You are currently viewing ከተጎዱ ወገኖቻችን ጎን በመሆን ሰብአዊ ድጋፍ ያደረጋችሁ እና የምታደርጉ በጎ ፈቃደኞች ሁሉ ከፍ ያለ ምስጋና ይድረሳችሁ! አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ   ሚያዝያ 15 ቀን 2014 ዓ.ም…

ከተጎዱ ወገኖቻችን ጎን በመሆን ሰብአዊ ድጋፍ ያደረጋችሁ እና የምታደርጉ በጎ ፈቃደኞች ሁሉ ከፍ ያለ ምስጋና ይድረሳችሁ! አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሚያዝያ 15 ቀን 2014 ዓ.ም…

ከተጎዱ ወገኖቻችን ጎን በመሆን ሰብአዊ ድጋፍ ያደረጋችሁ እና የምታደርጉ በጎ ፈቃደኞች ሁሉ ከፍ ያለ ምስጋና ይድረሳችሁ! አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሚያዝያ 15 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ አሸባሪው እና ወራሪው ኦነግ ሸኔ ከዘር ማጥፋት ተባባሪዎቹ ጋር በመሆን መስከረም 7/2014 እናት እና አባታቸውን በግፍ በጥይት እና በስለት ከመኖሪያ ቤታቸው እያሉ ነበር የገደለባቸው። አቶ አይሁሩ አሰፋ እና ደብሬ ሽፈራው ከሁለት ልጆቻቸው ጋር ሀገር ሰላም ብለው ለዘመናት ከኖሩበት፣ሀብት ንብረት ካፈሩበት ምዕራብ ሸዋ ዞን ዳኖ ወረዳ አጅላ ዳሌ በተባለ ቀበሌ በቤታቸው ውስጥ ተቀምጠው ነበር። ልክ ከምሽቱ 2 ሰዓት ላይ ባትሪ የሚያበሩ መሳሪያ እና ስለት የያዙ የአሸባሪው እና ወራሪው ኦነግ ሸኔ አባላት እና የዘር ማጥፋት ተባባሪዎቹ አማራዊ ማንነትን እንደ ወንጀል ቆጥረው ወደ እነ አቶ አይሁሩ አሰፋ ቤት በር ሰብረው በመግባት ነበር የጥይት እሩምታ ያርከፈከፉት፤ በስለትም ጭምር ባልና ሚስትን በመግደል 4 ህጻናትን ያለ እናትና አባት ያስቀሩት። የሁሉም ትልቅ መሰረት አይሁሩ እና የሁሉም ትንሽ ወርቃለም አይሁሩ ባጋጣሚ ወደ ገጠር ሄደው ስለነበር የተፈጸመውን ነገር ምን እንደሆነ አልሰሙም። በእለቱ ከእናት አባታቸው ጋር አብረው ከነበሩት መካከል ህጻን አቤል አይሁሩ እንደ እግዚአብሔር ፍቃድ ጣራ ላይ ወጥቶ ሲተርፍ የእሱ ትልቅ ሚሚ አይሁሩ ደግሞ በስለት ተወግታ ወድቃለች፤ ሞታለች በሚል ገዳዮች ጥለዋት ቢሄዱም ፈጣሪ በምህረቱ ጎብኝቷት ለመትረፍ ችላለች። ሚሚ አይሁሩ በአቤት ሆስፒታል በአንዳንድ በጎ ፈቃደኛ ወንድም እና እህቶች ትብብር የህክምና ድጋፍ ተደርጎላት ዛሬ ላይ በመልካም የጤንነት ሁኔታ ላይ ትገኛለች። ትብብር ካደረጉ ወገኖች መካከል የተወሰኑትን በመጥቀስ እናመሰግናለን:_ 1) አቶ ለገሰ ሀብተ ጊዮርጊስ እና 2) መምህር ልዑል፣ ከምዕራብ ሸዋ ዞን ዳኖ ወረዳ ወደ አዲስ አበባ በማስመጣት ከተጨማሪ ጥቃት የታደጉ እና ከአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ጋር ያገናኙና በቅርብ ሆነው የሚከታተሉ ናቸው። 3) ቅድስት ከጀርመን ለመድኃኒት መግዣ ድጋፍ ያደረገች፣ 4) ሙሉ ከአሜሪካ ለቤት ኪራይ፣ ለአስቤዛ እና ለቤት እቃ መግዣ የደገፈች፣ 5) ሰገነት ኃይሌ ከአሜሪካ ቤት ተከራይተው፣ አስቤዛ አሟልተውና ተስፋ ሰንቀው እንዲኖሩ በሙሉ ኃላፊነት እየደገፈች የምትገኝ፣ 6) ጋዜጠኛ መዓዛ መሀመድ_ለአንዳንድ ወጭ በሚል ድጋፍ ያደረገች፣ 7) አማራ ኢመርጀንሲ ፈንድ በየወሩ እየደገፈ ያለ በጎ አድራጎት ድርጅት፣ 😎 አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) አቤት ሆስፒታል ድረስ በማቅናት ሙሉ መረጃውን ሰብስቦ ድምፅ በመሆን፣ በቅርብ ሆኖ የልጆቹን ሁኔታ እየተከታተለ የሚገኝ፣ 9) የሸዋ ሰላም እና ልማት ማህበር (ሸዋሰማ) ስራ አስኪሂያጅ ረ/ፕሮፌሰር ሲሳይ አውግቸው ለትንሳኤ በዓል መዋያ የገንዘብ እና የአልባሳት ድጋፍ በማድረግ፣ የድጋፍ ደብዳቤም በመጻፍ ከጎናቸው መሆናቸውን አረጋግጠዋል። 9) ስማቸው ያልተጠቀሱ ቅን አሳቢ ወንድም እና እህቶች ጭምር ላደረጋችሁት እና ለምታደርጉት ሰብአዊ ድጋፍ ከፍ ያለ ምስጋና ይድረሳችሁ። ምንም ዓይነት ማስረጃ የላቸውም። በክፉዎች ተቃጥሎባቸዋል። በዚህም ትምህርታቸው ተቋርጧል። እኒህን እና መሰል የተጎዱ ወገኖቻችንን በምንችለው ሁሉ በመደገፍ አብሮነታችን ማሳየት የሰው ልጆች ሁሉ ተግባር ሊሆን ይገባል። ዘላቂ መፍትሄ መፈለግ ደግሞ ያልተነካ የኢትዮጵያዊያን ትልቁ የቤት ስራ ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply