
ከተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች በአማራዊ ማንነታቸው ብቻ ተፈናቅለው በደቡብ ወሎ ዞን ቦረና ወረዳ መካነ ሰላም የሚገኙ ወገኖች የእርዳታ ጥሪ አቀረቡ። ጥር 23 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ከተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች በአማራዊ ማንነታቸው ብቻ በተደራጁ እና የቡድን መሳሪያ በታጠቁ ኦነጋዊያን ተፈናቅለው በደቡብ ወሎ ዞን ቦረና ወረዳ መካነ ሰላም የሚገኙ ወገኖች የእርዳታ ጥሪ አቅርበዋል። ከአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ጋር ቆይታ ያደረጉት ተፈናቃይ ወገኖች እንደሚሉት:_ ከመጋቢት ጀምሮ በ2013 ዓ/ም፣ በ2014 በመስከረም ወር፣ እና ንዲሁም በ2015 ህዳር ጀምሮ ከምስራቅ ወለጋ ዞን አርጆ ጉደቱ፣ ከሀሮ አዲስ ዓለም፣ ከአንገር ጉትን፣ ከሊሙ፣ ከጊዳ አያና እና ከአሙሩ ተፈናቅለው ወደ ደቡብ ወሎ ዞን አቅንተው ቦረና ወረዳ መካነ ሰላም ከተማ የሚኖሩ በትንሹ ከ8 ሽህ በላይ ተፈናቃዮች ይገኛሉ። ተፈናቃይ ወገኖችም በመካነ ሰላም ሶስት የመጠለያ ካምፖች ውስጥ ተጠልለው ይገኛሉ፤ እነሱም:_ 1) በትምህርት ጽ/ቤት ውስጥ ያለ የመጠለያ ግቢ፣ 2) ለገማራ እና 3) ዴባት (መካነ ሰላም ደብር) የሚገኙ ናቸው። እንደ ተጎጅዎች አገላለጽ በአጠቃላይ ከ8 ሽህ በላይ ተፈናቃይ ወገኖች በችግር ላይ መሆናቸው ተገልጧል። አስቸኳይ የሰብአዊ እርዳታ እንዲደረግላቸው ጥሪ አድርገዋል። አሚማ እንደዘገበው “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24
Source: Link to the Post