ከስምንት ዓመት በኋላ ቻይና የአሜሪካን ልዕለ ሀያልነት እንደምትነጥቅ  የአውሮፓውያን ጥናት አመለከተ፡፡ ( አሻራ ታህሳስ 18፣ 2013 ዓ.ም) ከዓለም ጠቅላላ ህዝብ 22 ከመቶውን የያዘችው…

ከስምንት ዓመት በኋላ ቻይና የአሜሪካን ልዕለ ሀያልነት እንደምትነጥቅ የአውሮፓውያን ጥናት አመለከተ፡፡ ( አሻራ ታህሳስ 18፣ 2013 ዓ.ም) ከዓለም ጠቅላላ ህዝብ 22 ከመቶውን የያዘችው…

ከስምንት ዓመት በኋላ ቻይና የአሜሪካን ልዕለ ሀያልነት እንደምትነጥቅ የአውሮፓውያን ጥናት አመለከተ፡፡ ( አሻራ ታህሳስ 18፣ 2013 ዓ.ም) ከዓለም ጠቅላላ ህዝብ 22 ከመቶውን የያዘችው ቻይና አሜሪካን በኢኮኖሚ እንደምትቀድም ከወዲሁ ተገምቷል፡፡ ዓለም አሁን ላይ በኮሮና ወረራ ውስጥ እያለችም እንኳ ቻይና ፈጣን እና ተከታይነት ያለው ለውጥ እያስመዘገበች እንደሆነ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡ መሰረቱን እንግሊዝ ያደረገ ታዋቂ የጥናት ተቋም እንዳረጋገጠው በ2028 እኤአ አሜሪካ ሙሉ በሙሉ ልዕለ ሀይልነቷን ለቻይና ትሰጣለች፡፡ አሜሪካ ልዕለ ሀይልነቷን ከእንግሊዝ ከ1945 እኤአ ተቀብላ ለአንድ ክፍለዘመን አስቀጥላ ነበር፡፡… ነገር ግን አሜሪካ በሳይንስ፣ በኢኮኖሚ እና በቴክኖሎጂ እየደገመች ቻይና በፍጥነት እየተምዘገዘገች ነው፡፡ ኮሮና ቫይረስ በቻይና ቢገኝም በቻይና በኮሮና የተያዘው የህዝብ ቁጥር ከኢትዮጵያ ያንሳል፡፡ አሜሪካ በኮሮና ክፉኛ የጤና ተቋሟ እና ኢኮኖሚዋ ሲደቅ ቻይና በኮሮና ሰበብ ልዕለ ሀያል ሆናለች፡፡ እንዳውም አሜሪካውያን ኮሮና በቻይና የተሰራ ቫይረስ ነው ሲሉ ይከሳሉ፡፡ ኮሮናን አሜሪካ በዶናልድ ትራንፕ በኩል የቻይና ቫይረስ ተብሎ የተሰየመ ሲሆን፣ የዓለም የጤና ድርጅት ግን ኮቪድ 19 ብሎ በተገኘበት ዓመተምህረት መዝግቦታል፡፡ በዚህም አሜሪካ ለዓለም ጤና ድርጅት እርዳታ ለማቆም ወስና ነበር ፡፡ ይህ ሁሉ የሀይል የበላይነትን ለመያዝ የሚደረግ ፉክክር ነው፡፡ ቻይና አሜሪካን በኢኮኖሚ ስታሸንፍ የካፒታሊዝም ስራዓት እየበሰበሰ የኮሚኒዝም ስራዓት ሊያብብ ይችላል፡፡ ቻይና በኢኮኖሚ፣ በህዝብ ብዛት እና ቴክኖሎጂን በማላመድ ዓለምን እየመራች ሲሆን፣ ከቀጣይ ስምንት ዓመት በኃላ ግን በየትኛውም ዘርፍ ቻይና የዓለም መሪ ትሆናለች ሲል ቢቢሲ የጥናት ፁሁፍ ጠቅሶ ዘግቧል፡፡ አሜሪካ በቻይና ስትነጠቅ የአውሮፓ ስልጣኔም አይታ ሊያጣ ይችላል፡፡ ዓለም ትኩረቱን ወደ መካከለኛው ምስራቅ እና እስያ ሊያተኩር ይችላል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply