ከሶማሊያ ወደ ኢትዮጵያ ለሚገቡ ስደተኞች ዕርዳታ እንዲደረግ ተጠየቀ

https://gdb.voanews.com/01000000-0aff-0242-5746-08db2af98bb8_w800_h450.jpg

ጦርነትን በመሸሽ ከሶማሊያ ወደ ኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል በመግባት ላይ ለሚገኙ ስደተኞች ሕይወት አድን ዕርዳታ ለማድረግ የ116 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ እንዲደረግ የተባበሩት መንግሥታት የረድኤት ድርጅቶች ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ባለፈው ወር ላስካኑድ በተባለቸው የሶማሊያ ግዛት ግጭት ከተቀሰቀሰ በኋላ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ሶማሊያውያን የሃገር ውስጥ ተፈናቃይ ሲሆኑ፣ አንድ መቶ ሺህ የሚጠጉት ደግሞ የኢትዮጵያን ድንበር አቋርጠው ገብተዋል፡፡

አብዛኞቹ ኢትዮጵያ የደረሱት ስደተኞች ሕጻናትና ሴቶች እንዲሁም በዕድሜ የገፉ አዛውንቶች ናቸው ሲል የተመድ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ዛሬ ከጀኒቫ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

በመሬት ላይ ያለው የሰብዓዊ ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑንና በሽታ የመከሰት ዕድሉም ከፍተኛ ነው ብሏል ኮሚሽኑ ከሌሎች ረድኤት ድርጅቶች ጋር በመሆን ባወጣው መግለጫ።

የኢትዮጵያ መንግሥትና የአካባቢው ማሕበረሰብ ስደተኞቹን በመቀበል ሰብዓዊ ዕርዳታ በማድረግ ላይ ቢሆኑም እየጨመረ በመጣው የስደተኞቹ ቁጥር ምክንያት አቅርቦቱ እየተመናመነ በመሆኑ ተጨማሪ ዕርዳታ ያስፈልገናል ብለዋል የረድኤት ድርጅቶቹ ከጀኒቫ ባወጡት መግለጫ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply