ከሽግግር ሂደቱ በፊት በሃገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች እየተካሄዱ ያሉ ግጭቶች በቅድሚያ ሊቆሙ ይገባል ሲል ሴታዊት የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅትና አጋሮቹ አስታወቁ፡፡

በታቀደዉ የሽግግር ፍትህ ሂደት ዙርያ ሴታዊትና አጋሮችዋ የአቋም መግለጫ አውጥተዋል፡፡
ከድርጅቱ ለጣብያችን ኢትዮ ኤፍ ኤም በተላከው መግለጫ መሠረትም የሽግግር ፍትህ ስርዓቱ ከመጀመሩ በፊት የሽግግር ፍትህ ሂደቱን ለማካሄድ አመቺ እና አስቻይ ሁኔታዎች መፈጠር መቻል አለበቸው ብሏል ።

በሃገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች እየተካሄዱ ያሉ ግጭቶች በቅድሚያ ሊቆሙ ይገባል ያለው መግለጫው በግጭት ሳቢያ ለመፈናቅል የተጋለጡ ህዝቦች ወደ ቅያቸው ሊመለሱ እና ለመልሶ ማቋቋም አመቺ እና አስቻይ ሁኔታ ሊሟላላቸው ይገባል ሲል ያክላል።

ባለ 20 ነጥቡ መግለጫ በርካታ መደረግ ያለባቸውን ቅድመ ሁኔታዎችን ያገናዘበ መሆኑንም ጣብያችን ተመልክቷል፡፡

የሽግግር ፍትህ ሂደት ዘላቂነት ያለው ሰላም እና ፍትህ ለማምጣት የሚካሄድ ስርዓት እንደመሆኑ መጠን አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት የሚካሄዱ ጉዳዮቸ ላይ የተመረኮዘ ሊሆን አይገባም ይላል።

ከዚህ በተጨማሪ ከታጣቂ ሃይሎች ጋር እየተካሄዱ ያሉ ስምምነቶች ለማህበረሰቡ ግልጽ እና ተዓማኒነት ሊፈጥሩ ይገባል የሚለው መግለጫው ለግጭቶች እና የተለያዩ ማህበረሰባዊ ችግሮች መፈጠር በተለያየ መልኩ ወሳኝ እና ጉልህ ሚና ሲጫወቱ የነበሩ አካላት በሽግግር ፍትህ አፈጻጸም ሂደቱ ላይ ግልጽ እና ውስን ሚና ሊኖራቸው ይገባልም ተብሏል።

መግለጫው በመንግስት አካላት ሴቶች ላይ በግጭት ሳቢያ ለተፈጸሙ ጥቃቶች እውቅና ሊሰጥ እና ይቅርታ ሊጠይቅ ይገባል ሲልም ያክላል፡፡

ሴታዊት የፃታ ፍትህ ማህበር እና አጋሮቹ ባወጡት መግለጫ በጦርነቱ ሳቢያ ወሲባዊ ጥቃት የተፈጸመባቸው ተጠቂዎች እንደ አንድ ቡድን ተይዘው በሽግግር ፍትህ ሂደቱ ላይ ቀጥተኛ ተሳታፊ ሊሆኑ እና ጉዳዮቻቸው በልዩ ሁኔታ ሊያዝ ይገባል ሲልም በላከልን መግለጫ አስታውቋል፡፡

የሽግግር ፍትህ ረቂቅ ፖሊሲ በቅርቡ በሚኒስትሮች ምክር ቤት መፅደቁ የሚታወስ ነው፡፡

በአቤል ደጀኔ

ሚያዝያ 12 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply