You are currently viewing ከበለው ጅጋንፎይ ወረዳ በማንነታቸው ምክንያት የተፈናቀሉ በሽህ የሚቆጠሩ አማራዎችን ቅሬታ ለፌደራል መንግስት የተለያዩ ተቋማት ለማሰማት የመጡ ከ40 በላይ ተጎጅዎች ሰሚ ማጣታቸውን ገለፁ። አ…

ከበለው ጅጋንፎይ ወረዳ በማንነታቸው ምክንያት የተፈናቀሉ በሽህ የሚቆጠሩ አማራዎችን ቅሬታ ለፌደራል መንግስት የተለያዩ ተቋማት ለማሰማት የመጡ ከ40 በላይ ተጎጅዎች ሰሚ ማጣታቸውን ገለፁ። አ…

ከበለው ጅጋንፎይ ወረዳ በማንነታቸው ምክንያት የተፈናቀሉ በሽህ የሚቆጠሩ አማራዎችን ቅሬታ ለፌደራል መንግስት የተለያዩ ተቋማት ለማሰማት የመጡ ከ40 በላይ ተጎጅዎች ሰሚ ማጣታቸውን ገለፁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጳጉሜ 5 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ከማሼ ዞን በለው ጅጋንፎይ ወረዳ ሀሮ ደዴሳ ቀበሌ ተፈናቅለው መንግስታዊ እውቅና እና ድጋፍ ተነፈገን ያሉ በሽህ የሚቆጠሩ አማራዎችን የወከሉ ከ40 በላይ ተጎጅዎች አዲስ አበባ ገብተዋል። እኒህ አዲስ አበባ የገቡ የተፈናቃይ ተወካዮች ጳጉሜ 3 ቀን 2013 ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ጭምር ደብዳቤ በፖስታ ማስገባታቸውን አስታውቀዋል። የፌደራል አደጋ መከላከልና ስጋት ኮሚሽን ጥያቄያችን ተቀብሎ በአግባቡ ሊያስተናግደን አልፈቀደም፤ አገልግሎት አሰጣጡ ላይ ከፍተኛ ቅሬታ አድሮብናል ሲሉ ገልፀዋል። በጉምዝ ታጣቂዎች ጉህዴን ከተፈናቀሉበት ከሀምሌ 8 ቀን 2013 ጀምሮ ለሶስተኛ ጊዜ ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ለፌደራል ተቋማት አስቸኳይ የሰብአዊ ድጋፍ እንዲደረግልንና ሌሎች ተያያዥ ጥያቄዎች እንዲፈቱልን የጠየቅን ቢሆንም በሚያሳዝን መልኩ ከቃላት ያለፈ በተግባር አንዳች ተገቢ እና ተስፋ ሰጭ መልስ አላገኘንም ብለዋል። ለሰላም ሚኒስትር፣ለመከላከያ ሚኒስትር፣ለግብርና እና ለፍትህ ሚኒስትር ደብዳቤ ማስገባታቸውን አውስተዋል። ከጥይት በተጨማሪ ሰዉን በርሃብ እንዳናጣ የሁላችንን ቀና ርብርብ ይጠይቀናል ያሉት ተወካዮቹ በትንሹ ከ7,500 በላይ ወገኖች በሁለንተናዊ ችግር ላይ ናቸው ብለዋል። ቅሬታ አቅራቢዎች ከተፎካካሪ ፓርቲዎች መካከልም ፒያሳ ቴዎድሮስ አደባባይ አካባቢ በሚገኘው የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት መኢአድ ዋና ጽ/ቤት ተገኝተው እንዲታገልላቸው፣ ድምፅ እንዲሆናቸው ጠይቀዋል። አሚማ በስፍራው ተገኝተው በአማራዎች ላይ በመንግስታዊ መዋቅር በመታገዝ ጭምር ደረሰብን ያሉት በደል ምን እንደሆነ አነጋግሯል። ሙሉ ዝግጅቱን በአሚማ የዩቱብ አድራሻ ይጠብቁ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply