ከቤንሻንጉል እና ከኦሮምያ ክልሎች የተፈናቀሉ ችግር ላይ መሆናቸውን ገለፁ

https://gdb.voanews.com/01460000-0aff-0242-23f5-08da7007ca9a_tv_w800_h450.jpg

በግጭት እና ጥቃት ምክኒያት ከአንድ ዓመት በፊት ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና ከኦሮምያ ክልሎች የተፈናቀሉ ቁጥራቸው የበዛ ተፈናቃዮች ችግር ላይ መሆናቸውን ገለፁ።

ከቤንሻንጉል ካማሽ ዞን ያሶ ወረዳ እና ከኦሮምያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን በ2013 ዓ.ም ተፈናቅለው አሁን በምስራቅ ወለጋ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች ውስጥ እንደሚገኙ የገለፁ ተፈናቃዮች በቂ ድጋፍ እየተደረገላቸው አለመሆኑን ተናግረዋል።

ስሙን ከምስራቅ ወለጋ ዞን አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ወደ “ቡሳጎኖፋ” የቀየረው ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳኜ ለቺሳ በፀጥታ ችግር ምክኒያት መንገድ በመዘጋቱ እህል ለማጓጓዝ ችግር እንደገጠማቸው ገልፀው፤ እየተደረገ ያለው ድጋፍ ከተፈናቃዮቹ ቁጥር አንፃር በቂ አለመሆኑን ተናግረዋል።

ከተለያዩ ቦታዎች የተፈናቀሉ ከ197 ሺሕ በላይ ተፈናቃዮች ድጋፍ እየተደረገላቸው መሆኑን ጠቅሰው፤ ከ110 ሺሕ በላይ ሰዎች ደግሞ ወደ የአካባቢያቸው መመለሳቸውን ኃላፊው ጨምረው ገልፀዋል።

/ሙሉውን የተያያዘው ፋይል ያዳምጡ/

Source: Link to the Post

Leave a Reply