ከሶስት ዓመታት በፊት ተቋቁሞ የነበረው ሳልሳይ ወያኔ ትግራይ በምርጫ ቦርድ እውቅና ማግኘቱን አስታወቀ፡፡የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ለሳልሳይ ወያኔ ትግራይ የክልላዊ ፓለቲካ ፓርቲ ዕውቅና መስጠቱ…

ከሶስት ዓመታት በፊት ተቋቁሞ የነበረው ሳልሳይ ወያኔ ትግራይ በምርጫ ቦርድ እውቅና ማግኘቱን አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ለሳልሳይ ወያኔ ትግራይ የክልላዊ ፓለቲካ ፓርቲ ዕውቅና መስጠቱን አስታውቋል፡፡

የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ኪሮስ ሀይለስላሴ ከጣብያችን ጋር በነበራቸው ቆይታ ደግማቹ ጉባኤ አድርጉ በመባላችን በድጋሚ ጉባኤ አድርገን ዕውቅናው ሊሰጠን በቅቷል ብለዋል፡፡

ነገር ግን ለምን ጉባኤውን በድጋሚ እንዲደርግ እንደተደረገ ምንም ግልፅ ነገር የለም ብለውናል፡፡
ቦርዱ ምንአልባትም በጦርነቱ ወቅት አንድ አንድ የፓርቲው አባላት በጦርነት ወቅት በመሳተፋቸው ምክንያት ከዚህ ጋር በተያያዘ ሊሆን እንሚችል ተናግረዋል፡፡

ከጦርነቱ በፊት ግዚያዊ ዕውቅና ተሰቷት መንቀሳቀስ ሲጀመር የሰሜኑ ጦርነት በመቀስቀሱ የፓርቲው ህልውና አደጋ ላይ ወድቆ መቆየቱ ተገልፃል፡፡
ከዚህ ቀደምም ባይቶና አባይ ትግራይ በተመሳሳይ ዕውቅና በቅርቡ ማግኘቱ የሚታወቅ ነው፡፡

ከሰሞኑ በትግራይ የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች ዕውቅና እየተሰጣቸው መሄዱ የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ የፓርቲ ሕወሓት ሕጋዊ ሰውነት ሊመለስ ይችላል ወይ የሚል ጥያቄ ተነስቷል፡፡

በቅርቡም የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ በፓርቲያቸው ጉዳይ ከፌደራል መንግስት ጋር በተወያየበት ወቅት የሕወሓት ሕጋዊ ሰውነት እንዲመለስ ውይይት መደረጉን ተናግረዋል፡፡
በዚህም ሕወሓት በምርጫ ቦርድ እንዲመዘገብና ዕውቅና እንዲያገኝ ተስማምተናል ብለው ነበር፡፡

ይህንንም በተመለከተ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድን ጠይቀን የነበረ ሲሆን ከሰሞኑ የፓርቲዎች ዕውቅና ማግኘት ከህውሃት ጉዳይ ጋር የማይገናኝ ነው ሲሉ ምላሽ ሰጥተውናል፡፡

በአቤል ደጀኔ
የካቲት 22 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Source: Link to the Post

Leave a Reply