችን የምትገኙና በውጭ ሐገር የምትገኙ የሚዲያ አካላት እና የመንግስት አስተዳደር የሚመለከታችሁ ሁሉ፥ በእብሪት ሐገራችንን ለማፈራረስ በፎከው ልክ በድርድር መልክ ጊዜ እየገዛ በህዝቦች ላይ መጠነ ሰፊ ጭፍጨፋ በመፈጸም ላይ በመሆኑ ይህንን ፅንፈኛ ቡድንና ግብረአበሮቹን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የሚሰራውን ግፍና በደል በወለጋ በተለያዩ ጊዜያት ያለምንም ጥፋታቸው የታሠሩትን አማራወች በመፍታት፤ ያለአግባብ ትጥቃቸውን የፈቱትን በሙሉ ከእስር በመፍታት ትጥቃቸውን በመመለስና ያለምንም ፍትህ በየወረዳዎቹ ፖሊስ ጣቢያዎች የታሠሩትን የአማራ ተወላጆችን በመፍታት ለሐገራችን በአጠረ ጊዜ ውስጥ በተባበረ ክንድ ነፃ በማድረግ ምቹና የፈረሱትን የመንግስት መዋቅሮች ወደመደበኛ ስራቸው በመመለስ ጉልህ ሚና ስላላቸው መንግስት በአስቸኳይ መፈታቸው እንደሚገባ በወለጋ የሚኖሩ የማህበረሰብ ክፍሎች ለመንግሥት እና ለሚመለከታቸው የሚዲያ አካላት አድርሱልን ሲሉ ጠይቀዋል። በዛሬው ዕለትም በቡኖ በደሌ ዞን መኮ ወረዳ ኦነግ ጥቃት መክፈቱን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። መኮ ወረዳን ተቆጣጥረው ወደ ደጋው እየገሰገሱ ነው ብለዋል። ጉዳዩ አፋጣኝ መፍትሔ ይሻል ብለዋል። በወለጋ የአማራ ህዝብ ላይ ቀጣይ ጥቃት ለማድረስ ኦነግም ቅስቀሳ እያደረገ ነው ። ሌላው የኦነግ የጥፋት ቅስቀሳ ስንመለከት ደግሞ ግንባሩ ዛሬ ባወጣው መግለጫ አሁን በኦሮሞ ህዝብ ላይ ጥቃት እያደረሰ ያለው ፋኖ አስቀድመው በሰፈራ መልክ ኦሮሚያ ውስጥ የነበሩትን ከለላ በማድረግ ከአማራ ክልል መምጣቱን ገልጿል። ይህ በሰፈራ መልክ ኦሮሚያ ውስጥ በነበሩ ዜጎችና በመንግሥት ፀጥታ መዋቅር የሚደገፈው ቡድን ሰሞኑን በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን አገምሳ ከተማን በመውረር በፈፀመው ጥቃት ከ65 በላይ ዜጎች መገደላቸውን ተናግሯል። የኦሮሞን ህዝብ ከመሬቱ ለማፈናቀል የተቀናጀ እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን ጠቅሶ፣ በኦሮሞ ህዝብ ላይ ጭፍጨፋ ሲፈፀመ መንግሥት በዝምታ አለፈ ሲል ይከሳል። ዋናው ዓላማቸው ተጎጂ አማራው ሆኖ እያለ የእነሱን ልሳኖች በመጠቀም የተቀዳይን ጩኸት በመቀማት አዲስ የጭፍጨፋ ስልት እየተጠቀሙ መሆኑን የመረጃ ምንጮቻችን ገልፀውልናል። ትኩረት በወለጋ ለሚኖሩ የአማራ ተወላጆች!! ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply