ከባህርዳር – ላሊበላ የገናን በዓል ለማክበር  ለመጀመሪያ  ጊዜ  የእግር ጉዞ ተጀመረ፡፡ ጉዞው 13 ቀናትን ይፈጃል፡፡ 310 ኪ.ሜም ይሸፍናል፡፡  (አሻራ ታህሳስ 18፣ 2013 ዓ.ም)…

ከባህርዳር – ላሊበላ የገናን በዓል ለማክበር ለመጀመሪያ ጊዜ የእግር ጉዞ ተጀመረ፡፡ ጉዞው 13 ቀናትን ይፈጃል፡፡ 310 ኪ.ሜም ይሸፍናል፡፡ (አሻራ ታህሳስ 18፣ 2013 ዓ.ም)…

ከባህርዳር – ላሊበላ የገናን በዓል ለማክበር ለመጀመሪያ ጊዜ የእግር ጉዞ ተጀመረ፡፡ ጉዞው 13 ቀናትን ይፈጃል፡፡ 310 ኪ.ሜም ይሸፍናል፡፡ (አሻራ ታህሳስ 18፣ 2013 ዓ.ም) መነሻቸውን ከባህርዳር ያደረጉ አምስት ተጓዦች ወደ ላሊበላ የገናን በዓል ለማክበር የእግር ጉዞ ጀምረዋል፡፡ ጉዞው ተራረ እና ሸለቆውን አቆራርጦ 310 ኪሜ የሚሸፍን ሲሆን፣ ታህሳስ 28 እንደሚደርሱም ይጠብቃል፡፡ ከአምስቱ ተጓዦች መካከል ሶስቱ መንገዱን አጋምሰው በተሽከርካሪ ላሊበላ ለመግባት ወጥነዋል፡፡ ሁለቱ ግን በእግራቸው ቀጥታ ከባህርዳር ላሊበላ እንደሚገቡ አረጋግጠዋል፡፡ ከአዲስ አበባ አድዋ ከአንድ ሺ ኪሎሜትር በላይ ርቀት ተጉዘው በወራት ጉዞ አድዋን በሶሎዳ ተራራ የሚያከብሩ ወጣቶች እንዳሉ ይታወቃል፡፡… ይህ ከባህርዳር የተጀመረው ጉዞም የአድዋ ተጓዦችን አርአያነት ወስዷል፡፡ የገና በዓል ታህሳስ 29 በላሊበላ ሚሊየኖች በታደሙበት የሚከበርበት ሲሆን፣ በዓሉ የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ይዘከርበታል፡፡ ንጉስ ላሊበላ፣ ክርስቲያኖች ከኢትዮጵያ ወደ እስራኤል (ኢየሩሳሌም) ለስድስት ወር ተጉዘው የልደት በዓልን ያከብሩ ነበር፡፡ ንጉስ ላሊበላ ዳግማዊ ኢየሩሳሌምን በሮሃ ስለሰሩ ጉዞው ወደ ላሊበላ ሆኗል፡፡ ላሊበላ በዓለማችን ካሉ ዘጠኝ አስደናቂ ኪነህንፃዎች መካከል አንዱ ሲሆን፣ ከዘጠኝ መቶ ዓመት ዕድሜ በላይ አለው፡፡ አሻራ ሚዲያ የላሊበላን ጉዞ በተመለከተ የተጠናከረ የቪዲዮ መረጃ ይዞ ይመለሳል፡፡ ከአሻራ አይጥፉ!!

Source: Link to the Post

Leave a Reply