ከስዕሎቹ ሁሉ አብልጦ የሚወደውን፣ እንዲሸጠው በመቶ ሺዎች ብር ቀርቦለት ፤ አልሸጥም አሻፈረኝ ያለውን ስዕሉን ለቤተ መንግስት በስጦታ የሰጠው ሰአሊ ተክለማርያም ዘውዴ ‘’በ2008 አካባቢ ት…

https://cdn4.telesco.pe/file/Ss9qGWqZURXuR2QoPbi-orEzaOLyT8JXJGKMqkhV4qgijx1yOQ4HDamiynCrXFH6wH_G-W6DCMNc3bkpKVW11wZK7mbH0JgwSRbtJzqUl6IQjYzxP6Ltv9UELzQ2WVxitbdyI_OLvthEGuKxKaxoPwXLcPLfBT_aCA4IfBzNGJY5ZcUvTdvNK2GAcyiCsqJ6b7uHzJGc2s8K7PX8F0ZBRPrzwB7B8hPM4msBCmBxQX_HyEFpUKM76gDVTfAL-4F9xv6mQ90vtIgkJpU4EkxY_nIKhj5s0_aXj9VYWAqFHx56utQ6C5PGlDKvorjBkxjVp0GWNpc5r5eFmbJXvqgApA.jpg

ከስዕሎቹ ሁሉ አብልጦ የሚወደውን፣ እንዲሸጠው በመቶ ሺዎች ብር ቀርቦለት ፤ አልሸጥም አሻፈረኝ ያለውን ስዕሉን ለቤተ መንግስት በስጦታ የሰጠው ሰአሊ ተክለማርያም ዘውዴ
‘’በ2008 አካባቢ ትዝ ይለኛል ፣ በሀገራችን ሁኔታ ተረብሼ ብሩሼን አነሣሁ ወቅቱን ይገልፃል ብዬ ያሠብኩትን ሸራው ላይ አስቀመጥኩ፡፡ ብዙ ጊዜ ለፍቼበታለሁ፣ ደክሜበታለሁ፡፡ ይህንን ስዕል ለግለሰብ መሸጥ ሊዋጥልኝ አልቻለም፡፡ ከስዕሎቼ ሁሉ ለዚህ ስዕል ሰጠሁ፡፡ በእውነት ተሠዋሁለት፡፡ የምጥልበት ሳይሆን የማስረክብበት አስጨነቀኝ፡፡

ቤተ መንግስት ውስጥ እጄን ወደ ስዕሉ ቀስሬ
በሠዎቹና በብርሀኑ መካከል የጠቆረ ዳመና አለ ፣ ይህ ሀገራችን ውስጥ ያለውን ምስቅልቅልና የህዝቦች ሁኔታ ያሳያል፡፡ አይነት መልእክት አስተላለፍኩ፡፡ በፅሞና የሰሙኝ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ” ስዕሉን የሚታይ ቦታ ስቀሉት ለጎብኚዎች የሃገራችሁን በሙሉ እርሱ እንደነገራችሁ በሏቸው ነገር ግን ደመናውን ወይ እናተነዋለን ወይ ይዘንባል በሏቸው ” ብለው ለባለስልጣኖቻቸው ትዕዛዝ አስተላለፉ፡፡ ስሜቴ ተገማሸረ፡፡ ‘የስዕሌ ግጣሙ ግድግዳው እዚህ ነው ማለት ነው?……ስል ስለምወደው ስዕሌ ዕጣ ፈንታ በድስታ አሰብኩ……ሰአሊ ተክለማርያም ዘውዴ

ክቡራትና ክቡራን ፕሮግራማችን ከ 10፡00 ሰዓት ጅምሮ ከሰዓሊ ተክለማርያም ዘውዴ ጋር እንጨዋወታለን፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply