ከሸዋሮቢት እስከ ካራቆሬ ባሉ ከተሞች የከፍተኛ ኃይል ተሸካሚ መስመሮችን የመጠገን ሥራ መስራት ተገለጸ በሽብርተኛውና የህወኃት ቡድን ጉዳት የደረሰባቸው ከሸዋ ሮቢት እስከ ካራቆሬ ባሉት ከ…

ከሸዋሮቢት እስከ ካራቆሬ ባሉ ከተሞች የከፍተኛ ኃይል ተሸካሚ መስመሮችን የመጠገን ሥራ መስራት ተገለጸ

በሽብርተኛውና የህወኃት ቡድን ጉዳት የደረሰባቸው ከሸዋ ሮቢት እስከ ካራቆሬ ባሉት ከተሞች የሚገኙ የከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች ተጠግነው ተጠናቀዋል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በሸዋሮቢት፣ በጀውሀ፣ በሰንበቴ፣ በአጣዬና ካራቆሬ ከተሞች የሚያልፈውን የከፍተኛ መስመር በመጠገን ለስርጭት መስመሮች ኃይል መስጠት እንዲችሉ ዝግጁ የማድረግ ሥራ አጠናቋል።

ይህን ተከትሎ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የጀመረው የሥርጭት መስመሮች የጥገና ሥራ እንደተጠናቀቀ የተጠቀሱት ከተሞችና አጎራባች የገጠር ቀበሌዎች በፍጥነት የኤሌክትሪክ ያገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በቀጣዮቹ ቀናት ከካራቆሬ እስከ ከሚሴ ያለው መስመር የመጠገን ሥራ እንደሚሰራ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን
ህዳር 27 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply