ከስጋ ነጋዴ ላይ ጉቦ ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ ተያዙ!በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ከስጋ ነጋዴ ላይ ጉቦ የተቀበሉ የከተማ ግብርና ጽህፈት ቤት ሰራተኞች እጅ ከፍንጅ መያዛቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/DKyijsrTUeYzatt6yHr8XB8VJrgipCfHZ8L_XOCGk29HIi3Oridn3kB5G9n1r4oE-z4jefL_weeN49rLg1vWBUGokD4cf3UFyoTdqZnjrBTXprB0EnnPsl7Hj1C8TVzF1cJ3AeTPFfUYXHTiRGiPQEUTNh1lHqGOFHNTNzEN9p1IlkJrYfZYLH1tldYBuTZV2lYZkFNVz1vWxZ6WvOZN_SJ7Sflrl9BTEBnShi51-XopJgl9hBo3We06lwhqZvDFTHTc0TKeiLgqlX1lfOo5ev0Del49RRNZsHEMJoNUXIub9EzQ-qfh2-I2KUmQSqXA97-5Dy2crxe6VyLIM-FXDQ.jpg

ከስጋ ነጋዴ ላይ ጉቦ ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ ተያዙ!

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ከስጋ ነጋዴ ላይ ጉቦ የተቀበሉ የከተማ ግብርና ጽህፈት ቤት ሰራተኞች እጅ ከፍንጅ መያዛቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገለፀ።

በቁጥጥር ስር የዋሉት ተጠርጣሪዎች በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የከተማ ግብርና ጽህፈት ቤት ሰራተኞች ሲሆኑ ሰለሞን ቴዎድሮስ የተባለው ግለሰብ የግብርና ኢንስፔክሽንና ሬጉላቶሪ ቡድን መሪ እንዲሁም መለሰ ቢራራ ደግሞ የእንስሳትና ስጋ ቁጥጥር ባለሙያ ናቸው፡፡

ሰራተኞቹ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ልዩ ቦታው ሰባተኛ አካባቢ ከአንድ ግለሰብ ግሮሰሪ ውስጥ ገብተው የ6 ወር የጤንነት ሁኔታ ማረጋገጫ ወረቀት አላሳደስክም ስለዚህ ከአሁን ሰዓት ጀምሮ ምንም አይነት ምግብ እና ስጋ መሸጥ አትችልም ብለው በማስፈራራት ቤቱን እንደሚያሽጉት ለስጋ ነጋዴው ይነግሩታል፡፡

ስጋ ነጋዴው የግል ተበዳይም ጉዳዩን ለፖሊስ በማሳወቃቸው እና ፖሊስም አስፈላጊውን ክትትል በማድረጉ ተጠርጣሪዎቹ 1ሺህ ብር ጉቦ ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ ሊያዙ መቻላቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።

ሙስና እና ሌብነት ሊወገዝ እና ትግል ሊደረግበት የሚገባው በመጠኑ መብዛት እና ማነስ ብቻ ሳይሆን በአስተሳሰብ እና በአመለካከት ዙሪያ የሚታዩ ችግሮች እንዲቀረፉ ጭምር በመሆኑ ህዝብን እያማረሩ ያሉ ከአነስተኛ እስከ ከፍተኛ ደረጃ የሚገለፁ የሙስና ወንጀሎች እንዲከስሙ የግል ኪሳቸውን ለማደለብ የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦችን አጋልጦ በመስጠት ህብረተሰቡ ወቅቱ የሚጠይቀውን ቀና ተባባሪነት አጠናክሮ እንዲቀጥል የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪውን አቅርቧል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ታህሳስ 25 ቀን 2015 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply