ከቤተ-አማራ ወሎ ዓለም አቀፍ ማህበር (ቤወአማ) በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የተሰጠ መግለጫ:- ታሕሳስ 3 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ባህርዳር በሕወሃት(ወያኔ) ተነድፎ በኦነግ ደጋፊነት በመ…

ከቤተ-አማራ ወሎ ዓለም አቀፍ ማህበር (ቤወአማ) በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የተሰጠ መግለጫ:- ታሕሳስ 3 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ባህርዳር በሕወሃት(ወያኔ) ተነድፎ በኦነግ ደጋፊነት በመላው የኢትዮጵያ ግዛት የተዘረጋው፤ በመለስና ዓብይ መሪነት የተተገበረው አንደዚሁም በመተግበር ላይ ያለው የዘር ፖለቲካ የህዝባችንን በፍቅር አብሮ የመኖር ዋስትና እደጋ ውስጥ ከመክተቱም በላይ ንፁሀን የአማራ ተወላጆች በግፍ እየተጨፈጨፉና እየተገደሉበት ይገኛል። ይህንንም ስንል በተለይ የአማራው ሕዝብ የዚህ አስከፊና አደገኛ የፖለቲካ ሸፍጥ ግንባር ቀደም ተጠቂና ሰለባ ሆኖ ይገኛል። አማራው ለኢትዮጵያ አገራችን ክብርና ነፃነት ፤ ደሙን አፍስሶ አጥንቱን ከስክሶ በዓለም ደረጃ ሰንደቆን ከፍ እንዳላደረገ ዛሬ ግን በእናት ጡት ነካሾች ከቀየው እንዲፈናቀል፣ እንዲታሰር፤ ንብረቱ እንዲዘረፍ፣ የመገልገያና የልማት ተቋማቶቹን ሆን ተብሎ እንዲወድሙና ይህም ታልቅ ሕዝብ እንደ አዉሬ እየታደነ እንዲገደል የፖለቲካውን ርከን በጨበጡት ነፍሰ ገዳይ የዘር ፖለቲከኞች ፍርድ ተበይኖበታል። በአሁኑ ሰዓት ሕዝባችን ህልውናውና መብቱ በየትኛውም አቅጣጫ አጣብቂኝ ውስጥ መግባቱ ለማንም ግልጽ ነው። የዚህ አስከፊ የዘር ጭፍጨፋና የሴራ ፖለቲካ መዳረሻ ፡ በአንድ በኩል የአማራን ህዝብ ከኢትዮጵያ ለመነጠልና ታሪካዊ ስፍራውን ለማስለቀቅ ሆን ተብሎ የተሸረበ የጥፋት እርምጃ ሲሆን፣ በሌላ በኩል ደግሞ አማራን አንገቱን በማስደፋት ከሃገሪቱ የፖለትካ ተጋሪነት በማስወገድ በእድገትም ይሁን በመብት እኩል ድርሻና እጣፈንታ እንዳይኖረው ፤ በተጨማሪም ከነበረበት ጠንካራ የስነ – ልቦና አቅም በማውረድ ተንበርክኮ የሚገዛ ሕዝብ ለማድረግ የተወጠን ሴራ ነው። በአሁኑ ሰዓት የአማራ ሕዝብ እጣ ፈንታ ዋልታ ረገጥ በሆኑ የኦሮሞና የትግሬ ጽንፈኞችና አክራሪ ጎጠኞች እጅና መዳፍ ሥር በመውደቁ፤ በመሠረታተና የሕይወት ዋጋ በከፈለላት አገራችን ኢትዮጵያ፤ እንደ አውሬ እየታደነ በግፍ የሚገደለው፣ የሚታሰረው፣ የሚሰደደውና የሚዘረፈው ዐማራ ሃገርም መንግሥትም አልባ ሆኖ ይታያል። በውሸትና በትርክት ላይ የተመሰረተው አጉራ ዘለል ፕሮፓጋንዳቸው ፈር ለቆ፣ ቂም ጠምቆ ፣በቀል ቋጥሮ አቅሙበፈቀደ መጠንና ባገኘው አጋጣሚ ጊዜ ሁሉ የጥፋት ክንዱን በማናለብኝነት በአማራ ሕዝብ ላይ በማንሳት ለዓመታት በአርባጉጉ፣ በባሌ፣ በአርሲ፣በሻሸመኔ፣ በሐረር፣ በጉርፈረድ፣ በመተከል እንዲሁም እስካሁን ደርስ በአማራ ደም በጨቀየዬችው የደም ምድር ወለጋ የተፈፀመውና እየተፈፀመ ያለው የዚሁ ሴራቸው ዋናና አወንታዊ ማስረጃ ነው። በአማራው ላይ ጅምላ የዘር ፍጅት እንዲደርስ፣ ከመኖሪያ ቀየው እንዲያፈናቅል፣ እናቶችና እህቶቹ እንዲደፈሩ፣ ንብረቱና ልማቱ እንዲወድም ሲወሰንበት፣ ወክለንሃል የሚሉት የአማራ ፖለቲከኞች አጋልጠውና አሳልፈው ለገዳዩና ለአረመኔው የዓብይ ኦሮሞ መንግስት እንደፍሪዳ ለመሰዋዕት አቅርበውታል። አማራው በእንኝህ በተንኮል የተመረዙ የፖለቲካ ሰዎች የተፈረደበት ግድያ ብቻ ሳይሆን በምጣኔ ሃብት አቅርቦትና ክምችት እንዲደኸይና እንዲደቅ፣ ለእርዛትም እንዲጋለጥ ጭምር ነው። አባቶቹ ደማቸውን አፍሰው አጥንታቸውን ከስክሰው አብረው ከሌሎች ቅን ኢትዮጵያዊያን አጋሮቻቸው ጋር በገነቧት አገርና በወለዱባትና እንዲሁም በዳሩባት ቀዬ በጭካኔና በግፍ ያለልክ እየተሰቃየና እየተገፋ ምጻተኛ እንዲሆን ተደርጓል አሁንም እየተደረገ ነው። በተለይም ደግሞ በአሁኑ ወቅት በአማራነቱ ልክ የለሽ ገፈትና ዘግናኝ ጭፍጨፋ እየደረሰበት የሚገኘው ሕዝባችን በወለጋ-ቄለም ሆረጉድሩ፣ በሸዋ ደራ፣ በራያ-ወሎ፣ በመተከል-አሶሳ፣ በአበርገሌ-ዋግ፣ በወልቃይት-ጠለምት አንዴ በጦርነት፣ አንዴ በዘር ፍጅትና ጭፍጨፋ ዘሩን የማጥፋት፣ የማሳሳት፣ የማቀንጨርና የመከለስ የጥፋት ዘመቻ በተቀነባበረና በተጠና መንገድ እየተካሂደ መሆኑ በጅጉ ያሳስበናል። አሁን ደግሞ ይህ አልበቃ ብሎ ለዚሁ የአማራ ሕዝብ ሌላ ስውር የጥፋት ድግስ በብልጽግና መንግሥት እና በትግራይ አሸባሪ ኃይላት በኩል ሲታቀድለትና ሲሰዘረጋለት እየተመለከትን ነው። በእርቅና የሰላም ስምምነት ሽፋን በአማራ ሕዝብ ሕልውና ላይ በመቆመርና በመደራደር የሕዝባችንን ሕልውና ለሌላ ለከፋ አራተኛ ዙር የጥፋት አደጋ ውስጥ ለመክተት ክወዲሁ ዝግጅቱ ተጠናቋል፣ በአማራ ሕዝብም ላይ የብልፅግና መንግስት አጥፊ የሆነውን ሰይፉን ለመምዘዝ ተቃርቧል። እኛም እንድ አማራ ሕዝብ ይህ የአማራውን ውክልን ያላካተተ ማንኛውም ስምምነት ፋይዳ የሌለው መሆኑን በዚሁ አጋጣሚ አስረግጠን ከመግለጻችን በተጨማሪ ስምምነቱ አማራን ባለማካተቱ አጥብቀን እንቃወማለን። ይህ ስምምነት ዋናወቹን ባለቤቶች አማራንና አፋርን ከማግለሉም ሌላ የጦርነቱ ቀጥተኛ ተጎጂዎችና ሰለባዎች ከስምምነት ሆን ተብሎ እንዲገለሉ መደረጉ በጅጉ አሳዝኖናል። በተጎዳኙም ስምምነቱ በዘላቂነት የአማራንም ሆነ የአገሪቱን ችግር ይፈታል ብለንም አናምንም። እንዲያውም የአማራን እና የአፋርን ሕዝብ ያገለለ ስምምነት በመሆኑ አማራውንም ሆነ አፋሩን ዳግም ለከፋ የዘር ፍጅትና ዘር ተኮር ጥፋት ተጋላጭ የሚያደርግ በመሆኑ በእጅጉ ያሳስበናል። ይህም የዓብይ መንግስት አካሄያድ ሆን ተብሎ ሃገሪቱን በሴራ የማዳከምና የዜጎች መብት በጉልበተኞችና አምባ ገነኖች እጅ እንዲወድቅ በር የሚከፍት ከመሆኑም በላይ፣ የሕግና ፍትሕ የበላይነት እንዳይከበር፤ የዜጎች መብት እንዲጣስ፣ ዲሞክራሲ እንዳይሰፍንና እንዳይተገበር አሉታዊ ሚናው ከፍተኛ እንደሆነ በዚሁ አጋጣሚ ልናሰምርበት እንገደዳለን። ሕዝባችንንም ሆነ ታላቋ ኢትዮጵያ አገራችንን ከዚህ አስከፊ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ቀውስ ለመታደግ እንደ አንድ የተገፋ የአማራ ሕዝብ አብሮ መቆምና ከዕውነታው ጋር ፊት ለፊት ለመጋፈጥ ግድ ይለናል፤ ይህም ስልታዊ የዘር ማጥፋትና ግድያ እስኪቆም ድረስ ትግልችን ይቀጥላል። ስለሆነም፦ 1. በማንኛውም የኢትዮጵያ ግዛት የሚገኙና በተለይም በኦሮሞ ክልል የሚኖሩ አማራዎች ላይ የሚደረገው አፈና፣ድብደባና ግድያ ብሎም የዘር ማጥፋት ወንጅል በአስቸኳይ እንዲቆም እንጠይቃለን። 2. በአሁኑ ወቅት የብልጽግና መንግሥትና ትህነግ እያካሄዱ ያሉት የአማራን ሕዝብ ያገለለ እርቅና ስምምነት በአማራ ሕዝብ ሕልውና እና መቃብር ላይ አዲስ የዘረኞች የጥፋት ውልና የሴራ ኪዳን የማደስ እርምጃ በመሆኑ፣ የአማራን ታሪካዊ ርስቶችና ይዞታዎች፣ መብትና ጥቅም አሳልፎ ለትህነግ በመስጠት የማደስ ሴራን አጥብቀን የምንቃወም ሲሆን ተቀባይነት የሌለው ታሪካዊ ስህተት መሆኑንም መግለጽ እንወዳለን። 3. በማንኛውም አማራ ነክ ጉዳይ አማራው የራሱ ቀጥተኛ ወኪሎች እንዲኖሩት ለማድረግ የሚደረገውን ጥረትና መግለጫዎች የምንደግፍ ሲሆን፣ በዚህ ረገድ በአማራው ዘንድ ተቀባይነት ያላቸውን መሪዎችና ወኪሎች በማንኛዉም አማራን በሚመለከቱ ስምምነቶች ሁሉ አሁን በወቅቱ ያለው የብልጽገና መንግስት ያለምንም ጥያቄ ወኪሎቹን ተቀብሎ የስምምነቶቹ ተሳታፊ እንዲሆኑን ሙሉ መብት እንዲሰጣቸው እንዲያድረግ እንጠይቃለን። 4. በመላው የአማራ ሚድያ ተቋማቶችና የአማራ ተወላጅ ጋዜጠኞች ላይ በሚፍጸምና በመፍጸም ላይ ያለው አፍና፣ እስር፣ እንግልት በአስቸኮይ እንዲቆም እንጠይቃለን። 5.. ሁሉም የአማራ መር ድርጅቶች ሕዝባችንን በማንቃትና በማደራጀት በደጀንነት አብረው ከሕዝባችን ጎን በጽናት እንዲቆሙ ጥሪ እናስተላልፋለን። ከዚሀም ሌላ በተለያዩ የአማራ አደረጃጀት የተደራጁ ድርጅቶች ያላቸውን ልዩነት በማስወገድ በአንድ አመራር ስር የሕልውናውን ትግል እንዲቀላቀሉ ጥሪ እናስተላልፋለን። 6. መላው የአማራ ምሁራን ከተጫነባችሁ ድንዛዜና አድርባይነት ድባብ ፈጥናችሁ በመውጣት በዚህ ወሳኝ በሆነ ታሪካዊ ወቅት ሕዝባችሁን ከጥፋት ለመታደግ አብራችሁ በግምባር ቀደምትነት በመቆም የፖለቲካ ትግሉን እንድትቀላቀሉና የበኩላችሁን ታሪካዊ ድርሻ እንድትወጡ ጥሪ እናቀርባለን። 6. 7. የአማራዉን የሕልዉና ትግል ፈር ለማስያዝና የድል ባለቤት ለማድረግ፣ ከዚያም ባለፈ የኢትዮጵያን ዳር ድንበር፣ክብርና ሎዓላዊነት ለማስጠበቅ፣ አጥንታቸውን በመከስከስ ደማቸዉን በማፍሰስ ላይ ያሉት የአማራ ፋኖዎች ለይ የሚደረገውና በብልጽግና አመራሮች እየተተገበረ ያለው አፈና፣ እስርና ግድይ በአስቸኳይ እንዲቆም ጥሪ ከማድረጋችንም ባሻገር፣ አሁን በእስር ላይ ያሉት ፋኖዎችም ካለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ ጥሪ እናቀርባለን። ክብር የጎሰኞችን ቀንበር ለዓመታት ተሸክሞ ለሚሰቃየውና አሁን በድል ለመወጣት ለሚታገለው ለአማራ ሕዝብ ይሁን !!! “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply