You are currently viewing ከሸኖ እስከ ለገጣፎ በፀጥታ ኃይሎች በመንገደኞች ላይ የሚደርሰውን ጭቆና እንዲቆም የአማራ ወጣቶች ማህበር በሸዋ ጠየቀ! ሰ.ሜሪካ :- ነሀሴ 02/2014 ዓ.ም…

ከሸኖ እስከ ለገጣፎ በፀጥታ ኃይሎች በመንገደኞች ላይ የሚደርሰውን ጭቆና እንዲቆም የአማራ ወጣቶች ማህበር በሸዋ ጠየቀ! ሰ.ሜሪካ :- ነሀሴ 02/2014 ዓ.ም…

ከሸኖ እስከ ለገጣፎ በፀጥታ ኃይሎች በመንገደኞች ላይ የሚደርሰውን ጭቆና እንዲቆም የአማራ ወጣቶች ማህበር በሸዋ ጠየቀ! ሰ.ሜሪካ :- ነሀሴ 02/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ለአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ባህርዳር ጉዳዩ:- ከሸኖ እስከ ለገጣፎ በፀጥታ ሀይሎች በመንገደኞች ላይ የሚደርሰውን ጭቆና እንዲቆም ስለማሳሰብ ከላይ በርእሱ ለመግለፅ እንደተሞከረው ማህበራችን የአማራ ወጣቶች ማህበር በሸዋ ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ በፅሁፍ፣በቃል አቤቱታ ቢያቀርብም ምንም አይነት ምላሽ አላገኘም ችግሩ ከቀን ወደ ቀን ተባብሶ አሁን ላይ ከቆቦ፣ ከደሴ፣ ከኮምቦልቻ፣ ከሚሴ፣ አጣዬ፣ ከሸዋሮቢት፣ከደብረ ሲና፣ ከደብረብርሃን እና ከተለያዩ የክልላችን ወረዳዎች ወደ አዲስ አበባ በሸኖ የሚጓዙ ተጓዦች ላይ ከሸኖ እስከ ለገጣፎ ድረስ ከመኪና በማስወረድ እንዲሰለፉ በማድረግ ወደ አዲስ አበባ መግባት የምትችሉት የአዲስ አበባ መታወቂያ ብቻ ያለው ነው፡፡ ከዛ ውጭ ያላችሁ ማለፍ አትችሉም የሚሉ የፀጥታ ሃየሎች ከወጣቶች ጋር ሆኖ በመሳሪያ ጭምር ህዝባችንን እያስፈራሩና እንግልት እየፈፀሙባቸው ይገኛል። የችግሩ ሰለባ ከሆኑት መካከል፡- 1 በጤና እክል ምክንያት ሪፈር የተባሉ ፣ አዛውንቶች፣ ከትራንስፖርት ውጭ የሌላቸው ምስኪኖችም ያሉ መሆኑ። 2 በትልቅ እድገት ላይ ያሉ ከተሞች ወደ ሪጅዩ ፖሊታንት ማደጋቸው ይታወቃል ይህን ተከትሎ ደብረ ብርሃን ሪጅዮ ፖሊታንት ወደ በአምስት (5) ክፍለ ከተማ ተዋቅራለች በዚህም እምዬ ምኒልክ ክፍለ ከተማ አንዱ ሲሆን ከደብረብርሃን ወደ አዲስ አበባ የሚጓዙ የክፍለ ከተማውን መታወቂያ የያዙ ነዋሪዎችን ምኒልክ የሚለው ስም መታወቂያው ላይ ምን ይሰራል ለምን ተቀበላችሁ በማለት ለድብድብ ለእስር እየተዳረጉ እንዲሁም መታወቂያቸውን በመቅደድ እንግልት እየፈፀሙባቸው ይገኛል፡፡ ስለዚህ አቤቱታቸውን ለሚመለከተው አካል ቢያቀርቡም ምንም አይነት ምላሽ ባለማግኘታቸው አላስፈላጊ ነገር ውስጥ ከመግባታችን በፊት ይህን ችግር እየፈጠረ ያሉትን የመንግስት የፀጥታ ሀይሎች፣ግለሰቦች ሀገርን ከሚመራው የመንግስት ስርዓት ውጭ በመንግስት ስር ተደብቀው የሚፈፅሙትን እንዲያቆሙ ከሚመለከተው ጋር በመነጋገር መፍትሄ ኢንዲያገኝ እያሳሰብን ይህ የማይሆን ከሆነ የህዝባችንን እንግልት ድብደባ ለማስቆም አማራጭ የትግል ስልት እና መብት የማስከበር ሂደት የምንጠቀም መሆኑ ታውቆ በአስቸኳይ እንዲፈታልን ማለት እንወዳለን። ግልባጭ፡- ሰላም ለሁሉም!! 👉ለአማራ ክልል ሰላምና ደህንነት ቢሮ 👉ለሰ/ሸዋ ዞን አስተዳደር 👉ለሰ/ሸዋ ዞን ሰላምና ደህንነት መምሪያ 👉ለደብረብርሃን ሪጅዮ ፖሊታንት ከተማ አስተዳደር 👉ለደብረ ብርሃን ሪጂዮ ፖሊታንት ከተማ አስተዳደር ሰላምና ደህንነት መምሪያ ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply