ከቀናት በፊት በመተከል ዞን ድባጤ ወረዳ ንጹሃንን ያስጨፈጨፉ 4 አመራሮች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡ አሻራ ሚዲያ ህዳር፡-12/03/13/ዓ.ም ባህር ዳር አሁን በደረሰን መረጃ መሰረት ከአራቱ…

ከቀናት በፊት በመተከል ዞን ድባጤ ወረዳ ንጹሃንን ያስጨፈጨፉ 4 አመራሮች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡ አሻራ ሚዲያ ህዳር፡-12/03/13/ዓ.ም ባህር ዳር አሁን በደረሰን መረጃ መሰረት ከአራቱ አመራሮች እስከ ቀበሌው ሄደው ሽፍቶቹን ካደራጇቸው የድባጤ ወረዳ አመራሮች ውስጥ 3ቱ በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡ በቁጥጥር ስር የዋሉት አቶ ዝሆኔ ግራንዞ ፣አቶ ፍሬው ዝሌና፣ አቶ ሹፌር ወሲፕ መሆናቸው ነው የተገለጸው፡፡ አቶ ሹፌር ወሲፕ ማለት ከታች በምስሉ ላይ የምትመለከቱት ሲሆን የድባጤ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ፅ/ቤት ሲሆን ያምፕ ቀበሌ የነበሩ ጉምዞችን አደራጅቶ ህዝቡን ያስጨረሰ ነው። በተጨማሪ የሹፌር ወሲፕ ወላጅ አባት አቶ_ወሲፕ የተባለው ያምፕ ቀበሌ ላይ መትረየስ_ተኳሽ የነበረ ህዝቡን የጨረሰ ሲሆን ከመከላከያ በተተኮሰ ጥይት ተመቶ አሁን ቆስሎ ይገኛል ነው የተባለው። ያመለጡ እና በቁጥጥር ስር ያልዋሉ እንዳሉም ምንጫችን ገልጸዋል፡፡ አሁንም ድረስ አቶ መኩሪያው በተሃና የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ደበሊ በልጋፎ እስካሁን በቁጥጥር ስላልዋሉ መረጃ እያቃበሉ መከላከያው ላይ ጥቃት እንዲደርስ ብሎም ህዝቡ እንዲያልቅ እያደረጉ ይገኛል እሳካሁን የ3 መከላከያ ህይወት ቀጥፈዋል ተብሏል። ዘጋቢ፡-ጥላሁን ታምሩ

Source: Link to the Post

Leave a Reply