You are currently viewing ከሸኖ እስከ ለገጣፎ በፀጥታ ሀይሎች አማካኝነት በመንገደኞች ላይ የሚደርሰው ጭቆና እንዲቆም የአማራ ወጣቶች ማህበር በሸዋ ጠየቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ    ነሃሴ 2 ቀን 2014 ዓ.ም…

ከሸኖ እስከ ለገጣፎ በፀጥታ ሀይሎች አማካኝነት በመንገደኞች ላይ የሚደርሰው ጭቆና እንዲቆም የአማራ ወጣቶች ማህበር በሸዋ ጠየቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ነሃሴ 2 ቀን 2014 ዓ.ም…

ከሸኖ እስከ ለገጣፎ በፀጥታ ሀይሎች አማካኝነት በመንገደኞች ላይ የሚደርሰው ጭቆና እንዲቆም የአማራ ወጣቶች ማህበር በሸዋ ጠየቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ነሃሴ 2 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የአማራ ወጣቶች ማህበር በሸዋ ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ በፅሁፍ እና በቃል አቤቱታ ቢያቀርብም ምንም አይነት ምላሽ አላገኘም። ይልቁንስ ችግሩ ከቀን ወደ ቀን ተባብሶ አሁን ላይ ከቆቦ፣ ከደሴ፣ ከኮምቦልቻ፣ ከሚሴ፣ ከአጣዬ፣ ከሸዋሮቢት፣ከደብረ ሲና፣ ከደብረብርሃን እና ከተለያዩ የአማራ ክልል አካባቢዎች ወደ አዲስ አበባ የሚመጡ ተጓዦች ከሸኖ እስከ ለገጣፎ ድረስ ከመኪና በማስወረድ እንዲሰለፉ በማድረግ እንዲመለሱ እየተደረገ ስለመሆኑ ጠቅሷል። የጸጥታ አካላትም አዲስ አበባ መግባት የምትችሉት የአዲስ አበባ መታወቂያ ሲኖራችሁ ብቻ ነው በማለት ያልተገባ እንግልትና ወከብ እየፈጸሙ ስለመሆኑ የአማራ ወጣቶች ማህበር በሸዋ አስታውቋል፡፡ ይህ የኦሮሚያ የፀጥታ ሃይሎች (የኦሮሚያ ልዩ ኃይል አባላት) ከወጣቶች ጋር ሆነው በመሳሪያ ጭምር ህዝባችንን እያስፈራሩ እና እንግልት እየፈፀሙባቸው ይገኛል ያለው ማህበሩ የችግሩ ሰለባ የሆኑትንም እንደሚከተለው ዘርዝሮ አስረድቷል፡- 1) በጤና እክል ምክንያት ሪፈር የተባሉ ፣ አዛውንቶች፣ ከትራንስፖርት ውጭ ገንዘብ የሌላቸው ምስኪኖችም ያሉ መሆኑ። 2) የእምዬ ምኒልክ ክፍለ ከተማ የደብረ ብርሃን ሪጅዮ ፖሊታንት አንዱ ክ/ከተማ ሲሆን ከደብረብርሃን ወደ አዲስ አበባ የሚጓዙ የክፍለ ከተማውን መታወቂያ የያዙ ነዋሪዎችን “ምኒልክ የሚለው ስም መታወቂያው ላይ ምን ይሰራል?፣ ለምን ተቀበላችሁ?” በማለት ለድብደባ እና ለእስር እየተዳረጉ ነው፤ እንዲሁም መታወቂያቸውን በመቅደድ እንግልት እየፈፀሙባቸው ይገኛሉ ሲል በአማራ ላይ የሚፈጸመውን ተደራራቢ በደል ገልጧል፡፡ አቤቱታቸውን ለሚመለከተው አካል ቢያቀርቡም ምንም አይነት ምላሽ ባለማግኘታቸው አላስፈላጊ ነገር ውስጥ ከመግባታችን በፊት ይህ ጥያቄ መፍትሄ ሊሰጠው ይገባል ብሏል። በመጨረሻም የአማራ ወጣቶች ማህበር በሸዋ ይህ የማይሆን ከሆነ የህዝባችንን እንግልት፣ ድብደባ ለማስቆም አማራጭ የትግል ስልት እና መብት የማስከበር ሂደት የምንጠቀም መሆኑ ታውቆ በአስቸኳይ እንዲፈታልን በማለት ለአማራ ክልል መንግስትና ለሌሎች መንግስታዊ ተቋማት ጭምር ጥሪ አድርጓል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply