#ከሸዋሮቢት ከንቲባ ግድያ ጋር በተያያዘ በወንጀል ተጠርጥረው ካለምንም ፍትህ ታስረው የሚገኙት መምህር ከፈለኝ ደረሴ በተደራራቢ ህመም እየተሰቃዩ እንደሚገኙ ተገለፀ! ታሕሳስ 21 ቀን 20…

#ከሸዋሮቢት ከንቲባ ግድያ ጋር በተያያዘ በወንጀል ተጠርጥረው ካለምንም ፍትህ ታስረው የሚገኙት መምህር ከፈለኝ ደረሴ በተደራራቢ ህመም እየተሰቃዩ እንደሚገኙ ተገለፀ! ታሕሳስ 21 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ የመምህር ከፈለኝ ደረሴ ቤተሰቦች መምህሩ በስኳር እና በግፊት በሽታ እየተሰቃዩ እንደሚገኙ ገልፀው፤ የታሰሩት ወንጀል ሰርተው ሳይሆን ከላይ ባሉ አመራሮች ይሁንታ ነው ሲሉ ለአሻራ ሚዲያ ተናግረዋል። መምህሩ ዕድሜያቸው የገፉት በማስተማር ስራ ነው። የሽዋሮቢት ህዝብ ያውቃቸዋል። ተንኮል እና ሴራ አያቁም። ለእስር የሚያበቃ ምንም አይነት የወንጀል ማስረጃ አልተገኘባቸውም ብለዋል። ይሁን እንጃ ፍ/ቤቱ ነጻ ቢያሰናብታቸውም በአንዳንድ አመራሮች ምክንያት ከህግ አግባብ ውጭ ታስረው እየተሰቃዩ ይገኛሉ ሲሉ ተናግረዋል። አክለውም ታህሳስ 19ቀን 2015 ዓ /ም በደብረ ብርሃን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዋለው ችሎት በ8000 ሺህ ብር ዋስ እዲፈቱ በፍ/ቤቱ የተወሰነ ቢሆንም፤ ከዞን በመጡ አመራሮች ከፍርድ ቤት ሊወጡ ሲሉ በር ላይ አስረው ወደ ባሶ ፖሊስ ጣቢያ ወስደዋቸዋል ብለዋል። ጨምረውም በተመሳሳይ ሌሎች ወንድሞቻችን እንደ መምህር ከፈለኝ በግፍ ታስረው ለሚሰቃዩ ፍትህ እንጠይቃለንም ሲሉ ገልፀዋል። ይህ አካሄድ የፍትህ ስራዓቱን የናቀ እና በርካታ ወገኖቻችንን አደጋ ላይ የጣለ በመሆኑ በፍትህ ስራዓቱ ውስጥ ጣልቃ እየገቡ ያሉ አካላት ከዚህ ድርጊታቸው ሊታረሙ ይገባል በማለት መልክታቸውን በአሻራ ሚዲያ አስተላልፈዋል። “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply