ከሱዳን የተነሱ የሕወሓት ታጣቂዎች ከሰሞኑ በወልቃይት በኩል ትንኮሳ መፈጸማቸው ተሰማ! ታሕሳስ 21 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ከሱዳን የተነሱ የሕወሓት ታጣቂዎች ከሰሞኑ በወልቃይት…

ከሱዳን የተነሱ የሕወሓት ታጣቂዎች ከሰሞኑ በወልቃይት በኩል ትንኮሳ መፈጸማቸው ተሰማ! ታሕሳስ 21 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ከሱዳን የተነሱ የሕወሓት ታጣቂዎች ከሰሞኑ በወልቃይት አስተዳደር ሉግዲ በተባለ ስፍራ ትንከሳ መፈፀማቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለአማራ ድምጽ ገልጸዋል። የአማራ ድምጽ ያነጋገራቸው የሉግዲ ከተማ ነዋሪዎች እንዳሉት፣ ታህሳስ 18 ቀን 2015 ዓ.ም ከሱዳን የተነሱ የሕወሓት ታጣቂዎች ከሱዳን ወታደሮች ጋር በመሆን ትንኮሳ ፈጽመዋል ብለዋል። በትንኮሳው የጎላ ጉዳት እንዳልደረሰ የተናገሩት ነዋሪዎቹ፤ የመከላከያ ሠራዊት እና የአካባቢው ሚሊሻዎች ትንኮሳውን ለመመከት መቻላቸውን ገልጸዋል። የወልቃይት አስተዳዳሪ አቶ ክብረአብ ስማቸው ከሰሞኑ አንከር ቲቪ ከተባለ የበይነ መረብ ሚዲያ ጋር ባደረጉት ቆይታ ሕወሓት በወልቃይት በኩል ትንኮሳ እየፈፀመ እንደሚገኝ ገልጸው ነበር። አስተዳዳሪው በቆይታቸው፣ በፌደራሉ መንግሥት በኩል ወለቃይትን በተመለከተ የተያዘው አቋም ግልጽ አይደለም፡ በዚህም ስጋት ገብቶናል ማለታቸው ይታወሳል። በ ዘረባቤል አለምአየሁ ዘገባው የአማራ ድምፅ ነው ። “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply