
ከሸዋሮቢት ወደ አርማኒያ ቀበሌ ማፉድ እና አባያ አጥር_ራሳ ፋኖን ትጥቅ ለማስፈታት አቅንቷል የተባለው የኦህዴድ ብልጽግና አገዛዝ ጦር በከባድ መሳሪያ ታግዞ ተኩስ በመክፈት በአርሶ አደሮች ላይ ግድያ ፈጽሟል ሲሉ የዐይን እማኞች ተናገሩ። የአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ግንቦት 10/2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ከሸዋሮቢት ወደ አርማኒያ ቀበሌ ማፉድ እና አባያ አጥር_ራሳ ፋኖን ትጥቅ ለማስፈታት አቅንቷል የተባለው የኦህዴድ ብልጽግና አገዛዝ ጦር በተለይም ግንቦት 9/2015 ከጠዋት ጀምሮ በከባድ መሳሪያ ታግዞ ተኩስ በመክፈት በአርሶ አደሮች ላይ ግድያ ስለመፈጸሙ አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ያነጋገራቸው የዐይን እማኞች ተናግረዋል። እንደአብነትም እስካሁን በተገኘው መረጃ መሰረት በአባያ አጥር ራሳ ልዩ ስሙ አራዳ በተባለ አካባቢ በቤታቸው የነበሩ 5 አርሶ አደሮች ተገድለዋል፤ በተመሳሳይ ወዲያ አገር በተባለ የራሳ አካባቢም ሰዎች ስለመገደላቸው ተነግሯል። ነዋሪዎች እንደሚሉት ከሸዋሮቢት ወደ አርማኒያ እና ራሳ 20 መኪና ትጥቅ አስፈች ነው የተባለው የአገዛዙ ኃይል ግንቦት 9/2015 በሰሜን ሸዋ ዞን ቀወት ወረዳ አርማኒያ ቀበሌ ማፉድ አካባቢ ጠዋት ላይ ተኩስ ከፍተው አርፍደዋል። ግንቦት 9/2015 ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ እስከ ቀኑ 12 ሰዓት ድረስ ደግሞ አባያ አጥር ቀበሌ ራሳ አካባቢ፦ 1. ሳላይሽ፣ 2. አራ ጎብዲ፣ 3. አራዳ እና 4. አሻር ላይ ተኩስ ከፍተው ውለዋል።
Source: Link to the Post