“ከትላንትና እብሪተኛና ዘራፊ የወያኔ ቡድን አወዳደቅ በመማር የዛሬዎቹ ተረኛ የኦሮሙማ መሪዎች በአረመኔያዊ ጭካኔ ህይወት ቀጥፎ በአማራ ደም የጨቀየ መሬት የራሴ ለሚሉት ብቻ በባለቤትነት ለመ…

“ከትላንትና እብሪተኛና ዘራፊ የወያኔ ቡድን አወዳደቅ በመማር የዛሬዎቹ ተረኛ የኦሮሙማ መሪዎች በአረመኔያዊ ጭካኔ ህይወት ቀጥፎ በአማራ ደም የጨቀየ መሬት የራሴ ለሚሉት ብቻ በባለቤትነት ለመ…

“ከትላንትና እብሪተኛና ዘራፊ የወያኔ ቡድን አወዳደቅ በመማር የዛሬዎቹ ተረኛ የኦሮሙማ መሪዎች በአረመኔያዊ ጭካኔ ህይወት ቀጥፎ በአማራ ደም የጨቀየ መሬት የራሴ ለሚሉት ብቻ በባለቤትነት ለመያዝ የሚደረገው ጉዞ አንድም ቀን የምንታገሰው መሆን የለበትም።” ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት (ሞወዐድ) በወቅታዊ ጉዳይ የሰጠው መግለጫ! አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ጥር 20 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ “ትግላችን ትውልድ ተሻጋሪ ነው።የዐማራው መደራጀት የኅልውናው እና የማንነቱ መሠረት ነው።” የሚለው ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት በወቅታዊ ጉዳይ የሰጠው መግ የግለሰቦችን ሰብዓዊ መብት የሚጨፈልቅና ንፁሀንን በማንነታቸው በጅምላ ኢንዲጨፈጭፉ የሚፈቅደው ህገመንግስት ሳይቀየር ምርጫ ማሰብ፣ ኢትዮጵያን ወደባሰ አደጋ የሚወስዳት ነው። በለስ ቀንቶት በድጋሚ የኢትዮጵያን በትረ ስልጣን የተቆጣጠረው የቀድሞው የትግራይ ወያኔ ኢህአዲግ ስሙንና ነገዱን ቀይሮ የዛሬው የኦነግ/ ኦዴፓ ብልፅግና ወደከፋና ወደተባባሰ የመከራ ማጥ ውስጥ ዘፍቆን በለቅሶና በሀዘን ሶስት አስከፊ አመታትን አሳልፈናል። ህገ መንግስት ተብየው የወያኔ ህገአራዊት በዶ/ር አብይ አስተዳደር የአንዳንድ ነገዶችን ጎጅ ባህል እንዲያቆጠቁጥና ጠላት የተባለው አማራ እንዲታረድ፤ ስጋው በሰው እንዲበላ እየተደረገ ነው። በአለም ላይ ባልተወከለበት ህገመንግስት በባርነት የሚገዛው አማራ ብቻ ነው ብሎ ሞረሽ ወገኔ የአማራ ድርጅት ያምናል። ህገ መንግስቱ የአማራ ብሎም የኢትዮጵያ መጥፊያ ፀረ ሰው ህገመንግስት፣ የጎሳ ክልል አወቃቀሩ አፓርታይዳዊ የሆነ ፀረ ሰውና ፀረ ማህበረሰብ ነው። ባለ ዘጠኝ ክልል የነበረው አከላለል በፌዲራል መንግስቱ ህገመንግስት ህግ ተጥሶ ዛሬ ባለ 10 ክልል መሆኑ ይታወቃል። የዘጠኙ ክልል አወቃቀር ለኢትዮጵያውያን አንድ አይነት መብት አይሰጥም። ነገር ግን በአማራ ክልል ተብየው ያለው ክልሉ የኑዋሪዎቹ ሁሉ ስለሆነ ሁሉም ነገድ ባለመብት ነው። መምረጥ መመረጥ ስራ መቀጠር ይችላል። ቁጥራቸው 500 000 የማይሆኑት የኦሮሞ ተወላጆች ዞን ስላላቸው በሳቸው ቋንቋ በሚፈልጉት መሪ እንዲተዳደሩ ፈቅዷል። በክልሉም ውክልና አላቸው። በቀሩት 9ኙ ክልሎች ግን ክልሉ ለተመረጡ የቋንቋ ማህበረሰቦች ብቻ ነው። ለምሳሌ አሁን የገሃነም ምድር በሆነው የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል የክልሉ ባለቤቶች የሚባሉት ብሔር፣ ብሔረሰቦች በርታ፣ ጉሙዝ፣ ሽናሻ፣ ማኦ እና ኮሞ ናቸው ይላል። በዚህም ምክንያት በቁጥር ከሁሉም የሚበልጠው አማራ በሚኖሩበት ዞኖች ሳይቀር በግፍ በቀስት ይገደላል፤ ስጋውም በሰው ይበላል። እንዲሁም በወያኔ የኦሮሞ ክልል ተብሎ በተከለለው አካባቢ ከ 15 000 000 በላይ አማራ እየኖረ፣ አማራ በክልሉ ምንም አይነት ውክልና እንዳይኖረው ተደርጎ፣ የመምረጥና መመረጥ መብት የለውም፤ እንዲሁም የስራ እድል ተነፍጓል። ከዚያም ባለፈ ከ1983 ዓ/ም ጀምሮ አማራን ሲያስገድሉ የኖሩት ኦነጋውያን ሌንጮ ባቲና ሌንጮ ለታ የአሁኑ ጠቅላይ ሚኒስትር የዶ/ር አብይ አህመድ አማካሪ ሲሆኑ፤ ባለፉት 3 ዓመታት “የለውጥ ወቅትም” በተባባሰ መንገድ በኦሮሙማ አራማጅ የመንግስት አካሎች ድጋፍ አማራውን በወለጋና በመሳሰሉት እያስጨፈጨፉ ነው። በኦነጋውያኑ አማካሪነት ስራቸውን የሚያከናውኑት ጠቅላይ ሚኒስትር ግድያ ለማስቆም በሚል ሰበብ ወደ መተክል/ቤኒሻንጉል ጉምዝ ተጓዙ። ዶ/ር አብይ አማራ ገዳይ ናቸው ከሚላቸው የቤኒሻንጉል ጉምዝ አመራርና የተመረጡ የግድያው ተባባሪዎች ጋር በአዳራሽ ጉባዔም አደረጉ። በስብሰባው ላይ አማራ እንዳይሞት የሚረዳ ውይይት ሳይሆን የአማራን ክልል ልዩ ኃይል ስም የሚያጎድፍና የመክሰስ ብሎም የአማራን ስም የማጠልሸት ምክክር አድርገው ተመለሱ። ከምክክሩ በኋላ 24 ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ግድያው ተጠናክሮ ቀጥሎ ከ250 በላይ ንፁሃንን አሳርዶ ከመተከል ዞን ብቻ ከ97 000 በላይ ህዝብ ያለእለት ልብስና ጉርስ እንዲፈናቀሉ ተደርጓል። በአንድ ሳምንት ብቻ በኮንሶ 66 ሰው ሲገደል 132 000 ሺ ሰው ተፈናቅሏል። በሱማሌ 30 የሱማሌ ተወላጅ ተገድሏል። ኢትዮጵያ እንዲህ የደም መሬት የሆነችው የወያኔው ዘር ተኮር ህገመንግስት በተረኞቹ ኦዴፓ/ ኦነግ ተግባራዊ እየተደረገ በመሆኑ ነው። የዶ/ር አብይ መንግስት ኃላፊነትን ባለመወጣቱ የንፁሃን ደም በግፍ የሚፈሰው በመላው ኢትዮጵያ ነው። ለዚህም ዋናው ምክንያት ዘርን መሰረት ያደረገው ክልላዊ አደረጃጀትና በኢትዮጵያ ልክ ኦሮሙማን ለመፍጠር የሚደረግ የአክራሪና ዘራፊ የኦሮሞ ፓለቲከኞች ህገወጥነትና ዘር ተኮር ግጭት በመፍጠር ኦሮሞ ያልሆኑትን ነገዶች የማጥፋት የሴራ ፓለቲካ ነው። ለዚህም ነው የመተከል አማራ፣ አገውና የሽናሻ ህዝብ የዘር ጭፈጨፋ እልቂት በመንግስት የታገዘ መሆኑን የአይን እማኖች የሚመሰክሩት ። ሰሞኑን የጎጃምን ክፍለሀገር 40% በላይ የቆዳ ስፋት በመያዝ አካል የነበረውን መተከል የአማራው ደም በአሰቃቂና መጠነ ሰፊ በሆነ ሁኔታ የሚፈስበት ዞን ሆኗል። ይህ የአማራና አገው ማህበረሰቦች ብዙሀን የሆኑበት መተከልን የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር ላለው እኩይ ዕቅድ አፈፃፀም ይመቸው ዘንድ የቤንሻንጉል ጉምዝ የአፓርታርታይድ ክልል ውስጥ አጥሮታል።ይህ መተከልን ኢፍትሀዊ በሆነ መንገድ ወደ ቤንሻንጉል ጉምዝ አካል መሆን እና ፍጹም አፓርታይዳዊ የሆነው ህገ አራዊት ብዙ የአካባቢው ነዋሪዎችን በተለይም አማራውን ክፍተኛ ዋጋ አስከፍሏል። ትህነግ ዘራፊነቱንና የታላቋ ትግራይን የመፍጠር ህልሙን እውን ለማድረግ በጠላትነት የፈረጀውን አማራ በክልሉ ውስጥ ዜግነቱን ገፏል፤ የዘር ማጥፋትና ሌሎች ብዙ አሰቃቂ ወንጀሎች ተቀባይ ሆኖ 27 የሰቆቃ አመታትን አሳልፏል። በጥገና ለውጥ ስልጣን የተረከበው የኦህዴድ /የኦሮሞ ብልፅግና መራሹ የመንግስት አካላት የሚሳተፉበት ዜጎችን በማንነታቸው መፍጀትና ማሳደድ በብዙ እጥፍ ተባብሶ ባለፉት ሦስት አመታት እያየነው ያለው ዘግናኝ እውነታ ነው። የወያኔን አስተሳሰብ ተሸካሚ የሆነው ተረኛው የኦሮሙማ እንቅስቃሴ ቤንሻንጉል ጉምዝን ለመሰልቀጥና በኢትዮጵያ ህዝብ ሃብት የተገነባውን የአባይ ግድብ የኦሮሞ ብቻ የማድረግ ህልም እውን ለማድረግ ክልሉን የደም መሬት አድርጓታል።የኦሮሞ ብልፅግና አመራሮችና ተባባሪቹ የቤንሻንጉል ጉምዝ ብልፅግና አመራሮች ከተጠያቂነት የማይድኑበት አሰቃቂ ወንጀሎች እየተፈፀሙ ናቸው።አገውና ሽናሻው በተለይ አማራው በየቀኑ በገፍ እየተጨፈጨፉ ፣ቤታቸው እላያቸው ላይ እየተቃጠለ፣ ለዘመናት ከኖሩበት ቀያቸው እየተፈናቀሉ ባገራቸው ለስደተኝነት ተዳርገዋል። ከትላንትና እብሪተኛና ዘራፊ የወያኔ ቡድን አወዳደቅ በመማር የዛሬዎቹ ተረኛ የኦሮሙማ መሪዎች በአረመኔያዊ ጭካኔ ህይወት ቀጥፎ በአማራ ደም የጨቀየ መሬት የራሴ ለሚሉት ብቻ በባለቤትነት ለመያዝ የሚደረገው ጉዞ አንድም ቀን የምንታገሰው መሆን የለበትም። ይህ ህይወት እያጠፋ ያለ አረመኔነትን ባስቸኳይ በማስቆም የዜጎችን ሰላም የመጠበቅ መንግስታዊ ኃላፊነቱን መወጣት የተሳነው ወይም የማይፈልገው የአብይ አህመድ መንግስት ስልጣኑን እንዲለቅ የኢትዮጵያን እንደሀገር መቀጠል የሚፈልግ ሁሉ በአንድነት ቆሞ መታገል ይኖርበታል። ትላንት ዘራፊዎችና ገዳዮች የነበሩትን ወያኔዎች ለሚያይ ሁሉ በተመሳሳይ ሁኔታ በተረኝነት ስሜት በህዝብ ላይ የሚያደርሱት ዘግናኝ ወንጀሎችና ዘራፊዎች እጣቸው ተመሰሳይ እንደሚሆን ታሪክ ትልቅ ምስክር ነው። መከላከያ ሰራዊት ከፓለቲካ አቋም ውጭ ሀገርና ህዝብን ጠባቂ መሆን ሲገባው የዘር ፓለቲካው ባመጠው ጣጣ የትግራይ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ከወያኔ ጋር ተመሳጥረው ጓዶቻቸውን ከድተው አስጨፍጭፈዋቸዋል። ከወያኔ ጋር በተደረገው ጦርነት ዶ/ር አብይ ድል ቁርሱ፣ ግስላው፣ አነፍናፊው ወዘተ ያሉዋቸውም ሰሜን እዝ ላይ የአማራ ወታደሮችን ከወያኔ ጋር ተመሳጥረው የፈጁ ሴረኞች ኦነጋውያን እንደሆኑ እየተሰማ ነው። እነ ጀኔራል ብርሀኑ ጁላና ኃይሉ ጎንፋ በሚናገሩት ፀረኢትዮጵያዊ ንግግር እንደኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከፓለቲካ አቋም ውጭ ሀገርና ህዝብን ጠባቂ ሳይሆን የአክራሪ የኦሮሞ ፓለቲከኞች አፈቀላጤ ወይም የብልፅግና ፓርቲ መከላከያ መሆናቸው ለመላው ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ስጋትን ይፈጥራሉ። የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትም በዚህ የአፓርታይድ ህገመንግስት ውስጥ እያለ እራሱን ከዘር ፖለቲካ ከፍፍልና በውስጥ ጠላቶች ከመጠቃት አላዳነውም። ሰራዊቱ ከመዋቅራዊ በሽታ ተላቆ የሀገርን ዳር ድንበር ከታሪካዊ ጠላቶቿ ለመጠበቅ የሚያስችለውን ሙሉ ጥንካሬ ሊያገኝ የሚችለው የትህነግ አፓርታይድ ህገመንግስት በህዝብ ሰፊ ተቀባይነት ያገኘ ፍትሀዊ ህገመንግስት ሲተካ ብቻ ነው። ለዚህም እውን መሆን በኢትዮጵያ የዜጎችን ሰላም፣ አንድነትና፣ እኩልነት ለማምጣት የሚታገሉ ኃይሎች ሁሉ ተባብረው እንዲቆሙ ሞረሽ ወገኔ ዐማራ ድርጅት ወገናዊ ጥሪአውን ያቀርባል። ስለዚህ ኢትዮጵያ አገራችን በትክክለኛ መንገድ እንድትመራ ካስፈለገ፤ በተለይም በህዝብ ተቀባይነት ያለው መንግስትን ሊወልድ የሚችል ነጻና ታማኝ ምርጫ ሚኪያሄድ የሚከተለቱ ቅድመ ሁኔታዎች መሟላት ይገባቸዋል። 1) በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች የዚጎች በሰላም የመንቀሳቀስና የመኖር መብት ኢንዲረጋገጥ፣ 2) የሰባዊ መብታቸው ተደፍሮ በሀገር ውስጥ ለመፈናቀል የተገደዱ ሁሉ አስፈላጊው መቋቋሚያና ድጋፍ ተደርጎላቸው ወደቀያቸው እንዲመለሱ መንግስት ግዴታውን እንዲወጣ፣ 3) ትክክለኛ የህዝብ ቆጠራ ተደርጎ የኢትዮጵያ ህዝብ ቁጥር በእድሜና በፆታ ተለይቶ እንዲታወቅ፣ 4) ተፎካካሪ የፖለቲካ ድርጅቶች ከመንግስት ጫና ተላቀው ያለምንምን ገደብ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍል እንዲቀሳቀሱ መንግስት ተገቢውን ኃላፊነቱን መወጣት፣ 5) ህገመንግስቱ ከፋፋይና የዘር ማጥፋት ወንጀልን የሚያስፈፅም ሰለሆነ እንዲቀየር፣ 6) ክልላዊ መንግስት ተብሎ የተካለለው የዘር አከላለል ብዙሀኑን ከ 80 በላይ ያለ ነገድ መብት የማያስከብርና ጠብ አጫሪ፣ ብሎም አብሮ ተዋዶ፣ ተጋብቶና ተዛምዶ የኖረን ነገድ የሚያራርቅ ስለሆነ ክልላዊ አወቃቀሩ ከጎሳ የፀዳ እንዲሆን፣ 7) በየትኛውም አካባቢ ከሰሜን እስከደቡብ ለተፈፀመውና ለሚፈፀመው ግድያና ማፈናቀል ከፓለቲካው ገለልተኛ በሆነ አካል አጣሪ ኮሚቴ ተጣርቶ ይፋ እንዲሆን፣ 8) ማንነትን መሰረት ያደረገውን የዘር ጭፍጨፋ እውቅና መበስጠት በግፍ ለተጨፈጨፉት ወገኖቻችን የመታሰቢያ ቀን እንዲወሰንላቸው፣ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ከየትኛውም የአገራችን ክፍል የተገኘን ሰዎች በየትኛውም አካባቢ ብንገኝ በሀገራችን ታሪክ ብንስማማም ባንስማማም፣ በሀይማኖትና በጎሳ ብንለያይም በሰላም ለመኖር እንችል ዘንድ፣ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በሰውነቱ ብቻ የፓለቲካ ውክልና ኖሮት በሰላም እንዲኖር ከላይ የተጠቀሱት ነጥቦች ከምርጫው በፊት የተሟሉ ሊሆን ይገባል፤ የጠ/ሚ አሻጋሪነት በሚያሳፍር መልኩ በመክሸፉ ኢትዮጵያን ካለችበት የጨለማ ጊዜ ወደተስፋ ዘመን ጅማሮ የሚያደርሰን ሰፊ የህዝብ ድጋፍና አመኔታ ያለው የሽግግር መንግስት እውን እንዲሆን ሰፊ እንቅስቃሴ ይደረግ ዘንድ ሞረሽ ወገኔ የአማራ ድርጅት ጥሪ ያቀርባል። አንድ ዐማራ ለሁሉም ዐማራ፤ ሁሉም ዐማራ ለዐንድ ዐማራ! ፈለገ አሥራት የትውልዳችን ቃል ኪዳን ነው!

Source: Link to the Post

Leave a Reply