ከባድ የእሳት አደጋ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ።

ዛሬ ጥር 27 ቀን 2016 ዓ.ም በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ አምስት ዮኒ ማስ የፕላስቲክ ፋብሪካ መጋዘን ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ ከባድ ጉዳት ደርሷል።

የእሳት አደጋዉን ለመቆጣጠር አምስት የአደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪ ከሰላሳ አራት የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች የተሰማሩ ሲሆን የእሳት አደጋዉ ወደፋብሪካዉ ማሽነሪዎች ተዛምቶ ተጨማሪ ጉዳት ሳያደርስ መቆጣጠር የተቻለ ሲሆን በአደጋዉ በሰዉ ላይ የደረሰ ጉዳት የለም።

በሌላ በኩል ቅዳሜ በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ ሸዋ ዳቦ አካባቢ ፣ በአዲስ ከተማ ወረዳ ሰባት ጎጃም በረንዳ አካባቢ ፣ የካ ወረዳ ስድስት ካሳንቺስ ፣ በልደታ ወረዳ ሰባት በአምስት የንግድ ሱቆች ላይ ተቃጥለዋል።

እሁድ አራት የእሳት አደጋዎች ተክለ ሀይማኖት በንግድ ቤቶች በመኖሪያ ቤቶች ላይ የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ጉዳት ሲደርስ ሶስት ሰዎች ላይ ቀላል ጉዳት ደርሷል።

እንዲሁም በሸገር ከተማ ሰበታ ክፍለ ከተማ በጤና ጣቢያ ላይ በአጋጠመ የእሳት አደጋ ጉዳት ደርሷል።

የኮሚሽኑ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች የእሳት አደጋዎቹ ተስፋፍተዉ ተጨማሪ ጉዳት ሳያደርሱ መቆጣጠር ተችሏል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል
ጥር 27 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply