You are currently viewing ከስንዴ ማሳ ጉብኝቱ የሚቀድመው ተግባር የቱ ነው?! የአሻራ ልዪ ምልከታ    ባህርዳር ።ሚያዚያ 08/2014/             አሻራ ሚዲያ ጠቅላይ ሚኒስትር…

ከስንዴ ማሳ ጉብኝቱ የሚቀድመው ተግባር የቱ ነው?! የአሻራ ልዪ ምልከታ ባህርዳር ።ሚያዚያ 08/2014/ አሻራ ሚዲያ ጠቅላይ ሚኒስትር…

ከስንዴ ማሳ ጉብኝቱ የሚቀድመው ተግባር የቱ ነው?! የአሻራ ልዪ ምልከታ ባህርዳር ።ሚያዚያ 08/2014/ አሻራ ሚዲያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አብዝተው ከጎበኟቸው ጉዳዮች አንዱ ስንዴ ነው። ስለስንዴም ብዙ ይናገራሉ። ስንዴ አንድ ቢሊየን ዶላር ወጭ ስለሚያስወጣ ስለስንዴ መናገራቸው፣ መጎብኘታቸው ልክነቱ አጠራጣሪ አይደለም።… ነገርግን ጠቅላይሚኒስትሩ በጎ ነገር ፍለጋ ላይ ናቸው። በጎ ነገር ያለ ስራ አይመጣም። የአማራ ክልል አርሶአደሮች 8 ሚሊየን ኩንታል ማዳበሪያ ይፈልጋሉ። እስካሁን ያገኙት ሁለት ሚሊየን አይሞላም። ከሚፈለገው ማዳበሪያ ገና 30 ከመቶ እንኳን ማግኘት አልተቻለም። የጠቅላይ ሚኒስትሩ የስንዴ ማሳ ጉብኝቱ ለአርሶአደሩ የግባት አቅርቦት ሚና ቢኖረው ኢትዮጵያ ከሁለት ዓመት በሗላ ዮክሬን ተክታ ራሷን አጥግባ አፍሪካን ትመግብ ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደ ሰሜን ሸዋ አቅንተው ስንዴ ሲጎበኙ የአማራ ክልል ዋና ዋና አመራሮች አልተከተሏቸውም። ጉብኝቱ ድንገተኛ ነው። አንዳንዶቹ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስንዴውን ሲጎበኙ ደብረብርሃን ቻይና ካምፕ ውስጥ የተፈናቀሉ ወገኖችንም ጎብኟቸው ሊሉ ይችላሉ። በአማራ ክልል 12 ሚሊየን ሰዎች በመፈናቀል እና በጦርነት እርዳታ ጠባቂ ሆነዋል። ሆስፒታል እና ትምህርትቤቶች ወድመዋል። ጠቅላይሚኒስትሩ እንደዚህ አይነት ነገር ጎብኝተው መላ ማበጀት አይመቻቸውም። ችግር አለ ሲባሉ አሜሪካም ችግር አለ ነው የሚሉ። ብልፅግና ወለጋን፣ መተከልን፣ ትግራይን አይመራውም ሲባሉ፣ ኢህኘዴግስ መቼ እስከ 1986 ዓም ወለጋን መራው በማለት ይመልሳሉ። በአማራ ክልል 12 ሚሊየን ሰዎች እርዳታ ጠባቂ ሆነዋል ቢባሉ፣ በህንድም 50 ሚሊየን ሰዎች እርዳታ ይጠብቃሉ ማለታችው አይቀሩም። ጠቅላይ ሚኒስትሩ አጣየ በእሳት ስትነድ ብሄራዊ ደህንነት ያስገነባውን ህንፃ መርቀዋል። በወቅቱም አበባ በመትከል ለምስራቅ አፍሪካ እንሸጣለን የሚል አይነት መልዕክት አስተላልፈዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ችግር የሚያነሳባቸው፣ ውስብስብ ነገር፣ ጥልቀት ያለው ትንታኔ አይመቻቸውም ይባልላቸዋል። ሽብርቅርቅ ነገር ይመቻቸዋል። የሚያወድሳቸው እና አሜን አሜን የሚላቸውን ሲያገኙ ነፍሳቸው ነው። የማዳበሪያ አቅርቦት እረፍት የነሳቸውን አርሶአደሮች ከማግኘት አስር ሄክታር የለማ ማሳ በመጎብኘት ኢትዮጵያ በቀጣይ ሰላሳ ዓመት ከአሜሪካ ቀጥላ ሁለተኛዋ ሀያል ሀገር ትሆናለች ይላሉ። በዚህ ሁኔታቸው ከምክትላቸው ከደመቀ መኮንን ጋርም ነፋስ ሳይገባባቸው የቀረ አይመስልም። አቶ ደመቀ እና ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በጋራ አይታዮም። ለመቃቃራቸው መንስኤ ባለፈው መጋቢት ሁለት እስከ አራት የተደረገው የማዕከላዊ ኮሚቴ ምርጫ ነው። ደመቀ መኮንን በተስፋየ ቤልጂጌ ለመተካት እና ደመቀንም እንደ አቶ ዮሃንስ ቧያሌው፣ ፀጋ አራጌ፣ ንጉሱ ጥላሁን፣ ላቀ አያሌው ወዘተ ለማባረር አስበው ነበር። አቶ ደመቀ መኮንን በስራ አስፈፃሚው እና በማዕከላዊ ኮሚቴው ምርጫ ብዙ ደስ ያላቸው አይመስልም። በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የሚመረጡ ካድሬዎች ችግር መስማት የማይፈልጉ፣ አሜን አሜን የሚሉ፣ ከብዙ ከሚያለቅሱ ሰዎች ይልቅ ስለ አንድ ስለሚስቅ ሰው ትኩረት የሚያደርጉ፣ ጥልቅ ትንታኔን የሚጠሉ ናቸው። በመሆኑም ስለአስከፊው የኑሮ ውድነት መፍትሄ ከመፈለግ ይልቅ የስንዴ ማሳ በመጎብኘት ይሄ ሲደርስ የኑሮ ውድነቱ ይጠፋል በማለት ለማፅናናት ይሞክራሉ። የአፈር ማዳበሪያ ጠፋ ሲባሉ የተፈጥሮ ማዳበሪያ መጠቀም ይቻላል ይላሉ። የቤት ማህበር ተደራጅተን ከተማ ቤት መስራት አልቻልንም የሚል ድምፅ ሲሰማ፣ በገጠርም መኖር ይቻላል የሚል ምላሽ ይሰጣሉ። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በፓርላማ የኑሮ ውድነቱ መንስኤ አብዝቶ መውለድ ነውም ብለው ነበር። በወቅቱ ከምክርቤቱ አባል የኢትዮጵያ የህዝብ ቁጥር ከቻይና፣ ከህንድ፣ ከፓኪስታን፣ ከኢንዶኔዥያ፣ ከአሜሪካ፣ ከናይጀሪያ ይበልጣል ወይ? ብሎ የጠየቀ አልነበረም። በአንድ ወቅት አቶ መለስ ዜናዊ የህዝብ ብዛት የኑሮ መወደድ መንስኤ አይሆንም። ሰው የሚወለደው መስሪያ እጅ እና ጭንቅላት ይዞ እንጂ ሆድ ብቻ ይዞ አይደለም ብለው ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ግን ሰው የሚወለደው ሆድ ብቻ ይዞ ነው የሚል ትንታኔ ሰጥተዋል። ይሄ ትንታኔያቸው አላወጣቸው ሲል የምግብ ባለሙያ ይሆኑና ዳቦ ውስጥ ሙዝ በመክተት ተመግቦ መሮጥ ይቻላል። ቅጠሎችን በጨው ነክሮ መመገብም ጥሩ ነው ይላሉ። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ትንታኔያቸው መድረኩን የተንተራሰ እንጂ ነገን የሚመለከት ላለመሆኑ አኔዱ ማሳያን እንጥቀስ። ሚያዚያ 2013 ዓም ለምክርቤት አባላት “ህወሃት ዱቄት ሆኗል። በኗል። ተኗል። ከእንግዲህ ህወሃት ህልውና የለውም” ብለው ነበር። ከሁለት ወር በሗላ ህወሃት ከሰኔ መጨረሻ ጀምሮ አማራ እና አፋርን ወሮ ክተት ታወጀ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የዲፕሎማሲ ስራቸው በመውደቁም እሳቸውን ጨምሮ በ90 ሹማምንቶች ላይ አሜሪካ የጉዞ ማዕቀብ ጣለች። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ኖቤል የተሸለመ ጠቅላይሚኒስትር ብቻ አይደሉም። የመጀመሪያው ማዕቀብ የተጣለባቸውም የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ናቸው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመርህ እና በተተነተነ መንገድ መራመድ ስለተሳናቸው የብልፅግና ወንጌል እየተፈረካከሰ የሀሜት ድርጅት ሆኗል። የአማራ ብልፅግና እነ አቶ ፀጋ አራጌ አሁንም ብልፅግና መርህ ይኑርህ እያሉት ሲሆን፣ የብሌፅግናው ወንጌል ፕሬዜዳንት ግን እኔ ስንዴ ማሳ ላይ ነኝ ፣ አልሰማም ያሉ ይመስላል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በእንደዚህ አይነት ካድሬዎች ሲማረሩ “ካድሬ ሌባ ነው። እናንተ ናችሁ ሀገር አዳኝ።”በማለት መከላከያውን ያጀግናሉ። ካድሬውን ሲሰበስቡ ሌላ ይናገራሉ። እንዲህ አይነት ዥዋዥዌነት የት እንደሚያደርስ የብልፅግና ወንጌል ብቻ ነው የሚያውቀው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply