
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ውስጥ የተከሰተው ችግር መፈታቱ ከተነገረ ከሁለት ቀናት በኋላ ስምምነቱ በአንደኛው ወገን በድጋሚ መጣሱን የቤተክርስቲያኗ አባቶች ገለጹ። የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ አቡነ አብርሃም እና የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊ የሆኑት አቡነ ጴጥሮስ አርብ የካቲት 10/2015 ዓ.ም. በሰጡት መግለጫ ላይ፣ በስምምነቱ ወደ ቤተክርስቲያኗ እንዲመለሱ የተወሰነላቸው አባቶች በድጋሚ ጥሰት መፈጸማቸውን ተናግረዋል።
Source: Link to the Post