“ከትላንቱ የቀጠለው የአማራ ህዝብ እረፍት የመንሳት ተግባር በቃ ሊባል ይገባል!” ሲል የአማራ ወጣቶች ማህበር በባህር ዳር ጥሪ አደረገ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 5 ቀን 2014…

“ከትላንቱ የቀጠለው የአማራ ህዝብ እረፍት የመንሳት ተግባር በቃ ሊባል ይገባል!” ሲል የአማራ ወጣቶች ማህበር በባህር ዳር ጥሪ አደረገ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 5 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የፌደራል መንግስት በሁሉም አቅጣጫ የመልሶ ማጥቃት እና ጠላትን ከወረረው አካባቢ የማስወጣት ኦፕሬሽን ተጀምሯል ስለመባሉ አውስቷል። ይሁን እንጅ የአማራ ወጣቶች ማህበር በባህር ዳር እንዳለው መልሶ ማጥቃት ተጀምሯል በተባለበት ማግስት ባለፉት ሁለት ቀናት የጠላት ሀይል በወገኖቻችን ላይ እያደረሰ ያለው ጥፋት እና መስፋፋት ጨምሯል። ማህበሩ ከወሎ አማራ አካባቢ ደረሰኝ ያለውን መረጃ ዋቢ አድርጎ እንደገለጸው በአምባስል ሶስት ቀበሌዎች፣ ማለትም ቀበሌ 13፣ 14 እና 15 ከትላንት በስቲያ ጥቅምት 3 ቀን 2014 ጀምሮ በጠላት እጅ ገብተዋል። በተመሳሳይ በዛሬው ዕለት ጥቅምት 5 ቀን 2014 በውጫሌ አካባቢ ከፍተኛ የሆነ የከባድ መሳሪያ ድብደባ እየተረደገ በመሆኑ ህዝባችን ለከፍተኛ መፈናቀል እና መከራ መዳረጉን ነገረውናል፤ ይህም በቃ ሊባል ይገባል ብለዋል። በወሎ ፣በሰሜን ጎንደር ፣በደቡብ ጎንደር እና ዋግኸምራ ህዝብ ላይ እየተሰራ ያለው ሸፍጥና ሴራ ሁሉም የአማራ ህዝብ አንድ በመሆን በቃን ልንል ይገባል ያለው ማህበሩ በአሁኑ ወቅት በአካባቢው የሚገኘው መከላከያ ሰራዊት ትዕዛዝ አልተሰጠኝም በማለት እየተዋጋ እንዳልሆነ የአካባቢው ምንጮች ለአማራ ወጣቶች ማህበር ገልፀዋል ሲልም አክሏል። የአማራ ወጣቶች ማህበር በባህርዳር በወሎ አማራ አካባቢ እየተከናወነ ያለው የወገኖቻችን ሞት ፣ስቃይ ፣መከራ እና ሀብት ንብረት ውድመት ሆን ተብሎ የተተወ ድርጊት እንደሆነ ፤በወገኖቻችን ላይ ሂሳብ እየተወራረደባቸው (Damage Equivalence) እንደሆነ ምልክቶችን አይተናል ብሏል። በተጨማሪም ከትላንቱ የቀጠለው የአማራ ህዝብን ማህበራዊ ዕረፍት የመንሳት አንዱ አካል የሆነው ድርጊት በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ ማጀቴ አካባቢ በትላንትናው ዕለት አርሶ ፣አለስልሶ ፣ዘርቶ ፣አርሞ እና አጭዶ የከመረውን ጤፍ በፅንፈኛ ኦሮሞዎች ዶግ አመድ ሆኖበታል ሲል ገልጧል። በወለጋ ላለፋት 3 ዓመታት በአማራ ህዝብ ላይ እየተደረገ ያለው ጭፍጨፋ እና ማፈናቀል በመንግስት ግደየለሸነት ፤በመንግስት ይሁንታ እየተደረገ ያለ የአደባባይ ሃቅ ስለመሆኑም ጠቁሟል። ከዚህም በተጨማሪ በመተከል -ጎጃም አማራ ህዝብ ላይ የዘር ማጥፋት ፣መገደል ፣መታረድ እና መፈናቀል ወንጀል ስለመፈጸሙ ገልጧል። በአጠቃላይ “ለውጥ “የሚባለው ከመጣ ጀምሮ የአማራን ህዝብ ካለፈው የቀጠለ ማህበራዊ ዕረፍት የመንሳት ተግባር እየቀጠለ በመሆኑ የአማራ ወጣት እና ህዝብ ይህንን ግፍና መከራ በቃን ልንል ይገባል ሲል ጥሪ አድርጓል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply