!ከሸዋሮቢትና አካባቢው ወጣቶች የተላለፈ አስቸኳይ መልክት:- ግንቦት 18 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ውድ የከተማችን ህዝብ ሆይ በቅድሚያ የማክበር ሰላምታችንን እያቀረብን እንደሚታወ…

!ከሸዋሮቢትና አካባቢው ወጣቶች የተላለፈ አስቸኳይ መልክት:- ግንቦት 18 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ውድ የከተማችን ህዝብ ሆይ በቅድሚያ የማክበር ሰላምታችንን እያቀረብን እንደሚታወቀው መንግስት በልጆቻችን እና በወገኖቻችን ላይ ጦርነት በገሀድ ከከፈተ ሰንብቷል ይሁን እንጂ የጀግናው የ እሸቴ ሞገስ ልጆች በሚገባው ቋንቋ አናግረው መልሰውታል እምብኝ አሻፈረኝ አልቀመስም ስላሉት አሁን ደግሞ ፊቱን ወደ ሽማግሌዎች እና በከተማችን አመራሮች ላይ አዙሮ እያስፈራራ እና ጫና እየፈጠረ ከተማውን እያጨናነቀ ይገኛል ሆኖም ግን በዚህች ሰዓት ማን ምን ማድረግ እንዳለበት እንደሚከተለው መልክታችንን አስተላልፈናል። 1,ሁሉም የከተማው ህዝብ አንድነታችን እንደሚበጀን አውቆ ከፋኖ እና ከ ከሽማግሌዎች ጎን እንድትቆሙ እያልን 2,አባቶቻችን ሳትፈሩ በ አቋማችሁ ፀንታችሁ ልጆቻችሁን አሳልፋችሁ እንዳትሠጡ እና ታሪክ እንዳታበላሹ 3,በከተማው ያለ የታጠቀ ሀይል ጫካ ገብቶ ከፋኖ ጎን እንዲቆም እምብኝ አሻፈረኝ ይበል 4,በከተማችን ያላችሁ መከላከያ ከተቻላችሁ ከቆራጡ ከከተማችን ህዝብ እና ከወንድማችሁ ከፋኖ ጎን እንድትቀላቀሉ ያ ካልሆነ ግን የበለጠ መጨራረስ እና መስዋትነት እንደምትከፍሉ እወቋት 5,በከተማዋ ያላችሁ ባንዳዎች አርፋችሁ እንድትቀመጡ ያ ካልሆነ ግን እያጋለጥን እንደምንረሽን እወቁት ሀቅ ነው ማስፈራሪያ አይደለም 6,በአጠቃላይ የከተማው ህዝብ እና አመራሮች ሽማግሌዎች ሳትፈሩ ከእኛ ከፋኖዎች ጎን እንድትቆሙ በጥብቅ እናሳስባለን አማራነታችንን, ነፃነታችንን በተባበረ ክንዳችን እናስመልሳለን #💪ድል ለአማራ ህዝብ እና ፋኖ መረጃው የአማራ ወጣቶች ማህበር በሸዋሮቢት ነው ። “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply