ከባሕር ዳር – ጋሸና – አላማጣ የተዘረጋው መስመር በመበጠሱ ኃይል መቋረጡን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ።

ባሕር ዳር: የካቲት 26/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ከባሕር ዳር – ደብረታቦር – ንፋስ መውጫ – ጋሸና – አላማጣ የተዘረጋው ባለ 230 ኪሎ ቮልት የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር በመበጠሱ በአካባቢዎቹ ኃይል መቋረጡን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል። በተቋሙ የማስተላለፊያ መስመሮች እና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ኦፕሬሽን ዘርፍ የሰሜን ምዕራብ ሪጅን የኦፕሬሽን እና ጥገና መምሪያ ዳይሬክተር ውበት አቤ ዛሬ ረፋድ ላይ […]

Source: Link to the Post

This Post Has One Comment

  1. Tesfa

    ህዝብን ለመከራና ለስቃይ እየዳረጉ ነጻ እናወጣሃለን ማለት እብደት መሆኑን አመላካች መንገዶች ብዙ ቢሆኑም የሚሰማ ግን የለም። ማቅራራት ነው። ከበሮ እየተደለቀለትና ክራር እየተከረከረለት በደመ ነፍስ ታግሎ በደመ ነፍስ ለሞተው ማስታወሻ የለውም። ወይም ያዙኝ ልቀቁኝ በማለት ጊዜአዊ ድል አገኘሁ ብሎ ለሚፈራገጠውና ከደስታው የተነሳ ወደ ሰማይ ጥይት እያንጣጣ በተኮሰው ጥይት ናላው ተቦድሶ ወይም ሌላውን ለሞት የዳረገው የእብድ ስብስብ ሁሉ ለሃገር ለወገን የሚያስብ አይደለም። ሲጀመር ጦርነት የመጨረሻ የሰው ልጅ የስቃይ ቋት ነው። በሃገራችን ከጥንት ጀምሮ ያየነው ይህኑ ነው። የጀርመኑ ሂትለር ንጽህ ዘር በሚል ፈሊጥ ስንቱን አውድሞ ሃገሩን አጥፍቶ እሱና መሰሎችም የመከኑት ምንም ፍሬ ሳያስገኙ ነው። ዝንተ ዓለም የሃይል ማመንጫዎችን የህክምና ተቋሞችን፤ ባንክ፤ የትምህርት ተቋማትን እየዘረፉና እያዘረፉ አልፎ ተርፎም እያወደሙ ለሃገር ነው፤ ለዚህኛው ብሄር ነው መባሉ የውስልትና ውስልትና መሆኑን ያለፈው የሻቢያና የወያኔ ታሪክ ቁልጭ አርጎ ያሳያል። ይህ የኩኩሉ ነጋ አልነጋም የልጆች ጫወታ እልፎችን ለመከራ እየዳረገ ጥቂቶች የሚናጥጡበት ሁኔታ መፍጠሩ ዛሬ የተጀመረ አይደለም።
    የአማራ ህዝብ ከወያኔ የእድሜ ልክ መከራ ወጣሁ ሲል አሁን ደግሞ በብልጽግናና በታጣቂ ሃይሎች ፍትጊያ የሚሞተው ከሞት የተረፈው አርሶ የሚያበላውና የሚበላው የዋሁ ገበሬ ነው። ትንሽ የሰላም ጭላንጭል ታዬ ሲባል ሌላ ገመናና ሃበሳ የሚጠበሰው ይህ ህዝብ መቼ ይሆን እፎይ የሚለው? ፋኖ ከተማ ያዘ፤ ፋኖ እንዲህ አደረገ ይላል ወሬ አናፋሹ፤ መከላከያ ይህን ሰራ፤ በድሮን ደበደበ፤ ቤ/ክርስቲያንና መስጊድ አቃጠለ ወዘተ ክሱ ይቆለላል በሁለቱም ወገኖች – እውነቱ ግን መከራውን የሚያደርሱት በጋራ ነው። ከተማን ለጥቂት ሰአታት መቆጣጠርና ያለ የሌለውን በውዞ መውጣት ለአማራ ህዝብ መቆም አይደለም። የሚገድለው አማራ የሞተው አማራ። በወረፋው ደግሞ መከላከያ አንተ እንዲህ ነህ አንቺ እንዲያ ነሽ ብሎ እንበለ ፍርድ መረሸኑ ከደርጉ ጊዜና ዘመን አይሻልም። በሁለቱም ሃይሎች ጉዳት የሚደርስበት የአማራ ህዝብ ነው። አሁን ደግሞ ይባስ ተብሎ የመብራት ማስተላለፊያ ገመዶችንና ሌሎች አባሪ ነገሮችን ማውደም ተጀመረ። ማብቂያው የቱ ላይ ነው? በዚህ ሁሉ እልቂትና ኋላ መቅረት ደስ የሚለው ማን ነው? የኦሮሞ የፓለቲካ አክራሪዎችና ወያኔ ፈንጠዝያውን አይችሉትም። የአማራ የትምህርት ተቋም እንዲዳከም፤ ሴቶች እንዳይወልድ፤ ሊያስቡ የሚችሉ ምሁራንን በየሰበቡ እያፈነ ጉድጓድ የከተተው ወያኔን አሁን በከፋ መልኩ በብልጽግና ተተክቷል። ዛሬ ላይ ማን ነው እስርቤት ያለው? ወንጀላቸውስ ምንድን ነው? ለምንስ ፍርድ ቤት አይቀርቡም? ይህ የአምባ ገነኖች አሰራር ሁሉን እውር የሚያድርግ በመሆኑ አሁን በአማራ ላይ የምናየው እሳት ሌላውንም ሊያዳርስ ይችላል። ግዕዙ እንዲህ ይላል “እስከ ማዕዜኑ” እስከ መቼ ድረስ ነው የህዝባችን መከራና ረሃብ የማይታየን? እውነት ነው የቀንድ ከብትን እንደ ዓሳ አሰግራለሁ ከሚሉ የፓለቲካ ወስላቶች ጋር ሰለ ሰላም መነጋገር ከባድ ነው። ግን ጊዜው ሆኖ ይሆን ይህ ሁሉ ሃበሳ በህዝባችን ላይ የሚደርሰው? ተፋላሚዎቹ አንተ ነህ አንቺ ነሽ ሲባባሉ ጊዜው ሮጠ። ዓለም ጥሎን ገሰገሰ። ተሰማ እሸቴ ከረጅም ዘመን በፊት ከጻፉት አንድ ስንኝ ልዋስና ይብቃኝ
    ለነዚህ ፋሽስቶች መድሃኒት ስጧቸው
    የሚያስቀምጥ ሳይሆን የሚያስመልሳቸው።

Leave a Reply