You are currently viewing ከባ/ዳር ተወስደው በመተማ ወረዳ በእስር ላይ የሚገኙት እነ ፋኖ ጥላሁን አበጀ፣ “የአደራ እስረኞቹ” የዋስትና መብታቸው ተጠብቆ ከእስር እንዲፈቱ ጠየቁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ    ታህሳ…

ከባ/ዳር ተወስደው በመተማ ወረዳ በእስር ላይ የሚገኙት እነ ፋኖ ጥላሁን አበጀ፣ “የአደራ እስረኞቹ” የዋስትና መብታቸው ተጠብቆ ከእስር እንዲፈቱ ጠየቁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳ…

ከባ/ዳር ተወስደው በመተማ ወረዳ በእስር ላይ የሚገኙት እነ ፋኖ ጥላሁን አበጀ፣ “የአደራ እስረኞቹ” የዋስትና መብታቸው ተጠብቆ ከእስር እንዲፈቱ ጠየቁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 21 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ ከባ/ዳር ታፍነው ወደ ምዕራብ ጎንደር ዞን ገንዳውሃ ተወስደው በአደራ እስረኛነት ተይዘው የሚገኙት እነ ፋኖ ጥላሁን አበጀ፣ አምስቱ ወጣቶች ዛሬ ታህሳስ 21/2015 ፍ/ቤት ይቀርባሉ። ፋኖ ጥላሁን አበጀ፣ ናትናኤል ዘነበ፣ ኃ/ማርያም ክብረት፣ ጌትነት እሸቱ እና መታገስ ጸጋው ፍ/ቤት የሚቀርቡትም:_ 1) ታህሳስ 21/215 ከቀኑ 8 ሰዓት ላይ በመተማ ወረዳ ፍ/ቤት የሚቀርቡት ወጣቶቹ ታህሳስ 20/2015 የዋስትና መብት ተጠብቆላቸው ከእስር እንዲፈቱ መጠየቃቸውን ተከትሎ ነው። በጉዳዩ ላይ የዐቃቢ ህግ አስተያዬት ከተሰማ በኋላ ዳኞች ውሳኔ የሚሰጡ ይሆናል። 2) ታህሳስ 21/2015 ረፋድ ላይ ደግሞ ተጥረጥረዋል ከተባሉበት ከሽብር ወንጀል ጋር በተያያዘ በምዕራብ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ቀርበዋ ዐቃቢ ህግ ሌላ ችሎት ላይ ነው በመባሉ ከቀኑ 9 ሰዓት ተቀጥረዋል። የመተማ ወረዳ ፖሊስ እና የዞኑ ፖሊስ የአደራ እስረኞች ስለሆኑ የእኔ ግንኙነት የሚሆነው አደራ ከሰጠኝ ጋር እንጅ ከሌላ አካል ጋር ሊሆን አይችልም በማለት ለሁለተኛ ጊዜ እስረኞችን ይዘው እንዲቀርቡ በወረዳ ፍ/ቤት የተሰጣቸውን ትዕዛዝ ሳያከብሩ ቀርተዋል። ለመሆኑ የአደራ እስረኝነታቸው እስከ መቼ ሊሆን ነው? ህጉስ ይፈቅዳል ወይ የሚሉ ጥያቄዎች እየተነሱ ነው። አደራ ሰጭው ወጣቶችን በግፍ አስሮ በማስቀመጥ ፈጣን ፍትህ እንዳያገኙ ቢያደርግስ የአደራ እስረኞች ስለሆኑ በሚል አደራ ተቀባዩ አስሮ የመክረም መብት አለው ወይ? እስከ መቼ አስሮ ሊቆይ ይችላል? ስንል ጠበቃ ሰለሞን ገዛኽኝን አነጋግረናል። የስነ ስርዓት ህጉም የአደራ እስረኛ የሚል አሰራርን አያውቀውም፤ በተለይ በአማራ የተለያዩ አካባቢዎች እየተለመደ የመጣ ህጋዊነት የጎደለው አሰራር ስለመሆኑ ነው በጉዳዩ ላይ አሚማ ያነጋገረው ጠበቃ ሰለሞን ገዛኽኝ የተናገረው። ማንም ሰው በቁጥጥር ስር ያዋለውን ተጠርጣሪ በ48 ሰዓት የማቅረብ ግዴታ ያለበት በመሆኑ የአደራ እስረኛ በሚል እስረኞችን የሚያንገላቱ እና የፍትህ ሂደቱን የሚያበላሹ አደራ ሰጭም ሆነ አደራ ተቀባይ ሁለቱም ከተሰሱ በህግ ፊት የሚጠየቁበት እና የሚቀጡበት እድል እንዳለ ተገልጧል። ሁኔታውን ያወቁ ወይም አቤቱታ የደረሳቸው የህግ አካላት የአደራ እስረኛ በሚል ፍትህን እያዛቡ ያሉ አካላትን በዝምታ ሊመለከቱ እንደማይችሉ ተመላክቷል። በመሆኑም የመተማ ወረዳ ፍ/ቤት የአደራ እስረኛ በሚል ስም የፍትህ ሂደቱን እያዛቡ ባሉ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ ሊወስድ እንደሚችልም ለአሚማ የደረሱ መረጃዎች ያመለክታሉ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply