ከባድ የአዕምሮ ህመም (ስኪዞፈሪኒያ) ምንድን ነው?

ስኪዞፈሪኒያ የአማርኛ ፍቺ ባይኖረውም በዋናነት ከባድ የሆነ የአስተሳሰብ፣ የሀሳብ መዛባት መሆኑን በዘርፉ ባለሞያዎች አቻ ፍቺ ይሰጠዋል፡፡
ስኪዞፈሪኒያ ከባድ የሚባል የሚባል የአእምሮ ህመም መሆኑ ይነገራል፡፡

ህመሙ ወጣቶችን የሚያጠቃ እና ሲሆን፤ አልፎ አልፎም ከ20 ዓመት በላች ያሉ ሰዎችን ያጠቃል ተብሏል፡፡ በዚህ ህመም የሚሰቃዩ ሰዎች የህክምና ክትትል ካደረጉ ከህመሙ የሚድኑበት ሁኔታ መኖሩ ተመላክቷል፡፡

ከ360 በላይ የአይምሮ ህመሞች መኖራቸውን የነገሩን የአእምሮ ሀኪም ስፔሻሊት የሆኑት ዶክተር እስጢፋኖስ እንዳላማው፤ ከእውነታው አለም ማፈንገጥ (ሳይኮሲስ) አንዱ ነው ብለዋል፡፡ እውነታን በተዛነፈ መልኩ መረዳት እና የሌለ ወይም ያልተፈጠረ ነገርን እንደተፈጠረ ማሰብ ማለት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ከሳይኮሲስ የአይምሮ ህመም ውስጥ አንዱ ስኪዞፈርኒያ ነው ብለውናል፡፡ የዶፓሚን ስርአት መዛባት በዋናነት ተጠቃሽ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

መነሻ ምክንያት፤

• በቤተሰብ ይህ ህመም ከነበረ
• አደንዛዣ እጾንችን መጠቀም በተለይም ካናቢስ በ6 እጥፍ ተጋላጭ ያደርጋል
• ስነ ልቢናዊ እና ማህበራዊ ጉዩዎች ህመሙን አባባሽ ናቸው ተብሏል፡፡
• በህመሙ የሚሰቃዩ ሰዎች ላይ የሚስተዋሉ ምልክቶች
• ምክንያት በሌለው ጉዳይ ላይ መጠራጠር እና መጨነቅ
• ሌሎችን ሊያጋራ የማይችሉ ጉዮች ላይ እምነትን የማሳደር ሁኔታ ሊስተዋልባቸው እንደሚችል ተጠቁሟል፡፡
• ያለሆኑ ነገሮችን እንደሆኑ እና የተከናወኑ አድርጎ ማሰብ
• በነባራዊ አለም ላይ የማሆኑ ነገሮችን እንደሚሆኑ ማሰብ
• የተለየ ጸጋ እንዳለው ማሰብ
• እራስን አደጋ ላይ ማጋለጥ
• ለሌሎች የማይታይ፣ የማይሰማን ማየት እና መስማት እና ማሽተት
• በንግግር መሃል ከሀሳብ መውጣት እንዲሁም ከማህበራዊ ህይወት እራስን ማግለል ይስተዋላል ተብሏል፡፡

ህክምናው፤

የሚተዋሉ ምልክቶች እስከ 6 ወራት መቆየት እንዳለባቸው የገለጹ ባለሞያው፤ ከ6 ወራት ውስጥ ለ አንድ ወር ያህል በጹኑ የሚታመሙ ይሆናል ብለዋል፡፡

ህክምናው በወራቶች ላይ የተመሰረተ ሲሆን፤ በቅድሚያ ምልክቶችን በማጥፋት እና በአንቲ ሳይኮቲክ መድሃት የተዛባውን የዶፓሚን ስርዓ-ት- ማስተካሰል እንደሆነ ተነግሯል፡፡

ስኪዞፈሪኒያ ከባድ የአይምሮ ህመም በመሆኑ የሰዎችን አስተሳሰብ ፣ ስሜት እና ባህሪ ላይ ከፍተኛ የሆነ ተጽእኖ እንደሚያሳድር ተነግሯል፡፡

ህመሙን የሚያባብሱ እና እንዲያገረሽ የሚያደርጉ ጉዳዮች

• የስከዞፈርኒያን መድሃኒት በድንገት ማቆም
• አደንዛዥ እጾችን መጠቀም
• አካላዊ ህመሞችን ሳይታከሙ ሲቀሩ ያደርጋል ተብሏል፡፡

ስለ ስኮዞፈሪኒያ የአይምሮ ህመም ምንነት ፣ በተማማሚ ላይ የሚተዋሉ ምልክቶች እና ህመሙ ላለባቸው ሰዎች ምን አይነት እንክብካቤት መስጠጥት እንደሚቻል ለህብረተሰቡ ማስተማር እና ግንዛቤን መፍጠር አስፈላጊ መሆኑ ተጠቁዋል፡፡

በእሌኒ ግዛቸው

ሚያዝያ 03 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply