ከታሪፍ በላይ ክፍያ ተጓዦችን እያማረረ ነው።ለአረፋ በአል እየተጓዙ የሚገኙ የበአሉ አክባሪዎች ከዚህ በፊት 250ብር የነበረው ታሪፍ አሁን እስከ 1ሺህ ብር ድረስ እየከፈልን ነው ብለዋል።ለአ…

ከታሪፍ በላይ ክፍያ ተጓዦችን እያማረረ ነው

ለአረፋ በአል እየተጓዙ የሚገኙ የበአሉ አክባሪዎች ከዚህ በፊት 250ብር የነበረው ታሪፍ አሁን እስከ 1ሺህ ብር ድረስ እየከፈልን ነው ብለዋል።

ለአረፋ በአል ወደ ተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች በማቅናት ላይ የሚገኙ ተጓዦች የህግ ያለህ ያሉ ሲሆን በአል በመጣ ቁጥር እየደረሰብን ያለው መጉላላት መፍትሔ አልተሰጠውም ሲሉ ተናግረዋል።

ለኢትዮ ኤፍ ኤም የታሪፍ ጭማሪው ከአዲስ አበባ ጀምሮ ነው ሲሉ የተናገሩት በአውቶቢስ ተራ መናኽሪያ የተገኙት ተሳፋሪዎች ወደ ሀገርቤት ለመሄድ ታሪፉ ሹፌሮች የሚያስከፍሉት ሶስት እጥፍ ነው ብለዋል።

ከተመን ውጪ የሆነው የታሪፍ ጭማሪ መፍትሄ እየተሰጠው አይደለም ያሉት ቅሬታ አቅራቢዎቹ ከኹለት ወር በፊት ከአዲስ አበባ በሚገኙ መናህርያዎች ሲከፈል ከነበረው ብር የ700 ብር ጭማሪ መኖሩን ተናግረዋል።

የታሪፍ ጭማሪው የተስተዋለው ከአነስተኛና መለስተኛ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ጀምሮ በሌሎች አገር አቋራጭ አውቶብሶችም ጭምር መሆኑን ቅሬታ አቅራቢዎቹ ተናግረዋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ለመጠየቅ ያደረግነው ሙከራ አልተሳካልንም።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

Source: Link to the Post

Leave a Reply