ከባህርዳሩ ስብሰባ ውሎ የደረሱን መረጃዎች ‼️ ታሕሳስ 27 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ዛሬ ባህርዳር በክልሉ ባሉ ሁሉም ወረዳዎችና ዞኖች ኮር አመራሩና የክልሉ ጠቅላላ አመራር…

ከባህርዳሩ ስብሰባ ውሎ የደረሱን መረጃዎች ‼️ ታሕሳስ 27 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ዛሬ ባህርዳር በክልሉ ባሉ ሁሉም ወረዳዎችና ዞኖች ኮር አመራሩና የክልሉ ጠቅላላ አመራር የተጠራው ከወረዳዎች ሶስት ሶስት ዋና ዋና አመራሮች በስብሰባው ላይ እንዲሳተፉ ተገኝተዋል ። ስብሰባውን የሚመሩት የኦሮሞ ክልል ፕሬዚዳንት ሽመልስ አብዲሳ፣የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ይልቃል ከፍለ እና አቶ አደም ፋራህ ናቸው ። የህ/ተ ምክርቤት አፈጉባኤ ታገሰ ጫፎና የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ አገኘው ተሻገር በታዛቢነት በስብሰባው ላይ ተገኝተዋል። የስብሰባው አጀንዳ በአገሪቱ ባለው ወቅታዊ ሁኔታ አመራሩ ጥያቄ እንዲያነሳ ነበር። አመራሩም የሚከተሉትን ጥያቄዎች አንስቷል❓ 1)እናንተ አገር መምራት አትችሉም። እንደ ኃይለማሪያም መልቀቂያ አስገባ ህዝባችንን አታስጨርስ ( ሽመልስን) 2) የአአ ባንዲራ መስቀል ምን ማለት ነው? አሁን የአአ አመራር የእናንተን ጉዳይ አስፈፃሚ አመራር በአማራ ታርጋ ብቻ ነው የምትሾሙት፤ 3) የጎጃም አአ መንገድና የወሎ ሸዋ አአ መንገድ የምትዘጋው የኦሮሞ ሪፐብሊክ አጀንዳ ነው ። አይሳካም አቁሙ፤ 4) ትግራይ ከአማራ ዘርፎ የወሰደውን ንብረት ሳናስመልስ የምን ስምምነት ነው። እናንተ ትግራይን እያቋቋማችሁ ነው። የአማራና አፋር የወደመ ንብረት ምንም አይመስላችሁም❓ 5) አቶ አገኘው የወልቃይትና ራያ ጉዳይ የተዘጋ ነው ስትል ሽጉጥ እጠጣለሁ ስትል ከርመህ አሁን ፌደሬሽን ስትሆን ምንነ ው ካድክ❓ 6) በወለጋ የሚታረደው አማራ ተጠያቂው ማን ነው? ካልቻልክ ልቀቅ የሚልና በርካታ ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን ከመድረክ ምላሽ ይጠበቃል ሲል ሹክ ብሎናል። “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply