ከሸዋሮቢት፣ከአጣዬ፣ከካራቆሬ እና ቆሪሜዳ ከተስፋፊውና ጽንፈኛው የኦነጋዊያን ቡድን አሰቃቂ ጥቃት የሸሹ አማራዎች የድረሱልን ጥሪ አቀረቡ።

ከሸዋሮቢት፣ከአጣዬ፣ከካራቆሬ እና ቆሪሜዳ ከተስፋፊውና ጽንፈኛው የኦነጋዊያን ቡድን አሰቃቂ ጥቃት የሸሹ አማራዎች የድረሱልን ጥሪ አቀረቡ።

አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ
ሚያዝያ 10 ቀን 2013 ዓ.ም
አዲስ አበባ ሸዋ

በኦሮሚያ የመንግስት አካላት ጭምር እንደሚደገፍ የተነገረለት ጽንፈኛ፣ተስፋፊና ዘር አጥፊ የኦነጋዊ ቡድን በተለይ ጠ/ሚ አብይ አህመድ ስልጣን ከያዙበት ጊዜ ጀምሮ ላለፉት 3 ዓመታት በአማራዎች ላይ መጠነ ሰፊ የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈጽሟል፤ አሁንም ቀጥሎበታል።

ይህ ጠባብ ፀረ አማራ እና ፀረ ኢትዮጵያ ቡድን የሰለጠነ፣ የቡድን መሳሪያዎችን ጭምር የታጠቀ አማራ ሆነው እስከተገኙ ድረስ
ህጻናት፣ሴትና አቅመ ደካሞችን ሳይመርጥ እየጨፈጨፈ ነው።

ከሚያዚያ 6 ቀን 2013 ጀምሮ በሸዋ አጣዬ፣ካራቆሬ፣ቆሪሜዳ፣ጀብውሃ እና ሸዋሮቢት አካባቢ በቡድን መሳሪያና በከፍተኛ የሰለጠነ የሰው ኃይል በመጠቀም ንፁሀን አማራዎችን ጨፍጭፏል፤ አጣዬ፣ካራቆሬና ቆሪሜዳን እንዳልነበሩ አድርጎ አውድሟል።

በዚህ አማራ ተኮር ጥቃት ከኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን በርካታ አመራሮች በዋና አሰልጣኝነት፣መሪነት፣በስንቅና ትጥቅ አቀባይነት የተሳተፉ መሆናቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል።

የፌደራልም ሆነ የአማራ ክልል መንግስት የአማራን ህዝብ ከተደራጀና በሴራ ከተሞላው ተደጋጋሚ የዘር ፍጅት ለመታደግ አለመቻላቸው የአደባባይ እውነታ ሆኗል።

ከአጣዬ፣ከካራቆሬ፣ከቆሪሜዳ፣ከጀብውሃና ከሸዋሮቢት ከጥቃቱ ሸሽተው በየጫካው በመሆን የድረሱልን ጥሪ እያቀረቡ ነው።

አሚማ ያነጋገራቸው ሚያዚያ 8 ቀን 2013 ከካራቆሬ ተፈናቅለው ሰለሎ በሚባል አካባቢ በሁለንተናዊ ችግር ላይ መሆናቸውን የገለፁት ከ2 ሽህ የማያንሱ አማራዎች መንግስት ካለ ይድረስልን ብለዋል፤ የሰው ልጅ ጉዳይ ለሚገዳቸው ሁሉ ጥሪ አድርገዋል።

ሰብአዊ እርዳታ እና የደህንነት ጥበቃ በእጅጉ ከሚያስፈልጋቸው መካከልም ከሸዋሮቢት ከተማ ሚያዚያ 9 ቀን 2013 ከቀኑ 9 ሰዓት ጀምሮ በተፈፀመባቸው ጥቃት እንዲሁም በስጋት ሸሽተው አርማኒያ በምትባል የገጠር ከተማ በከፍተኛ ችግር ላይ እንደሚገኙ ገልፀዋል።

እንዲህ ዓይነት መንግስት በህይወት ዘመናችን አይተን አናውቅም ያሉት ተፈናቃይ እናት በመቶዎች እየተገደሉ፣ሽህዎች እየተፈናቀሉና ከተሞች እየወደሙ አዲስ አበባ ላይ ቤት ሲያስመርቅ የሚውል ሲሉ ክፉኛ ተችተዋል።

አማራነት እንደ ማጥቂያ መስፈርት ተይዞ እየተጠቁ ካሉ ክርስቲያንና ሙስሊም አማራዎች ጋር ያደረግነውን ቆይታ በአሚማ የዩቱብ አድራሻ ይጠብቁ።


Source:- አማራ ሚዲያ ማዕከል

Source: Link to the Post

Leave a Reply