# ከባልደራስ ለእውነተኛና ዲሞክራሲ ፓርቲ የተሰጠ አስቸኳይ መግለጫ!! #በፓርቲያችን አባላት ላይ የሚደርሰው የሀሰት ውንጀላ ባስቸኳይ ይቁም!! ሰ.ሜሪካ :- ሐምሌ 28/2014 ዓ.ም……

# ከባልደራስ ለእውነተኛና ዲሞክራሲ ፓርቲ የተሰጠ አስቸኳይ መግለጫ!! #በፓርቲያችን አባላት ላይ የሚደርሰው የሀሰት ውንጀላ ባስቸኳይ ይቁም!! ሰ.ሜሪካ :- ሐምሌ 28/2014 ዓ.ም… አሻራ ሚዲያ ተረኛው ኦሕዴድ-ብልፅግና በባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) አመራሮችና አባላት ላይ እያደረሰ ያለው መጠነ ሰፊ እስር፣ ወከባ እና የስም ማጥፋት እንቅስቃሴ ዛሬም በስፋት ቀጥሏል። በዚህ ሳቢያ የፓርቲውን ከፍተኛ አመራር አቶ ስንታየሁ ቸኮልን ጨምሮ ሌሎች አባሎቻችን አሁንም በሕገ ወጥ እስር ላይ ይገኛሉ። ይህ አልበቃ ብሎ በወ/ሮ አዳነች አቤቤ የሚመራው የአዲስ አበባ መስተዳድር ትናንት አመሻሹን በፓርቲያችን የአመራር አባል ወ/ሪት አስካለ ደምሌ፣ በእስር ላይ በሚገኘው የፓርቲው ዘጋቢ ወግደረስ ጤናው፣ በድርጅታችን አባል ወጣት ብሩክ ጫኔ እና በፓርቲያችን አባል ወጣት ሽባባው ዘውዱ ስም የሀሰት መታወቂያ ሰርቶ ሲያበቃ በነዚህ አባላቶቻችን ስም የሰራውን የሀሰት መታወቂያ በመረጃ ቋቱ ላይ ለጥፎ የአባላቶቻችንን ስም እያጠፋና እያወናጀለ ይገኛል። እነዚህ አባላቶቻችን ህጋዊ የመኖሪያ ማረጋገጫ ያላቸው ናቸው። ከተማ አስተዳደሩ ከነዚህ የባልደራስ አባላት በተጨማሪ የአማራ ሕዝባዊ ሃይል (ፋኖ) መሪ የአርበኛ ዘመነ ካሤን ፎቶ ግራፍ ተጠቅሞ ሌላ ሀሰተኛ የኗሪነት መታወቂያም ይፋ አድርጓል። ድርጊቱ ንፁህ የሆኑትን የፓርቲችንን አባላት እና ፋኖን ከወንጀል ድርጊቶች ጋር ጡት የማጣባት ሙከራ እንደሆነ እንረዳለን።በመሆኑም፦ 1. የአዲስ አበባ ኗሪ ብሎም መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ይህንን የመስተዳድሩን ርካሸ፣ ለፖለቲካ ሂሳብ የማይመጥን ከንቱ ፕሮፖጋንዳ ከቁብ ሳይቆጥርና ሳይደናገር እንደ ከዚህ ቀደሙ የዚህን ውንጀላ ሻጥር የበለጠ በአንክሮ እንዲያጤነውና በጽናት እንዲቃወመው እናሳስባለን። 2. ከተማ መስተዳድሩ ይፋ ያደረገውን ሀሰተኛ መረጃ ከማሰራጫ ቋቶቹ ሁሉ እንዲያነሳ እና ይቅርታ እንዲጠይቅ እንጠይቃለን። 3. የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ድርጊቱን በቅርበት እንዲከታተል እና የራሱን ሚዛናዊ ርምጃ እንዲወስድ እንጠይቃለን። 4. መንግሥታዊ ያልሆኑ የሕግና ፍትሕ የሙያ ማህበራት፣ የዴሞክራሲ ተቋማት፣ መገናኛ ብዙሃን እና ሌሎች መሰል ተቋማት የራሳቸውን ምርመራ በማድረግ እውነቱን ለሕዝብ እንዲያሳውቁ እንጠይቃለን። 5. መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የዚህን መንግስት አደገኛ አካሄዶች እየተከታተለ ትግሉን እንዲቀጥል እንጠይቃለን። የአማራ ሕዝብ በቁርጥ ቀን ልጆቹ፤ በፋኖዎች ላይ የሚደረገውን እኩይ ዘመቻ በአንክሮ እንዲከታተል እና ልጆቹን ከጥቃት እንዲጠብቅ እናሳስባለን። በመጨረሻም ባልደራን ይህ ትንኮሳ ቅንጣት ሳይበግረው ትግሉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ይገልፃል። የከተማችን ብሎም የሀገራችን ችግሮች ውሎ እያደር በእጅጉ እየተባባሰ ስለመጣ መላው ደጋፊዎቻችን አባላት እና በየደረጃው ያላችሁ አመራሮች ለተሻለ ትግል እንድትነሱ ጥሪያችንን እናቀርባለን! ድል ለኢትዮጵያ! ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ሐምሌ 28 ቀን 2014 ዓ.ም. አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply